🇪🇹 ክፍል ስድስት 🇪🇹
የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦
አጼ ምኒልክን መጥላት ይወዳሉ፣
ጥላቻ የነብሳችን የመጨረሻው የበሽታ ምልክት ነው፡፡ ጥላቻ ኢምክንያታዊ ነው ወይም አመክንዮ የለውም፡፡ በጥላቻ ላይ የተጻፉ በርካታ ሳይንሳዊ ጽሁፎች እንደሚያመለክቱት በጥላቻ የተመረዙት ምንጊዜም ይጠላሉ ምክንያቱም ይፈራሉ፣ ደህንነት አይሰማቸውም፣ ምቀኞች ናቸው፣ ወይም ደግሞ እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም የጥላቻቸው መነሻ እና መድረሻ እነዚሁ በጥላቻ የተሞሉት ግብዞች ናቸውና፡፡ ከሁሉም በላይ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም ብቁነት የጎደላቸው፣ ኃይልየለሽነት፣ ተስፋቢስነት፣ እና የእረዳትየለሽነት ስሜት የተጠናወታቸው ነው፡፡ ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሰው በቆዳው ቀለም፣ ወይም ደግሞ በማንነቱ፣ ወይም በኃይማኖቱ ምክንያት ብቻ ማንም ማንንም ሊጠላ አልተወለደም፡፡ ሰዎች መጥላትን መማር አለባቸው፣“ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉትን የገዥው አካል ኃላፊዎች ሁኔታ በማስብበት ጊዜ በማንዴላ ፍልስፍናዊ ግምገማ ላይ አምነት ማጣት ይቃጣኛል፡፡ ማንዴላ እንዲህ በማለትም አክለዋል፣ “መጥላትን የሚማሩ ከሆነ ፍቅርን ሊማሩም ይችላሉ፣ ምክንያቱም ፍቅር ከተቃራኒው የበለጠ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ የመስረጽ ተፈጥሯዊ ባህሪ አለውና፡፡“ ተቃራኒውን በተጨባጭ የሚያመላክቱ በርካታ መረጃዎች ቢኖሩም የማንዴላ መርሆዎች በስልጣን ላይ ባሉት ባለስልጣኖች ሁሉ ሊተገበሩ እንደሚችሉ ጽኑ እምነት አለኝ፡፡
በመርህ እና በተግባርም እንደሚታየው በጋንዲ መርሆዎች መሰረት ለመኖር ጥረት ማድረግ አለብን፣ “ኃጢያተኛውን ሳይሆን ኃጢያቱን እንጥላ፣“ በጥላቻ የተመረዙትን የምንጠላ ከሆነ የእነርሱ የመስታወት ነጸብራቅ እንሆናለን፣ እራሳችንም የምንጠላቸውን እንሆናለን፣ እንደ ሰው ስብዕና አቶ መለስን እና መሰሎቻቸውን የምንጠላ ከሆነ እነርሱኑ ሆን ማለት ነው፡፡ የምንጠላ ከሆነ ምግባራቸውን እንጅ እንደ ሰው እራሳቸውን መሆን የለበትም፡፡
ጥላቻ ጠንካራ ኃይል ነው፡፡ በናዚዝስቶች የተሰራጨው ጥላቻ አገሮችን በጠቅላላ እንዲጠፉ አድርጓል፡፡ በሩዋንዳ የተከሰተው ጥላቻ የሚሊዮኖችን ሩዋንዳውያን ህይወት ቀጥፏል፡፡ በዳርፉር የተቆሰቆሰው ጥላቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሱዳን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተከሰተው የኃይማኖት ጥላቻ በናይጄሪያ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመሞት ላይ ይገኛሉ፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ ወደ ጥላቻ መግባት የለብንም፡፡
በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ህዝቦች እንዳሉ አምናለሁ፡፡ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ“ የሚለውን ወርቃማ ህግ የሚከተሉ ህዝቦች አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ “የመዳብ ህግ” እያልኩ በምጠራው “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ጥላ“ እያሉ የሚኖሩ ህዝቦች አሉ፡፡ በጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የእራሳቸውን እረዳትየለሽነት፣ የደህንነት እጦት ስሜት፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና በጥላቻቸው መሳሪያነት ድርጊቶችን በመለወጥ አሸናፊነትን የሚጎናጸፉ ይመስላቸዋል፡፡ ሌሎችን በመጥላት የራሳቸውን የበታችነት ስሜት እና የእራስን ዋጋ ዝቅ አድርጎ የማየት ችግራቸውን በማስወገድ እራሳቸውን ከፍ ያደረጉ ይመስላቸዋል፡፡ አጼ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች በእርግጥ አይጠሏቸውም፣ እራሳቸውን የሚጠሉ እና ምኒልክን ለመሆን የሚያስቡ ምኒልክ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ሁሉ ተምሳሌት ለማድረግ የሚጥሩ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት ሁሉ አዝንላቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ በጣም አዝንላቸዋለሁ፡፡ እነዚህ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች የኢትዮጵያን ታላላቅ መሪዎች እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት በመቀባት በቅርቡ በህይወት የተለዩትን መሪያቸውን እና የሁለት አስርት ዓመታት ኃጢያታቸውን በማስሰረይ ብጹ የሚያደርጓቸው ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን እና የቀዳማዊ ኃይለስላሴን በጎ ተግባራት ጥላሸት በመቀባት የአቶ መለስን ስብዕና የሚገነቡ ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን ሐውልት ከህዝባዊ ቦታዎች በማራቅ እና የአቶ መለስን እርካሽ ወረቀት ፎቶግራፎች በየመንገዶች ላይ በመለጠፍ አቶ መለስን ወደ መልዓክነት ያቀረቧቸው ይመስላቸዋል፡፡ አቶ መለስ የአጼ ኃይለስላሴ ሀውልት ከንክሩማህ ቀጥሎ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳይቆም ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል፡፡ ሆኖም ግን ንክሩማህ እራሳቸው የአጼ ኃይለስላሴ ያልተጠቆጠበ ጥረት ባይኖር ኖሮ የአፍሪካ ድርጅት እውን መሆን አይችልም ነበር በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉ.....
~ ይቀጥላል ~
ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም
❣ እናመሠግናለን ❣