እ ብ ደ ት
┈•✦•┈
እብደት ከሁሉ የባሰ ትልቅ በሽታ ነው። ከሁሉም የባሰ የሚያደርገው ሰው የሚከበርበትን አእምሮውን ስለሚያበላሸውና እንደ እንስሳ ስለሚያደርገው ነው። ለዚሁም ታሪካዊ ምሳሌ ልስጣችሁ።
ካሊጎላ የተባለው አንዱ የሮማ ንጉሥ አስቀድሞ አእምሮው የተካከለ ደህና ሰው ነበር። ኋላ ግን አእምሮው ወደ ክፋትና ወደ ጭካኔ ተለውጦ የሚሰራው ሥራ ሁሉ የእብደት ሥራ ሆነ።
ከዕለታት አንድ ቀን ከሁለት አማካሪዎቹ ጋራ በምክር ቤት ውስጥ ተቀምጦ ሳለ ልዩ ልዩ የመንግሥት ጉዳዮች ሲመካከሩ ንጉሡ ከት ብሎ ልቡ እስኪፈርስ ድረስ ሣቀ። ቁም ነገር በሆነው ይነጋገሩበት በነበረው ጉዳይ ውስጥ ምንም የሚያስቅ ነገር ስላልነበረበት ሁለቱ አማካሪዎች ገርሟቸው
«ንጉሥ ሆይ ምን የሚያስቅ ነገር አገኙ?» ብለው ጠየቁት። ካሊጎላም
«አሁን እኔ ቢያሰኘኝ በእኩል (በግማሽ) ሰዓት ውስጥ ሁለታችሁንም ለማስገደል የሚቻለኝ መሆኔን ሳስበው በጣም ያስቀኛል።» ብሎ መለሰላቸው።
ይህ ወደፊት ጨርሶ ለማበዱ ዋዜማው ሆነ። ከዚያም በኋላ ያለ ፍርድ የብዙ ሰዎችን ንፁህ ደም በከንቱ አፈሰሰ። ከጭካኔውም ብዛት የተነሳ
«ባንድ ጊዜ በሰይፍ ቆርጬ ለመጣል እንዲመቸኝ ምነው የሮማውያን ሕዝብ አንገታቸውና ራሳቸው የሁሉም አንድ ብቻ በሆነ ኖሮ» እያለ በገሀድ ይናገር ነበር ይባላል። ... ብዙ ሰዎች የካሊጎላን ጭካኔ በእብደት ተርጉመውታል።