“የአብነት መምህሩና ተማሪዎቻቸው ጭፍጨፋ የሥርዓቱ ሃይማኖት ጠልነት ማሳያ ነው!”
-በራያ በመንግስት ኃይሎች የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
በራያ አላማጣ ወረዳ፣ጥሙጋ ቀበሌ፣ ጥሙጋ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ሥር የሚገኙ አረጋዊ የአብነት መምህርና ተማሪዎቻቸው በጭካኔ ተረሽነዋል። የሰባ ሦስት ዓመቱ የኔታ ገብረ መድኅን በአካባቢው የታወቁና የተከበሩ የድጓ ሊቅ፣ በአገር ደረጃ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም ያፈሩ ነበሩ። የካቲት ፳፯ ቀን ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ወንበር ዘርግተው ማስተማር እንደጀመሩ ወደ ፲ ሰዓት ከ ፵ ደቂቃ ላይ ያልታሰበ እሩምታ ተኩስ ተጀመረ ይላሉ ኹኔታውን በቅርበት የተከታተሉ እማኝ።
እሩምታው እንደቆመ ፈራ ተባ እያልን ለማረጋገጥ ወደ አብነት ትምህርት ቤቱ ስንደርስ ዘጠኙ መሬት ላይ ወድቀዋል። በዚኽም መምህሩና ሦስት ተማሪዎቻቸው ወዲያው ሲሞቱ አምስቱ ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል። ከቆስሉት ተማሪዎች መካከል አንዱ ከጊዜ በኋላ ሕይወቱ አልፏል። የመንግሥት የፀጥታ ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ ያሏቸው ሰዎች መጥተው ‘ስንት ሰው እንደሞተ አረጋግጣችሁ ንገሩን፣ መረጃውን ግን ለማንም ብትናገሩ እንገላችኋለን’ እያሉ እንደዛቱ ለመገንዘብ ችለናል። በዚኽም ግድያው ኾን ተብሎና ታቅዶ ለመደረጉ ፍንጭ ይሰጣል።
በደረሰን መረጃ መምህሩ ማየት የተሳናቸው ናቸው። በዛሬው ዕለትም በአጥቢያው ሥር የሚገኘው ኹለተኛው የአብነት ትምህርት ቤት አራት ቤቶች ቃጠሎ ተከስቷል። ፓርቲያችን እንዲኽ ያለውን የጭካኔ ተግባር በጽኑ የሚያወግዘው ሲኾን የብልጽግና መንግሥት በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ ማንነትና ሃይማኖት ተኮር የዘር ጭፍጨፋዎች እንዲፈጸሙ ያደርጋል ወይም እንዳላየ ያልፋል በሚል በተደጋጋሚ ስንገልጽ ኖረናል።
ድርጊቱ መፈጸሙ ተገልጾ በይፋ አለመወገዙና የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ስለመደረጉ ምንም ፍንጭ አለመኖሩ ድርጊቶቹ በዓላማ የሚፈጸሙ መኾናቸውን ማሳያ እንደሆነ ፓርቲያችን ያምናል። ታሪክ እንደሚነግረን በዓለም ላይ የሚፈጸሙ ዘር ጭፍጨፋዎች መንግሥታዊ መዋቅርን የተከተሉና በማስተባበያ(denial) የታጀቡ ናቸው።
በዚኹ አጋጣሚ ጭፍጨፋው በአገር ውስጥና ዓለምአቀፍ ገለልተኛ አካላት እንዲጣራ ውጤቱም ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ የድርጊቱ ፈጻሚዎችም ለሕግ እንዲቀርቡ ግፊትና ጥረታችንን እንደምንቀጥል እየገለጽን ለሟቾች እረፍተ ነፍስን ለቤተሰቦቻቸውና እንዲኽ ዓይነቱን ሊቅና ምልክት ላጣው ለመላ የእምነቱ ተከታይ ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን።
እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ