#ትላንት_ዛሬ_ነገ
ዘመን ሳይዘምን ገና፣ ጸሐይ ሳትታይ በፊት፣ ጨረቃም ሳትወጣ ቀድሞ፣ ሰማይ ሳይዘረጋ፣ ምድርም ሳትቆም፣ ከዋክብት ሳይታዩ፣ ወንዞች ሳይፈሱ፣ ውቂያኖስ ሳይሞላ፣ አዕዋፋት ሳይበሩ፣ ፍጥረታት ሳይፈጠሩ፣ አራዊት ሳይኖሩ፣ ሰውም በምድር ላይ ሳይታይ፣ የሚታዩ እና የማይታዩት ፍጥረታት ሳይኖሩ፣ አመታት ሳይቆጠሩ፣ ወራት ሳይፈራረቁ፣ ሳምንታት ሳይቀያየሩ፣ ቀናትም አሃዱ ሳይባሉ፣ ሰዓታት ሳይቆጥሩ፣ ደቂቃና ሰከንዶች ሳይጀምሩ ብቸውን የነበረ፣ ከዘላለም በፊት የከበረ፣ ከመጀመሪያ በፊት ሆኖ መጀመሪያን ያስጀመረ፣ ከሁሉ ነገረ በፊት የነበረ፣ አንድ ተብሎ ቁጥር የማይጀመርለት፣ ለዘመኑ ቁጥር የሌለው እርሱ እግዚአብሔር ነው። ትላንት የነበረ እርሱ አምላካችን ነው።
አለም በኃጢያት ወደቃ፣ በሴሰኝነት ወጥመድ ገብታ፣ ሰው ክብሩን ጥሎ ቀሎ እየኖረ፣ ለአምላኩ ትቶ ለሆዱ እያደረ፣ ጽድቅ የሆነውን ለቆ ለበደል እየኳተነ፣ ፍቅርን ከመየዝ ይልቅ ጥላቻን እያነገበ፣ ቅን የሆነውን ረስቶ ለተንኮል እየነቃ፣ ሰው በብዙ ልከ በልሆነ ነገር ውስጥ ሆኖ እርሱ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ እያየ በዙፋኑ ላይ አለ። ትላንትን አሳልፎ አሁንን የሰራ፣ ያለፈውን የሚያውቅ ያለውን የሚያኖር፣ ዛሬን ከዘላለም በፊት የሚያውቃት፣ ሁሉን የሚገዛ ሁሉን የሚያስተዳድር፣ ሁሉን የሚመገብ ደግሞ ሁሉን የሚጠብቅ፣ ዛሬ በምንለው በየትኛውም ዛሬ ላይ ሁሌ ያለ እርሱ ፈጣሪያችን ነው።
ሁሉ ካለፈ በኋላ የማያልፍ ፣ ሁሉም ነበር ከሆነ በኋላ ነበር የማይባልለት፣ ከዘላለም በኃላ የሚኖር፣ እስከ ተብሎ የማይገደብ፣ በቃ ተብሎ የማይቋጭለት፣ ሁሉን በነበር መጥራት የሚችል፣ አሁን የለም የማይባልለት፣ የዘመን ቁጥር የማይሰላለት፣ የጊዜ ቀመር የማይቀመርለት፣ የእድሜ ገደብ የማይበጅለት፣ ሁሉ አልፎ የሚኖር እርሱ እግዚአብሔር ጠባቂያችን ነው። ነገን ያያት ነገን የሚያውቃት ነገም የሚኖር እረሱ መድሃኒታችን ነው።
ትላንት የነበረ አሁንም ያለ ዘመናትን አሰልፎ የሚኖር እርሱ እግዚአብሔር ነው። ስሙ ይክበር ይመስገን። አሜን
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
@orthodox_new_mezmur