ውድ ቤተሰቦቼ የእግዚአብሔር ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን እንዴት ናችሁ? ወርኃ ጽጌ እንዴት ነው? ያው ዛሬም እንደተለመደው በቡሬ ወረዳ የሚገኘው የሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አሁንም ብዙ ችግሮችን እያሳለፈ ይገኛል። በዚህ ወቅት ግን በዋናነት በመብራት ችግር እየተፈተነ ነው። ይህንን ችግር ለማስተካከል ደግሞ ሶላር መግዛት ይኖርባቸዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ አቅሙ የላቸውም። እኔ እና እናንተ ከተባበርን ግን የሚፈልጉትን ማድረግ እንችላለን። የበረከት ጥሪያቸውን ለሚቀበል እግዚአብሔር ይርዳው።