ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት dan repost
ቅዱሳት መጻሕፍት፦
ሁሉም ሰው እንደ አቅሙ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያነብ ይሆናል።ስናነባቸው በምን የመረዳት ደረጃ ውስጥ ሁነን ነው? ንዑስ መግቢያ የሚሆኑ መሠረተሀሳቦች ከዚህ ታች ተቀምጠዋል፦
[ ] ፩.በንባብ፣
[ ] ፪.በትርጉም፣
[ ] ፫.በአረዳድ፣
[ ] ፬.በምሥጢር፣
[ ] ፭.በሕይወት፣
[ ] ፮.በተስፋ..የከበሩ ናቸው።
በንባብ የከበሩ ናቸው፦ማለት ቃለ እግዚአብሔር ረቂቅ ሁኖ ሳለ በመጽሐፍ ከመጻፉ የተነሣ በዓይን የሚታይ በጆሮ የሚሰማ ሁኗል።ይህ ቅዱስ ቃል የሚነቡብ የሚታይ እንደመሆኑ መጠን የላይ የላዩ ንባብ ዘር ይባላል።
[ ] በትርጉም የከበሩ ናቸው ማለትም፦ ሁሉም የቅዱሳት መጻሕፍት ንባብ ትርጉም የሚያሻው እንደመሆኑ መጠን በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተቀመጠውን ሀሳበ እግዚአብሔር ለማወቅ የግድ ትርጉም ያስፈልጋል።እየተነበበ የሚተረጎም ቃለ እግዚአብሔር ዋና መሠረተ ሀሳቡ ሲተረጎም ለሰሚ ልቡና የተረዳ ይሆናል።
በአረዳድ የከበሩ ናቸው ማለትም፦ ተነበው እና ተተርጉመው ጥንተ መሠረቱን ሳይለቁ ፈቃደ እግዚአብሔርን የምንረዳባቸው ናቸው ማለት ነው።የቅዱሳት መጻሕፍት አረዳድ ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን ኅብረታዊ መሠረተ ሀሳብ ይዘው የሚቀጥሉ ናቸው እንጂ ዘመን አመጣሽ ሁነው መረዳት አይችሉም።
[ ] በምሥጢር የከበሩ ናቸው ማለትም፦የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና አረዳድ ለቅዱሳን የተገለጠውን ሃይማኖት እና የድኅነት ምሥጢርን መጠበቅና ለሰው ሁሉ መስጠት ሲችሉ ነው።የቀለም ሠረገለ መዳረሻው ወደ ትክክለኛ ምሥጢረ ድኅነት መሆን አለበት።
በሕይወት የከበሩ ናቸው ማለትም፦ተነበው፣ተተርጉመው፣ተረድተው፣ተመሥጥረው ሰውን ሁሉ በትክክለኛው የወንጌል ሕይወት ማኖር ይችላሉ ማለት ነው።የቅዱሳት መጻሕፍት ዓላማ ሰምቶ ለሚተገብራቸው ሁሉ ሕይወትን ማሰጠት ነውና።የሰማነው ያወቅነው ቃል በሕይወት ሲተረጎም የሚኖር ቃል ይሆናል እንጂ የሚነበብ ቃል ብቻ አይሆንምና።
[ ] በተስፋ የከበሩ ናቸው ማለትም፦በዚህ ዓለም የቅዱሳት መጻሕፍትን ሀሳብ ጠብቆ የኖረ ሰው ሁሉ ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ማግኘቱ አይቀሬ ነውና።ከሚታየው በኋላ፣ከሞት በኋላ፣ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ፣ የሚገኘውን ጸጋ ክብር ማግኘት የሚቻለው ዛሬ በቅዱሳት መጻሕፍት የተነገረውን ተስፋ ተረድቶ በመጠበቅ ላይ ጸንቶ በኖር ነውና።
ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናነብ ባጭሩ መታሰብ የሚገባቸው ቅደም ተከተሎች እነዚህ ናቸው።