ስድስት ትንግርታዊ የሐረር ቱውፊታዊ ታሪኮች
- ሳሙኤል በለጠ
መነሻ
ጋሽ ዓለማየሁ ገላጋይ ጎንደር የሕልሙ ከተማ ብትሆንበት እንዲህ አለ "ጎንደር የሕልሜ ከተማ ናት፤ ምናልባትም ከልደት በፊት-በፊት የማውቃት፤ ለአንዱ ጀግና አድሬ የተዘዋወርኩባት፣ ወይም በክፋት ያስጨነኩባት …" እያለ ይቀጥላል። እኔም ለሐረር እንዲህ ነው የሚሰማኝ በመንፈስ የነቃች ይመስለኛል። ከዓለማዊ መልክ የሸሸች በመንፈሳዊ ሥልጣኔ ያ' በበች ትመስለኛለች። በሥራ ምክንያት የተለያየ አገር ብሄድም ሐረር እንደ ሄድኩ ስገባ ልቤ ደንገጥ ብሏል። ትመስለኛለች ያልኳት ሐረር ገዝፋ ታየችኝ። ስልጣኔ ከቤት ይጀምራል፤ ጥንታዊነትና ዘመናዊነትን ከጥልቅ ትርጉም ጋር አቅፎ የያዘው ኪነ-ህንፃዊ አሰራሩ/architectural style፣ ቴክኖሎጂ ባልተወለደበት ዘመን የተጠቀሟቸው ለጤና ስሙም የሆኑ ንጥረ-ስሪቶች/materials፣ የእስልምና ኋይማኖትና የሐረሪ ብሄረሰብ መገለጫ የሆኑ ልዩ እሴቶች/values ኪናዊ ስብጥር ከብዙ ጥቂት መገለጫዎች ናቸው። ቤቱ የተቀባው ቀለም ሲታይ ዝምብሎ ይመስላል - ታሪኩ ሲነገር በቀለሙ ውስጥ የቁዛሜ ታሪክ ይዟል። እነዚህ የጥንት ስልጣኔያቸውን የሚናፍቁ የሚመስሉ የቤት ታሪኮች እልፍ ታሪኮችን ይዘው የቤቱ 'ዲካው'(ጣሪያው) ላይ ባሉት የዋንዛ ርብራቦች ቁጥር ልክ ታሪካቸው አይቆጠርም፤ አይቋጭም ።
የሐረሪ ሕዝብን ለመግለጽ ስለተቸገርኩ የባላዝ ሚዲያ አዘጋጅ የነበረው ግሊን ባክ በአንድ ወቅት ያለውን ልጥቀስ "ለአንተ መልካም ነው! ልብ አለህ አይደል? ነጻ መሆን ትችላለህ ግን ልብህን ከአእምሮህ ጋር አጣምረህ ወግ አጥባቂ መሆን ትችላለህ።" (Good for you, you have a heart, you can be a liberal. Now, couple your heart with your brain, and you can be a conservative.)
የሐረሪ ሕዝብ ነጻ ሕዝብ ነው። እዛ ያሉ ነፍሶች ልብና መንፈሳቸው ያ'ወሩ(ስሙም) ናቸው። ከልብ ለልብ የሚኖሩ ለልብ የቀረቡ ነፍሶች ከተማይቱን ሞልተዋታል።
የሥነ ጽሑፍ ኀያሲው ቴዎድሮስ ገብሬ "ቱውፊታዊ ታሪኮች የሰውን ነገረ ፍጥረትና የኅላዌ እንቆቅልሾችን (ontological and cosmological questions) ለተመሰቃቀለው ዓለም ሥርዓት (cosmic order) ለማበጀት የባተለበት እምነታዊና ፍልስፍናዊ ጥበብ ነው" ሲል ቱውፊታዊ ታሪክን ይገልጸዋል። እኔም በሐረር ቆይታዬ ያስደነቁኝን ቱውፊታዊ ታሪኮችን ላስከትል።
1. የሐረር አመሰራረትና ስያሜ
የዛሬይቱ ሐረር ከመመስረቷ በፊት ከአንድ ሺህ አመት በፊት በሰባት ጎሳዎች የሚመሩ በሰባት መንደሮች የተከፋፈለች ነበረች። ዊኪፕዲያ የታሪክ መዝገብ እንደሚለው ሐረር በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በተለምዶ ሼኽ አባድር በሚባሉ በመደበኛ ስማቸው ሸኽ ኡመር አል-ሪዳ (Abadir Umar ar-Rida) በተባሉ ብጹዕ የሐይማኖት አባት ከርሳቸው ጋር አራት መቶ አራት የሐይማኖት አዋቂና መምህራንን በማስከተል የሳውዲ ግዛት ከሆነችው ሂጃዝ ተነስተው የዛሬይቱ ሐረር እንደደረሱ በአፈ ታሪክ ይነገራል።
እነዚህ ሰባት የተከፋፈሉ ስምምነት ያልነበራቸው ጎሳዎች በማሰባሰብ የአንድ ነገድ ግንድ ጎሳዎች የሆኑ አካላት በሐይማኖትም በስነ-ምግባርም መለያየት አግባብ አይደለም በማለት አሰባስበው በማስታረቅ፣ በወንድማዊ ክር በማሰርና በማዋደድ አንዲት ጠንካራ መዲነቱል ሐረር እንደመሰረቱ በሐረር ቃለ ቱውፊት ብሎም በታሪክ መረጃዎች በወርቃማ መልኩ ተጽፏል።
2. የአጥንት ትውፊት
በጥንት ዘመን ሐረር ላይ ሥጋ ከተበላ በኋላ የስጋ አጥንት አይጣልም። ምክንያቱ ደግሞ፤ አንድ፣ አጥንት የመልካም ጂኖች ምግብ ነው፤ ሁለት፣ በአጥንቱ ውስጥ ክፉ ጂኒ(ቆሪጥ፣ አጋንንት) ይኖራል ተብሎ ይታመናል። ስለዚህ አጥንቶቹ ተሰብስበው በጀጎል ግንብ ዙሪያ ይቀበራሉ። የአጥንቱ መቀበር በርካታ ጥቅም አለው አንዱና ዋነኛው ጥቅም ሐረር በምስጥ እንዳትወረር ይጠብቃታል ተብሎ ይታሰባል። ሌላው ዝማሚት(ምስጥ) ወደ ሐርር ግንብ እንዳይገቡ ይከላከላል። ከገቡ ግንዶች፣ ጥንታዊ መጽሐፎች ስለሚያበላሹ የተቀበሩት አጥንቶች እንደ ተከላካይ ሆነው አገልግሎት ላይ ይውላል።
3. የሐረር ጅቦች
ጅቦች በባህሪያቸው የሞተና የበሰበሰ ነገር እንደሚመገብ(Scavenger Animal) እንደሆነ የገባቸው የሐረሪ መንፈሳዊ አባቶች ከሐረር በሮች ልክ 'ወራባ ኑዱል' የተባለውን በር ለጅብ መግቢያና መውጪያ አበጁለት። ጅብም የማይታይ ጅን(ቆሪጥ፣ አጋንንት) ማየት ስለሚችል እነዚህን እንዲሁም በየቤቱ የምግብና የስጋ ትርፍራፊ በልቶ ይወጣል። የሐረር ጅብ በአካል ያለን ፍጡር ስለማይበላ የሐረር መንፈሳዊ አባቶች ጅብን እንደ የቤት ድመትና መሰል እንስሳ አላምደዋል። በሰውኛ መጥሪያ ስሞች ጠርተው በእጅና አፍ ይመግባሉ። በየአመቱም ለጅቦች የሚዘጋጅ ልዩ ገንፎ የማብላት ትርኢተ-ድርጊት/festival አላቸው።
4. ጫት በሐረር
የዛሬን አያርገውና በጥንቱ ሐረር ጫት ጥቅሙ ለተከበረ ድርጊያ ነው የሚውል የነበር። ለስራ፣ ለጸሎት፣ ለኋይማኖታዊ አሰላስሎት/contemplation እንዲሁም ለጠቃሚ የጉልበት ስራ ነበረ የሚቃም። የመቃሚያ ሰዓት ደግሞ ፀሐይ ወጥታ አምስት ሰዓት ሲሆን ቆይታውም ፀሐይ እስኪከር ይሆናል፤ እንዳ'ሁኑ ምሳ በልቶ እስከመፍዘዝ መወዘፍ አልነበረም። ከዛ ገበሬ የሆነ ወደ እርሻው፣ ነጋዴ ወደ ንግዱ፣ የኋይማኖት ሼሁ ወደ ንባብና ወደ ፀሎት ይሄዳሉ። በዛች ሰዓት የቃሟት አንዲህ ፍሬ ጫት እስከ ለሊት ኢሻ(የቀኑ መጨረሻ ስግደት) ድረስ ሃይ/ህያው/ንቁ አድርጎ በማዝለቅ ጠሃይ ጠልቃ ጨለምለም ሲል በድካም ወደ መኝታቸው እንዲያመሩ ምትሃታዊ ጉልበት ይቸራቸዋል።
5. የሐረር ባለከለር ድመቶች
ሐረር ድንቅ የድመት ቃለ ቱውፊት አለ። በፊት የሐረሪ ባህላዊ ቤቶች ከአፈር ነበር 'ሚሰሩት። ሐረር ግንብ ዙሪያ ግንብ ውስጥም ጭምር እባብን ጨምሮ የተለያዩ ተሳቢ እንሰሳት ነበሩ። ስለዚህ እያንዳንዱ የሐረሪ ቤት ውስጥ የሚገኙ ድመቶች ስራ ይህን እባብና አይጦች ለመከላከልና ሌሎች ምስጢራዊ ሚስጥሮችን ያጨቁ ግብሮችን የሚያጎናፅፉ የሚያማምሩ ድመቶች ነበሩ፤ አሁንም አሉ!
6. የማይሞቀው የማይቀዘቅዘው የሐረር አየር
ሐረር ለሰው ልጅ እጅግ ተስማሚ አየር አላት። ሪቻርድ በርተን የተባለ የታሪክ ተመራማሪና ተጓዥ የሐረርን አየር እንዲህ ይገልጸዋል "ሐረር የምትሞቅ የማታቃጥል፤ የምትቀዘቅዝ የማትበርድ አየር(warm but not hot, Cool but not cold)" ያላት ከተማ ናት ይላል። ጥንት ሐረርን የመሰረቱ የሐረሪ በመንፈሳዊ ትምህርትና ጥበብ/ religious wisdom የመጠቁ አባቶች የከተማዋን ቦታ ሲወስኑ ለጤና ጥሩና ተስማሚ አየር እንዲኖራት በማሰብ ሙዳ ስጋ ቆርጠው ዛፍ ላይ ሰቀሉ፤ በነጋታዉ ሲመጡ ስጋው የተሰቀለበት ከባቢያዊ አየር ሙቀት ቢሆን ስጋው ይበላሻል፤ እጅጉን ቀዝቃዛ ከባቢያዊ አየር ካለ ደግሞ ስጋው ይደርቃል። የአሁኗ የሐረር ጂኦግራፊያዊ መገኛ ስፍራ በዚህ ጥበባዊ ስሌት ከብዙ የሙከራ መነሳትና መውደቅ/try and error በኋላ ስጋው ከአንድ ቀን አዳር በኋላ ሳይበላሽና ሳይደርቅ በነበረበት ቆይቶ ምንም ለውጥ ባለማሳየቱ ለሰው ልጆች ተስማሚ አየር እንደሆነ ተምኖበት እዚህ ቦታ ሐረር ትቆርቆር ብለው ሐረርን መሠረቱ!