ኤች አይ ቪ አሁንም የህልውና አደጋ ነው!
በአሁኑ ወቅት የኤች አይ ቪ ጉዳይ ብዙም ሲወራ ስለማንሰማ ብዙዎቻችን ከእነ አካቴው የጠፋ ሊመስለን ይችላል፡፡ እውነቱ ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡ ኤች አይ ቪ ዛሬም የህልውና አደጋ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ኤች አይ ቪ በደማቸው እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ይህን ያስታወቀው “ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤችአይቪ አገልግሎት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል የዓለም ኤድስ ቀን ትላንት በአድዋ ድል መታሰቢያ በተከበረበት ወቅት ነው፡፡
በሃገራችን ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ኤች አይ ቪ በደማቸው እንደሚገኝ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፤ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች በዓመት ውስጥ በኤች አይ ቪ እንደተያዙና ከ10 ሺህ በላይ ዜጎች ህይወታቸውን በኤድስ ምክንያት እንዳጡ ተናግረዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚጠቁመው፣ እ.ኤ.አ በ2023 ዓ.ም ማብቂያ ላይ በመላው ዓለም ከ630ሺ በላይ ሰዎች ከኤች አይ ቪ ጋር በተገናኙ ምክንያቶች የሞቱ ሲሆን፤ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በኤች አይ ቪ ተይዘዋል፡፡ ከኤች አይ ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 39.9 ሚሊዮን መሆኑ ታውቋል፡፡
እናም ጎበዝ ኤች አይ ቪ አሁንም የህልውና አደጋ መሆኑን አንርሳ ለማለት ያህል ነው፡፡ ጠንቀቅ ማለቱ ያዋጣል!!