ከአንድ መንደር በላይ ካለ ተራራ ላይ እንዲት እንስት ንስር ጎጆዋን ቀልሳ እንቁላል ጥላለች። አንድ ቀን ታድያ አከባቢውን ከባድ የምድር መናወጥ ይንጠውና ከእንቁላሎቹ አንዱ በተራራው ቁልቁል ተንከባሎ እግርጌው ካለ የዶሮ እርሻ ውስጥ ይወድቃል።
ዶሮዎቹም ከራሳቸው እንቁላሎች እንደአንዱ ስላሰቡት እንቁላሎቻቸው ጋር ቀላቅለው ታቅፈውት ይሰነብታሉ። ጊዜውም ሲደርስ እንቁላሉ ይፈለፈል እና በጣም የተዋበ ንስር ይሆናል።
ዶሮዎቹ ከዶሮነት ሌላ ስለማያውቁ ንስሩን እንደ ዶሮ አድርገው ያሳድጉታል።
ንስሩ ቤቱን እና ቤተሰቡን ቢወድም ውስጡ ግን ከለመደው ነገር የሚበልጥ አቅም እንዳለው ይነግረው ነበር።
አንድ ቀን ከዶሮዎቹ መካከል ሆኖ ጥሬ እየለቀመ ሳለ ድንገት ወደላይ ቀና ሲል ታላላቅ ንስሮች አየሩን እየቀዘፉ ሲበሩ ያያል። ሳያስበውም ድምፁን አውጥቶ "አቤት ምናለ እኔም እንደነዚህ ንስሮች መብረር ብችል" ይላል።
ይህንን የሰሙት ዶሮዎች ሳቃቸውን መቆጣጠር እቅቷቸው፣ "ዶሮ መሆንህን ረሳኸው እንዴ? ዶሮ ከመቼ ወዲህ ነው የሚበረው?" እያሉ በተረብ አዋከቡት።
ንስሩ ግን ዘወትር በአይኑ እውነተኛ ቤተሰቡን መፈለጉን አላቆመም። አንዳንዴ እንዳውም እንደመንጠራራት እያለ ክንፎቹንም ይፈትን ነበር።
ነገር ግን ወደላይ ባንጋጠጠና ክንፎቹን ባራገበ ቁጥር ዶሮዎቹ የሚያወርዱበት ተረብ እየበዛበት ሲመጣ ዶሮ መሆኑን የበለጠ እያመነ መጣ። ከጊዜ በኋላም የመብረር ህልሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ እንደ ዶሮ ኖሮ ጊዜው ሲደርስ እንደዶሮ ሞተ።
------------------------------
የሰው ልጅ ሁሉ #ገደብ_የለሽ የሆነ- ፈጣሪ ሁሉንም ነገር መሥራት የሚችል ፍጡር አድርጎ የፈጠረው ሆኖ ሳለ ይህንን ኃይሉን ካጣበት ምክንያት አንዱ ልክ እንደ ንሥሩ ከአትችልም፣ አይሆንም፣ ትወድቃለህ፣ ... ወዘተ ከሚል ወይም ይህንን ካላስተማረ ማህበረሰብ ውስጥ ማደጉ ነው።
ይህ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው የልጅ አስተዳደግ ዘይቤያችን አስተሳሰባችን ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህም ባህርያችንን ይቀርጻል።
ይህንን የበለጠ ለመረዳት እስከሆነ እድሜ ድረስ የነበረውን ልጅነታችንን አስቡ።
በጣም ነጻ፣ ደስተኞች፣ ደፋሮች፣ ጥሩዎችና ሁሉን ማድረግ የምንችል አይነት ስሜት የሚሰማን ነበርን። ነገር ግን እያደግን ስንመጣና የማህበረሰብ ሕጎችን እየተማርን ስንመጣ ፈሪዎች፣ ተጠራጣሪዎች፣ ንፉጎች፣ የተገደብን እና ነገሮችን እንደፈለግን ማድረግ የማንችል አይነት ስሜት እየተሰማን ይመጣል።
በእርግጥ አዕምሯችንና ሰውነታችን አደጋን በማስወገድ ሥራ ላይ የበለጠ ያመዝናል። በአብዛኛው ራስን ከአደጋ ለመከላከልና ውስብስብ ሥራዎችን በማስወገድ ሥራ ላይ ስለሚጠመድ 'ሪስክ' ለመውሰድ ችላ እንድንል ያደርገናል። ይህም የሆነበት ምክንያት አዕምሯችን እኛን ለመጠበቅ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው።
ይህ ከአስተዳደግ ጋር ተደማምሮ አዳዲስ ነገሮችን እንዳንሞክር፣ የውስጥ ተሰጥዖዎቻችንን በሚገባ እንዳናወጣ፣ ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን የተሻለ እንዳንሰራ እንቅፋት ይሆናል።
ሆኖም ግን ይህንን ሰብረው የወጡ ሰዎች ስኬታማ ሆነው እናገኛቸዋለን።
ስለሆነም ይህንን ለማስወገድና የተሻለ ውጤት ለማምጣት አዋዋልን ማሳመር፤ ራስን ለለውጥ ማዘጋጀት፤ የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን እና መፃሕፍትን ማንበብ፤ የተሻሉ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች ጋር ማዘውተር፤ እንዲሁም ራስንና አካባቢን ማወቅና መረዳት ያስፈልጋል።
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------