ኦርቶዶክሳውያን አስተማሪዎች እና አባቶች፦እንዲህ ቢሆኑ ጥሩ ነው።
ኦርቶዶክሳዊነትን ለማስቀጠል የክርስትና አደራን በሐዋርያዊነት ጠብቀው አስተምረው ለትውልድ የሚያቀብሉ አስተማሪዎች👇
=-ጥንቁቅ፣ጭምጥ፣ቁጥብ፣ሥውር፣ግልጽ የተራራ መቅረዝ መሆን አለባቸው።
=-በአርአያነት የሚያስተምሩ አባቶች፦ ለእግዚአብሔር መታመን፣ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ድኅነትንም ማመን፣ለሚያስተምሩት ምእመን በአባትነት መታመን መቻል አለባቸው።
=-ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች፦ግልጽ በሆነ የወንጌል ራዕይና የሐዋርያዊ አስተምህሮ ፍኖተ-ድኅነት መጓዝ መቻል አለባቸው።
=ኦርቶዶክሳውያን አስተማሪዎች፦
በተገለጸ ክርስቲያናዊ የወንጌል ዕቅድ እና ዘመኑን በተላበሰ የትኩረት አቅጣጫ ወንጌልን እያስተማሩ መመራት አለባቸው።
=-ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች፦
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ቅን እና አገልጋይ መስቀል ተሸካሚ መሆን አለባቸው።
=ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች፦ በእግዚአብሔር አማኝ፣ሁል ጊዜ የሚማር ትምህርት መማርን ያላቆመ፣ወቅቱን ሁኔታውን የተረዳ፣እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰማህትነት ህሊናን የተላበሰ፣እንደ ሰሎሞን ፍርድን ያስተካከለ፣መሆን አለባቸው።
=-ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች፦
በምንም አይነት ምድራዊ ጥቅም የወንጌልን እውነት መባያ የማያደርጉ፣በመስቀሉ የማይቆምሩ፣ምላስ አስልተው የማይሸነግሉ፣የሚሉትን የሚያስተምሩትን የሚኖሩ፣አውግዠ እስክመጣ እየፈጨሽ ቆይኝ የማይሉ፣በዓለም ቢኖሩም የምናኔ ሕይወትን የተላበሱ፣እንደ ኤልያስ እንደ ዮሐንስ ለእውነት የሚኖሩ፣የአክዓብ የሄሮድስን ግርማውን ማማውን አይተው የማይፈሩ..መሆን አለባቸው።
-መንፈሳዊ አስተማሪዎች፦
ትምህርት፣ዕውቀት፣መረዳት፣ኅብረት፣ተግባር፣ተስፋ..ያላቸው የሐዋርያት ልጆችና ተከታዮች መሆን አለባቸው።
እንዲህ እንሆን ዘንድ የቅዱሳን አምላክ ይርዳን።
ከምሠራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት ገጽ