ለምንድነው መኖር የደከመህ??
ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ?
ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም
ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ?
አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ
ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም
ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው
በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም
ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ፡
☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ
ታስፈልገናለህ፡፡
ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ
ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን
ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡
እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡
አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ
ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው
ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡፡ በህይወትህ
ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል
መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ
መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ
መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው
ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን
አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት
አትቸኩል ኢኼ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት ሞክር ማለት ነው፡፡
ታሪክህን ፃፍ እናንብህ፡፡
መልካም ኑሮ
@quoteseverr