ሠርግ በሰው ልጅ ሕይወት የሚፈጸም ልዩ ምሥጢር ነው። መድኃኔ ዓለም እና እናቱ አንዲት ዕለት በሙሽሮቹ ቤት ታድመው የቃና ዘገሊላው ድንቅ ተአምር ታየ ፤ የጎደለው ሞላ ፤ ያስጨነቃቸው ተፈታ ፤ ያላሰቡት ያልጠበቁት ተሰጣቸው ፤ የደስታው ጥሪ የደስታ ሆኖ ተደመደመ።
የእኛ ሕይወት ቃና ዘገሊላ ነው በክብር እናትና ልጁን ወደ ሕይወታችን ብንጠራቸው ፤ የጎደለው ይሞላል ፤ ያስጨነቀን ይፈታል ፤ ያላሰብነው ያልጠበቅነው ይሰጠናል።
አባ ጊዮርጊስ በሰዓታት ምስጋናው ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን “ቃልኪ መናዝዝ(ቃልሽ የሚያጽናና ነው) ገጽሽ ጨለማን የሚያርቅ መብራት ነው ፤ እንደ ቀን ዘወትር ያበራል ፤ ልጅሽም ማጣትን የሚያስረሳ በረከት ነው” ይላታል።
+ እናቱና ልጁን አክብረን የምንጠራቸው አንድ ዕለት እንዲታደሙ ሳይሆን እስከ መጨረሻው በእኛ ሕይወት እንዲኖሩ ቢሆን ደግሞ ፤ ሕይወታችን ምን ሊመስል ይችል ይሆን? ምን አይነት ድንቅ ይታይበት ይሆን? ለምን ያህል ዘመናት በትውልድ የሚነገር የሚታወስ ይሆን?
+ ድንግል ሆይ! በእምነትም በእውቀትም የጎደልን ልጆችሽን ፤ አምላከ ብርሃን የተባለ የእውቀት የእምነት ባለቤት ልጅሽ በእምነትና በእውቀት እንዲሞላን አሳስቢልን! ልጅሽ የሕሊናችንን ጨለማነት አርቆ ተናግረን የምንደመጥ ለቀመሱን እርሱ የሚመሰገንብን በጎ ባሪያዎቹ ያድርገን።
መልካም የቃና ዘገሊላ በዓል ይሁንልን!
ጥር 12 2016 ዓ.ም
🕯✨ ✝️መልካም በዓል✝️✨🕯
✨✨✨✨✨✨
✝️@orthodox_graphics_tub✝️