ጥር ፲፰ /18/
በዚችም ዕለት በገድል የተጸመደ የከበረ አባት ለቅዱስ ኤፍሬምም መምህሩ የሆነ የሀገረ ንጽቢን ኤጲስቆጶስ አባ ያዕቆብ(ቅዱስ ያዕቆብ ዘንፅቢን) (ከ፫፲፰ቱ) አረፈ።
ይህም ቅዱስ ተወልዶ ያደገው በንጽቢን ከተማ ነው እርሱ ግን ሶርያዊ ነው። ገና በልጅነቱ በብዙ ተጋድሎ የሚጋደልና ተአምራቶችን የሚያደርግ ሆነ። ትሩፋቱና ደግነቱም በተሰማ ጊዜ መርጠው በሀገር ንጽቢን ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት የክብር ባለቤት የክርስቶስን መንጋዎች ከአርዮሳውያን ተኵላዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ።
ይሕም ቅዱስ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱን የከበሩ አባቶች በኒቅያ ከተማ በሰበሰባቸው ጊዜ ይህ አባት አብሮ አለ ከእርሳቸውም ጋር አርዮስን አውግዞ ከክርስቲያን አንድነት ለየው የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓትና በሁሉ ምእመናን ዘንድ የታወቀች የሃይማኖት ጸሎትን ሠራ።
ንጉሥ ቁስጠንጢኖስም በደረሰ ጊዜ የሞተውን ሰው በጉባኤው ውስጥ አስነሥቷል ። የፋርስ ንጉሥም መጥቶ ሀገረ ንጽቢንን በከበባት ጊዜ ይህ ቅዱስ ያዕቆብ የጭጋግ ደመና በሠራዊቱ ላይ አመጣ ትንኞችም ፈረሶቻቸውንና ጎበዛዝቶችን ነደፏቸው ፈረሶችም ማሠሪያቸውን ቆርጠው ፈረጠጡ የፋርስ ንጉሥም አይቶ ታላቅ ፍርሀትን ፈራ ተነሥቶም ሸሽቶ ወደኋላው ተመለስ ። ነፍሱን የመንጋዎቹንም ነፍስ ጽድልት ብርህት አድርጎ ገድሉን በፈጸመ ጊዜ አረፈ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️