የምንሞትበትን ቀን የሚተነብየው አወዛጋቢ መተግበሪያ - "የሞት ስአት"
በሀምሌ ወር የተዋወቀው ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚጠቀም መተግበሪያ በአጭር ጊዜ በርካታ ደንበኞች ማፍራቱ ተገልጿል
አል-ዐይን
"የሞት ስአት" የህይወት ዘይቤ፣ አመጋገብ፣ የቤተሰብ ታሪክና ሌሎች መጠይቆች ላይ ተመስርቶ ነው ትንበያውን የሚያደርገው
ሁሌም እንደሚሞቱ እያሰቡ መኖር ህይወት ይበልጥ ትርጉም እንዲኖራት ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።
ብዙዎቻችን ይህቺን ምድር በሞት መለየታችን እንደማይቀር ብናውቅም ነፍሳችን ከስጋችን የምትለይበትን ትክክለኛዋን ቀን ማወቅ ምን ያህል ከባድ ጭንቀት ውስጥ ሊከተን እንደሚችል በማሰብ በተስፋ መኖርን እንመርጣለን።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) እየተስፋፋ መሄድ ግን የሰው ልጆችን የመሞቻ ቀን የሚተነብዩ መተግበሪያዎች በብዛት እንዲቀርቡ እያደረገ ነው።
በሀምሌ ወር የተዋወቀውና ለመሞት ምን ያህል ቀን፣ ስአት እና ደቂቃ እንደቀረን ይተነብያል የተባለው "ዴዝ ክሎክ" ወይም የሞት ስአት የሚሰጠው ትንበያ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።
የቴክኖሎጂ መረጃዎችን የሚያቀርበው "ቴክክራንች" ድረገጽ ዘጋቢው አንቶኒ ሃ በቅርቡ መተግበሪያውን አውርዶ መች እንደሚሞት ሲጠይቀው "በ90 አመትህ፤ የህይወት ዘይቤህን ካስተካከልክ ደግሞ እስከ 103 አመት ትቆያለህ" የሚል ምላሽ ሰጥቶት እንዳስደነቀው ተናግሯል።
አንድ የመተግበሪያው ተጠቃሚ ደግሞ "መተግበሪያው የመሞቻዬን ቀን ከነገረኝ በኋላ በዝግታ እየሞትኩ እንደሆነ ይሰማኛል፤ ዴዝ ክሎክ ህይወቴን እና ካሎሪየን እያወረደው ነው" ሲሉ በኤክስ ገጻቸው አስተያየታቸውን አጋርተዋል።
መተግበሪያው ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚጠቀም ነውና እንደ ህክምና ባለሙያ አስተዛዝኖ ሊነግር ወይም እድሜን ሊጨምር አይችልም የሚሉ ባለሙያዎችም ዝግጁ ያልሆኑ ሰዎች ባይጠቀሙት ይመክራሉ።
"ዴዝ ክሎክ" ፈጣሪ ብሬንት ፍራንሶን ግን መተግበሪያው ሰዎችን የሚሞቱበትን ቀን በመናገር የማስደንገጥ ወይም እድሜያቸው ከፍ የሚልላቸውን ሰዎች የማስደሰት አላማ እንደሌለው ይናገራል።
"የጤና ሁኔታችሁን በዝርዝር ይነግራችኋል፤ ምክሮችንም ይለግሳል" ነው ያሉት ከዴይሊሜል ጋር ባደረጉት ቆይታል።
ለአመታዊ አገልግሎት 40 ዶላር የሚያስከፍለው መተግበሪያው 53 ሚሊየን ሰዎች የተሳተፉባቸውን ከ1 ሺህ 200 በላይ ከእድሜ ጋር የተያያዙ ጥናቶች መሰረት በማድረግ ነው ትንበያውን የሚያስቀምጠው።
ተጠቃሚዎች ከአፕስቶር መተግበሪያውን እንዳወረዱ እድሜ፣ ጾታ፣ የዘር ሀረግ፣ የቤተሰብ ታሪክ፣ አመጋገብ፣ የህይወት ዘይቤና ሌሎች ግላዊ መረጃቸውን የሚሙሉበት መጠይቅ ይቀርብላቸዋል።
የበሽታ ተጋላጭነት፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ ልምድ፣ የእንቅልፍ ስአት ርዝማኔ እና ሌሎች ጥያቄዎችም "ትክክለኛ የመሞቻ ጊዜን ለመተንበይ" ወሳኝ ናቸው ብሏል።
"ዴዝ ክሎክ" በትንበያው ውጤታማነት ዙሪያ አሁንም ድረስ ትችቶች ቢበዙበትም ከ125 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች ማፍራት መቻሉ ተገልጿል።