የጃፓኑ ኩባንያ የሰው ማጠቢያ ማሽን ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን አስታወቀ
በኦሳካ ከተማ ላይ መቀመጫዉን ያደረገዉ የሻወር ቤት አምራች ሳይንስ ኩባንያ ሚራይ ኒንገን ሴንታኩኪ ወይም የወደፊቱ የሰው ልጅ ማጠቢያ ማሽን የሚል ስያሜ ማጠቢያ ማሽን መስራቱን አስታዉቋል፡፡
የጃፓኑ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሳንዮ ኤሌክትሪክ ኩባንያ አሁን ላይ ፓናሶኒክ ሆልዲንግስ ኮርፖሬሽን የሚባለዉ በዓለም የመጀመሪያው የሆነውን የሰው ማጠቢያ ማሽንን እ.ኤ.አ በ1970 ይፋ አድርጓል፡፡ ማሽኑ የእንቁላል ቅርፅ ያለዉ እና የአረፋ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ሲሆን የሰዎችን ትኩረት የሳበ እና በኤክስፓ ወደ አምራቹ ዳስ በርካቶች ገብተዉ እንዲመለከቱ ከዓመታት በፊት አስገድዷል። ያሱዋኪ አዮያማ የሳንዮ ማጠቢያ ማሽንን በተግባር ካዩት ከበርካታ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። በጊዜው የማወቅ ጉጉት ያለው የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነበር፣ ነገር ግን የፍርሃት ስሜቱ በጉልምስና ዕድሜው ሁሉ ከእሱ ጋር መቀጠሉን ያነሳል፡፡
ዛሬ ላይ የሳይንስ ኩባንያ ሊቀመንበር ሆኖ በመታጠቢያ ገንዳዎች ላይ የተካነ ኩባንያ የሚመራ እንደመሆኑ የራሱን የሰዉ ማጠቢያ ማሽን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነው። አዲስ የሰው ማጠቢያ ማሽን ከ1970 ኤክስፖው በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እናቀርባለን ሲል አዮማ በቅርቡ ለጃፓን ዘጋቢዎች ተናግሯል፡፡የተሻሻለው ሞዴል በኤፕሪል 2025 በኦሳካ ካንሳይ ኤክስፖ ላይ እንደሚታይ ይጠበቃል።የቀደሞ የሰው ማጠቢያ ማሽን በትላልቅ የአየር አረፋዎች የተፈጠሩ አልትራሳውንድዎችን ተጠቅሞ የአገልግሎት ፈላጊዉን ደንበኛ ለማጽዳት እና የፕላስቲክ ኳሶችን ለመልቀቅ እና ለማሻሸት ይጠቅሟል።
አዲሱ የሰው ማጠቢያ ማሽን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ ሲሆን ሰውነትን ለማፅዳት በጣም ውጤታማ የሆኑ ጥቃቅን የአየር አረፋዎችን እንዲሁም የተጠቃሚዉን የልብ ምት እና ሌሎችን የሰዉነት ክፍሎችን የሚለኩ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ይጠቀማል። ውሃውን በትክክል ለማሞቅ ባዮሎጂካል መረጃ ፣ እና ተጠቃሚው የተረጋጋ ወይም ደስተኛ መሆኑን የሚወስን የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ወይም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኤአይ ስርዓት ይተገበራል፡፡ በልብ ማጠቢያ ማሽን መልክ ተሰርቶ መቅረቡንም ኩባንያዉ አክሎ ገልጿል፡፡
ያሱዋኪ አያማ እንደተናገሩት ኩባንያው በሚቀጥለው ዓመት በኦሳካ ኤክስፖ እስከ 1,000 ሰዎች የፈጠራውን የልብስ ማጠቢያ ማሽን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ተስፋ አድርጓል ብለዋል።ሳይንስ ኩባንያ በሰው ማጠቢያ ማሽን ላይ ለተወሰኑ ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። የዋናው ፕሮቶታይፕ ንድፍ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀይሯል ፣ ኩባንያው በ2025 የመጀመሪያ ስራዉን ለገበያ ያቀርባል፡፡