Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ኢብራሂም– አንድ ሰው፣ ሁለት ስም!
~
አንተ ከሰዎች ዘንድ ማነህ? ደግ ወይስ ክፉ? ትሁት ወይስ በጥራራ? ፊተ በሻሻ ወይስ ጨፍጋጋ? ምራቅ የዋጠ በሳል ወይስ በቀዳዳ ሱሪ የሚጀነን ከንቱ ፍንዳታ? አንተ ማነህ? ሰዎች ስላንተ ምን ይላሉ? ምን እንደሚሉ ታውቃለህ? በክፉ መነሳት ያሳስብሀል? ወይስ የሰው ጉዳይ የማይጨንቅህ በራስህ ዛቢያ ላይ የምትሽከረከር ፍጡር ነህ?
አንቺስ ከሰው ዘንድ ማነሽ? ማን መባል ያምርሻል? ምን ስም እንዳይወጣልሽ ይጨንቅሻል? ባገር በመንደሩ ምን ስም አለሽ? ጨዋ? ዘል.ዛላ? ምላሳም? ቁጥብ? አጉል ነቃሁ ባይ? ግብረ ገብ? ቀብራራ? ኮስታራ?
ይህ ከሰው ዘንድ ነው። ከአላህ ዘንድስ እኛ ማነን? ምንስ ቦታ አለን? እስኪ ራሳችንን እንመልከት? አላህ ካዘዘብን ቦታ አለን? አላህ ከከለከለን ቦታ ርቀናል? ከሆነ ምንኛ መታደል ነው?! ከሆነ ከሰው ዘንድ ያለን ስም አያስጨንቀንም።
ከሰዎች ዘንድ እፍኝ የማይሞሉ፣ አይን የማይገቡ፣ ቢናገሩ ቃላቸው የማይሰማ፣ ቢጠይቁ ፊት የማይስሰጣቸው፣ በሰዎች መለኪያ እዚህ ግባ የማይባሉ ከአላህ ዘንድ ግን የላቀ የራቀ ደረጃ ያላቸው ስንትና ስንት የአላህ ሰዎች አሉ?! አላህ ዘንድ "ሰው" ከሆኑ በኋላ ሰዎች እንደ ሰው ባይቆጥሯቸው ምን ያጣሉ?! ኢብራሂምን አታይም? ከነዚያ ከበርቴዎች ዘንድ ማን ነበሩ? አንድ ተራ ወጣት!
(قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ)
"ኢብራሂም የሚባል #ወጣት (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል ተባባሉ።" [አልአንቢያእ: 60]
ከአላህ ዘንድስ ማን ነበሩ?
(إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ)
"ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ የሆነ #ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡፡" [አንነሕል: 120]
ከሰዎች ዘንድ እንደ ዋዛ "አንድ ወጣት" ተብለው የተቃለሉት ኢብራሂም ከአላህ ዘንድ "ህዝብ" ተብለው ነበር የተሞካሹት!! አንዱ ኢብራሂም ሁለት ስም ሲኖራቸው ተመልከት። አንዱ እንደ ምድር፣ አንዱ እንደ ሰማይ። አንዱ ከምድር፣ ሌላው ከሰማይ። ልዩነቱን አየኸው?! አላህ እንዲህ ከሰቀላቸው በኋላ ፍጡር ሊያወርዷቸው ቢጣጣር ምን ያመጣል?! በተውሒድ የነገሰን ማን ያወርደዋል?!
·
ድሮ ነው። ወሎ፣ ወረባቦ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ዑካሻ የተሰኙ በተውሒድ ጠንካራ የሆኑ፣ ህዝቡን የወረረውን ሺርካ ሺርክ የሚነቅፉና የሚፀየፉ ሸይኽ ነበሩ። "ከዘልማዳችን ወጥጣ" ብለው በጊዜው የነበሩ መሻይኾች ተሰብስበው "ፌንጥ" አሏቸው። ("ፌንጥ" አሁንም ድረስ ያለ አደገኛ ማህበራዊ ማእቀብ ነው። "ፌንጥ" የተባለ ሰው ከየትኛውም ማህበራዊ ህይወት ይገለላል። ሰላምታ እንኳን ይነፈጋል። ከሕዝብ መሐል እየኖረ በጫካ ውስጥ ከመኖር በላይ እየተሳቀቀ ባይተዋርነትን ይገፋል።)
ዑካሻ በጠንካራው የተውሒድ አቋማቸው የተነሳ አድማ ተመታባቸው። ከአቋማቸው ሊያሽመደምዷቸው በማለም ሸይኾቹ ተሰብስበው "ፌንጥ ብለንሀል" አሏቸው። የዑካሻ መልስ ግን ያልተጠበቀ ነበር። "እኔም ፌንጥ ብያችሁዋለሁ! ምን ታመጣላችሁ?!"
·
አዎ ሁለ ነገሩን ለአላህ የሰጠ ሰው፣ የሰው ሴራ ለአላህ ብሎ ከያዘው አቋሙ አያጥፈውም። የሰው ጭብጨባ በሙቀት አያቀልጠውም። አላህን የያዘ ምን አጥቷል! ከአላህ ጋር የሆነ ምን ያስፈራዋል!
·
ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! ከምንም በፊት ከአላህ ዘንድ ሰው እንሁን። በምኞት ሳይሆን በተግባር ሰው ለመሆንም እንጣር።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 13/2011)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor