"A man without principles is as a ship without a rudder — at the mercy of every wind and wave." ~ Christopher CHARLES
___
ሰው ቀለም አለው፤ ቀለሙ ጠይም፣ ጥቁር ወይም ነጭ አይደለም፤ የሰው ቀለም የስብዕና አሻራ ነው፣ ስብዕናም የሚቆምበት መሰረት አለው - መርህ!!
መኖር ቀለም አለው፣ ቀለሙ ማግኘትና ማጣት፣ ድህነት ወይም ሀብታምነት አይደለም፤ የኑሮ ቀለም የአስተሳሰብ ቅኝት መታያ ነው፣ አስተሳሰብም የክት መገለጫ አለው - መርህ!!
ብስለት ቀለም አለው፣ ቀለሙ ክሂለ-ነቢብ አይደለም፣ የስልጣን ከፍታ አይደለም፤ በከፈን መጊያጊያጥ፣ በዕውቀት መበላለጥ፣ በዕድሜ ብዛት ማጌጥ አይደለም፤ ብስለት የአስተውሎት ልኬት ነው፣ አስተውሎት ማንጸሪያ መልክ አለው - መርህ!!
__
የኑረት ብሉይ መስፈሪያ ሆኖ - የኖረ ሁሉ ወዳለመኖር ይመጣል፣ ቅርፃዊው ማንነት ወደ ፍራሽ፣ ፍራሽ ወደ ብስባሽ ይለወጣል... በውልደት እና ሞት መሃል በተዳሳሽ ማንነት የቆመው የሕይወት መልክ ጨርሶ እንዳይጠፋ የሚያደርገው የአኗኗር ቀለም ነው...
ቀለም በመኖር ብቻ አይከሰትም - የተወለደ ሁሉ ይኖራልና፤ ቀለም ለመኖር በወሰኑ ኗሪዎች ጥረት ነው የሚገለጠው - እንደሚገባ ለመኖር በቆረጡ ጀግኖች... እንደሚገባው ለመኖር የሚያስፈልገው ቀለም ደግሞ መርህ ነው!!
መርህ - ኑረት ከነሙሉ ክብሯ የምትገለጥበት የስብዕና ቀለም ነው፤ የእያንዳንዳችንን ልክና ደረጃ የሚያበጅ፣ መገለጫችንን የሚያደረጅ፣ ጎራችንን የሚፈርጅ... እንደ ሰው ስንኖርም ሆነ ጊዜ ደርሶ ስናልፍ ለህላዌ ትርጉም የሚሰጥልን ኃይል ነው - መርሕ!!
ስትኖር እንዴት ኖርክ ነው ጥያቄው... ንፋስ እንደሚያንከላውሳት ጀልባ ከአለት ከተራራው ስትላተም?... ከደረሰችበት ማረፊያ ሁሉ ጋር እንደምትለዋወጠዋ እስስት ለመኖር ስትመሳሰል?... በሌሎች ሃሳብና ፍላጎት ስርቻ ውስጥ ሞራልህን ድጠህ ስትርመጠመጥ?... ወይስ በራስህ ምሕዋር ውስጥ ቀለምህን ለማጽናት - በመትጋት?...
ሕይወትን፣ ኑረትን፣ ሰዋዊ ግንኙነትን፣ ሰርቶ ማግኘትን፣ ደስታን፣ ሃገርን፣ ቤተሰብን... ወዘተ የምትረዳበት መንገድ የኑረት መርሕ የምትቀርጽበት መሳሪያ ነው...
ሃገርን ሊታፈስ እንደተዘጋጀ የሰፌድ ላይ ቆሎ የሚመለከታት ሰው መርሁ መዝረፍ ነው፣ ሕይወትን እንደ ትርጉም አልባ ክስተት የሚገነዘባት ሰው አኗኗር ሰውነትን መበደል ነው፣ የኑረት ግቡ ጥቅም ማግኘት ብቻ የሆነ ሰው መርሁ 'ተመሳስሎ ማደር' ነው...
___
በምንም ጉዳይ ላይ አቋም የማይዝ፣ የራሱ standard የሌለው፣ ከመጣ ከሄደው ሁሉ ጋር የሚዋዥቅ፣ 'ሲጠሩት አቤት - ሲልኩት ወዴት' ከማለት የማይዘል፣ 'ለምን?' ያልፈጠረበት፣ የእይታ መስፈሪያ _ የእምነት ልኬት _ የሞራል ጥግ የሌለው ሰው መርህ አልባ ነው...
“The unexamined life is not worth living.” ~ Socrates
ሰው የጫኑትን ሁሉ የሚቀበል አህያ አይደለም፣ ባሰለቱለት ቦይ ሁሉ የሚፈስ ጎርፍ አይደለም፤ ያጎረሱትን ሁሉ የሚውጥ ጉድጓድ አይደለም፤ የነገሩትን ልክነት ይመረምራል፣ የሰበኩትን እውነትነት ይጠይቃል፣ 'ለምንታ' አለው፤ 'እንዴታ' አለው፤ 'ወዴታ' አለው፤ ማጥለያ አለው፤ ወንፊት አለው...
መርህ ከመንጋ ጋጋታ ይነጥላል... ከግርግር ሆታ፣ ከአጨብጫቢ ኳኳታ ያርቃል... ከሩጫ ተናጥቦ ማሰላሰል፣ ከልብ ጋር መምከር - ከእውነት ጋር ማመሳከር ይሻል... ብዙሃን ስለተቀበሉት ሳይሆን ከልብ ስለተስማማለት መቀበልን ይመርጣል... ያሰክናል!!
መርህ ድፍረት ይጠይቃል፣ መነጠልን የማስተናገድ ድፍረት... ፈሪዎች መርህ የላቸውም!! መርህ ትከሻ ይፈልጋል፣ ከጠባቂነት ነፃ የሚያወጣ ትከሻ... በራሳቸው የማይተማመኑ ሰዎች መርህ የላቸውም...
"It takes backbone to stand up for your principles and values. It’s what you do when no one is looking." ~ Bill Bolde
___
ሰውን ከመርሕ የሚያፋታው ሁለት ነገር ነው፦ የማግኘት ረሃብና የማጣት ስጋት!!...
ጥቅም የነገሮቻችን ሁሉ ማጠንጠኛ በሆነበት በዚህ ዘመን ለማግኘት ሲባል ለጆሮ የሚከብደው፣ ለልቡና የሚጨንቀው ሁሉ ይሆናል... በማግኘት ላይ የተመሰጡ ሰዎች አስቀድመው ጥግ የሚያስይዙት ሞጋች ህሊናቸውን ስለሆነ ምንም ዓይነት ተግባር ሲፈጽሙ የልክነትና ስህተት ሚዛን አይጠቀሙም፣ ጨካኝ ናቸው...
"A man without principles is commonly a man without character." ~ William Seward
ጉድለት ብቻ የሚመለከት፣ በረከቱን የማይቆጥር፣ ከሌሎች በመወዳደር ትግል ውስጥ ያለ፣ ሕይወትን ከቁሳዊ ኮተት አሻግሮ የማይመለከታት ሰው ስግብግብ ነው...
ሰው የሚበድለው ለማግኘት ብቻ አይደለም - ያገኘውን ላለማጣት ሲልም ይከፋል... ማግኘቱ ውስጥ ተገቢነት ስለሌለ እንዳላጣው ብሎ ይከረፋል... ጠላት ፈጠር ስለሆነ እንቅልፍ የለውም - ሴራ መጎንጎን ሃብቱ ነውና እረፍት አያውቀውም...
መርህ የሌለው ሰው ከመጨመር ሌላ ሃሳብ፣ ካለማጣት በላይ ጉዳይ ስለሌለው ይህን ያሳካልኛል በሚለው ሁኔታ ውስጥ ድንገት ለመታጠፍ ችግር የለበትም!!
በዕውቀቱ ስዩም አንዲት የግጥም ዘለላው ላይ ያኖራት ጥልቅ ሃሳብ ላነሳነው ጉዳይ እንደ ማሕተም ናት፦
--- ይድረስ ላድር ባይ ጓዴ
"እየለየ ጊዜ - ቦታ እየመረጠ
እስስታማ መልክህ - ገጽህ ተለወጠ
አህያ እንዳልነበርክ - በሰርዶዎች መሃል
አህዮች ሲበዙ - ዛሬ ጅብ ሆነሃል"
___
@