ቅመም 🧄🌶️
ፀሃዩ የዘላለም ይመስላል።ደመናውም ቢሆን ማንም የሌለበት።ወረቀት !በስፋቱ ልክ መታጠፉ የት ይቀራል።መንገዱ ለራሱ አላፊ ፅኑ መስሎ በደረቱ ስንቱን ያራምዳል።ሰው ከስራ መመለሱ ነው።ሁሉም ጠዋት ከሸከፋት ቦርሳው ጋር ወደየቀዬው ያመራል።
አቤት መኮሳተር አንዳች ታላቅ ውድ ምስጢር በግምባሩ የያዘ ይመስል ከቋጠረበት አይፈታውም....ሰዉ......።ወደ ፂሆን የሚሮጥ ይመስላል አብዛኛው ግን ወደ ሲኦል።ቆይ እኔን ማንፈራጅ አረገኝ?በቃ ባለቤቱ መጣው ብሎ ቢሄድ መሬት ላይ ዘለልንባት አይደል? ባየን ፣በተያየን ፤ጉዱን ባበራበት ፤እንቅብ ስር እንደተገኘ በረሮ መግቢያ ነበር ምናጣው።
ከካደው እጀታ ትውልድ ዝንጋት ተቀበለ ከቸልተኞ ጓዳ አለማወቅን የጠገበ ትውልድ ተነሳ ውዝግቡ መለስ ሲል ደግሞ ሁሉም በየፊናው መዳንን ይፈለፍል ያዘ ።እንደራሱ ጥበብ በደመነፍስ ሚዛን እየለካ ፈርጅ ያዘ ፍትህ ሚሉት መለኪያ ለሁሉም እርሻ ሰጣቸው እና በለፀጉ ።በአይን ሳይሆን በልብ ይቀመሱ ጀመር።ሁሉም ይመሳሰላሉ ግን በቅመም አገባብ ተለያይተዋል።