ቤተ ክርስቲያን ተቀርጸን የምንወጣበት ተቋም ናት
(ለወላጆች እና ለአሳዳጊዎች)
በልጅነት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተቀርጸን ስናድግ እጅግ መልካም ነው። ጅማሮ በመልካም ቦታ ከሆነ አዎን ፍጻሜውም ያማረ ይሆናል። መጨረሻው የሚያምረው መጀመርያው ያማረ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ነው። ልጆቻችንን ወደ ቤተ ክርስቲያን የምንልከው ደግሞ መልካም ሰዎች እንዲወጣቸው ብቻ ሳይሆን ቅዱሳንን እንዲሆኑ ነው።
ልጆች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰጥቶ ማሳደግ ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር እንዲኖራቸውና ለሃይማኖታቸው ባዕድ እንዳይሆኑ ያደርጋል። ቅዳሴው ሰዐታቱን ኪዳኑን በልጅነት ካልታወቀ ዕድሜ ከገፋ በኋላ የሚመጣ ንዝላልነት እና ስንፍና ለቤተ ክርስቲያን እና ስርዐቷ ባዕድ ያደርጋልና ከልጅነት የተኮተኮተ ፍቅረ እግዚአብሔር በወጣትነት በጎልማሳነት ያፈራል። በእሮግናም ክብር ይሆናል።
ልጆች እንዴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳሉ
ነገር ግን ልጄን እንዴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ዝም ብዬ እልካለው የሚል የወላጆች ፍርሃት አለ። እንደ እውነቱ ልጅን በፍርሃት ማሳደግ ከምንም አያድነውም። በዓለም ከስንት ነገር ጠብቀንስ ይቻላል። ባይሆን ልጅ በእምነት ሲያድግ መልካም ነው። እግዚአብሔርን በማመን ያደገ ልጅ ጠንካራ የሚጠቅመውን እና የሚጎዳውን የሚያውቅ በመንፈሳዊ ህይወቱም ብርቱ ዘወትር የሚያድግ ይሆናል። ፍርሃት ሳይሆን እምነት ልጅን ጤናማ አድርጎ ያሳድጋል። ልጆች መንፈሳዊ እንዲሆኑ የሚደረግ የወላጆች ትጋት ወላጆችንም መንፈሳዊ ያደርጋል። የአንድ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ለመረዳት ህጻናቶቿን ላይ እየሆነ ያለውን መመልከት ነው።
ልጆች እንዴት ይደጉ
ሀገራችንን ስንመለከት ደግሞ በእውነት እግዚአብሔር ካልሆነ በማን መታመን ይቻላል? ልጆቻችንን ጠንቅቀው በሃይማኖት እንዲያድጉ የንባብ የጸሎት የምጽዋትን ፍቅር በልባቸው እንኮትኩትባቸው። ለሰው መራራትን ለሕገ እግዚአብሔር ያለ ቀናኢነት በልጅነት ካልተሰራ በኋላ አይመጣም። ቢመጣ ብዙ ያለፋል። ስለዚህ እንዲህ እናሳድርግ
፠ ልጆቻችንን በአደራ ለአብነት መምህራን ወስደን እንስጥ ዘወትርም እንከታተል
፠ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ቀጥታ እንከታተል
፠ ከትምህርት ሰዓት ውጪ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንቆጣጠር
፠ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያፈሩትን ጓደኛ እንመልከት
፠ ቤተክርስቲያንን እንደ መዋያ ሳይሆን ሕይወት ይመለከቷት ዘንድ መንፈሳዊ አቅጣጫ እንስጥ
፠ ከሥርዐተ አምልኮት ከቅዳሴ እንዳይርቁ ክትትል እናድርግ
፠ ሚዲያን ስልክን ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እናስለምድ
፠ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና የቅዱሳንን ህይወት ማወቅ ከልጅነት ይተረክላቸው
፠ ቅዱሳንን አርአያ እንዲያደርጉ ከቅዱሳን ጋር ቤተሰብ እናድርጋቸው።
፠ ካህናት ማናገር እና ንስሐሃም ይለማመዱ
፠ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ባለው ማንነታቸው እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚቀረጸው መካከል ተስማሚነት ላይ አተኩረን እንስራ።