ወንድሜ ምን ማለት እንኳን እንዳለብኝ በቅጡ አላውቅም። ብቻ ግን ልቤ ተሰብሯል። በእውነት እኔ አላመንኩም። በቅርብ እኮ እያወራኸኝ ነበር። #ልጥገብ የልጅ አዋቂ ነበርክ። መካሪ ነበርክ። እንባዬን ለጊዜው ላቆየው! ለመላው ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ እንዲሁም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ መጽናናትን እመኛለሁ። Black_Friday! 😰😥😢😭😭😭😭
~ እንጉርጉሮ ~ 😭😢😢😥😥😥
ምነው ታይተህ ጠፋህ አይተን ሳንጨርስህ ፣
ምነው በቅለህ ደረቅህ ሳንበላ ከእሸትህ ፣
ምነው ወጥተህ ቀረህ ሥራህን አቋርጠህ ።
😢😢😢
እኔማ ደስ ብሎኝ ሥራ ስትጀምር ፣
እሰይ ዳነ ብዬ ምሥራች ሳበስር ፣
ወንድሜ ተሻለው ብዬ ለሰው ስነግ-ር ፣
አንተ ግን ኮበለልክ መኖር ጠላህ ምድር ።
በቃ ልጥገበው ወይ አንተን ማወቅ አልነበረብኝም። ወይ ደግሞ እኔ እንጃ! ወንድሜ ነፍስህን በአጸደ ገነት ያሳርፋት ዘንድ ጸሎቴ ነው። 😥😭😭😢😢😢😰😰😰