ሳሙኤል በለጠ(ባማ)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የሐሳብ ነገር
| @wosdomati |

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


አልተዛወረችምና እውናዊ ልብ ወለድ
[ኂሳዊ ዳሰሳ]
በሳሙኤል በለጠ

"የልብ ወለድ ደራሲ ወይ ነገር ተመልካች ወይም ደግሞ አመላካች ነው። በተጨማሪም በልብ ወለዱ በሬካታ ተሞካሪ ነገሮች አሉ፥ ወይ እውነት ይሰጥሃል ወይ የእውነቱን መነሻ ነጥብ ታገኝበታለህ፥ ገጸ ባህሪያት የረገጡትን ምድር አልፎም ማለዳና ጨለማውን ለማሳየት ገጸ-ባህሪ ፈጥሮ የሰውንና የተፈጥሮን ምስል ያሳይሃል።"( Émile Zola, The Experimental Novel, p. 8 )

ደራሲ ገጣሚና ኀያሲ በዮሐንስ አድማሱ በ1961 ዓ.ም በጻፉት "የልብ ወለድ ሥነ ጽሑፍ ጉዞ" በሚለው ኂሳቸው ላይ በዘመኑ የነበሩ የልቦ-ለድ መጽሐፎች በሦስት መሰረታዊ ምክንያት ጥሩ እንዳልነበሩ ይነግሩናል።

ሀ/ በቴክኒክ ጉድለት፤
ለ/ በሒስና በሐያሲ እጦት፤
ሐ/ በደራስያኑ አማርኛ መበላሸት።

የነፍቅር እስከ መቃብር ዘመን አልፎ ያልተቀበልናቸው እነ ዳኛቸው መጥተው ልቦለዳችን ወደ ድህረ-ዘመናዊው አጻጻፍ በነ አዳም ረታ፣ በነ ስንቅነህ እሸቱ(ኦ ታም ፕልቶ)፣ በነ ሌሊሳ ሲተካ የልብ ወለዱ ዘርፍ አበበ ነገር ግን አሁንም ዮሐንስ አድማሱ ያነሱት ጉድለቶች ነበሩ ወደ ተነሳንበት እንምጣ አሌክስ አብርሃም በሥስት የሥነ-ጥበብ ዘርፍ ማለትም በግጥም፣ በአጫጭር ልብ ወለድ፣ አሁን ደግሞ በረጅም ልብ ወለድ በዚህ ዘመን ብዕራቸው ከደመቀላቸው እንዲሁም ሠፊ አንባቢ ማግኘት ከቻሉ ደራሲዎች ተርታ ለመሰለፍ ችሏል።

ለዛሬ በሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ገጽ በአራት ክፍል የተከፈለውን "አልተዛወረችም" ሲል አሌክስ ርዕስ የሸለመውን መጽሐፉን ከእውናዊ(Realism Literature) የሥነ-ጽሑፍ አጻጻፍ ይትብሃል አንጻር እንመልከተው ሁሌም እንደምጽፈው ሥነ-ጽሑፍ በተለያየ ዲሲፕሊን ሲኄስ የኀያሲው ምልከታ እንጂ ደራሲው እንደዛ አስቦ ላይጽፈው ይችላል።

እንሂድ ዳኛቸው ወርቁ ከሞልቬር ጋር በነበረው ቃለ-ምልልስ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር "Good Literature reflects the life and spirit of a people"¹ (ደገኛ ሥነ-ጽሑፍ የሚህበረሰቡን መንፈስና ሕይወት የሚያንጸባርቅ ነው።) የአሌክስ አልተዛወረችም የማሕበረሰቡን መንፈስና ሕይወት በማንጸባረቁ ደገኛ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ይካተታል እንበልና ወደተነሳንበት ጉዳይ እንዝለቅ:-

ሀ.የአጻጻፉ ይትባህሉ ምንነት!

ሪያሊዚዝም በአሌክሳንደር ሹሽኪን የተዋወቀ ርዕዮተ ዓለማዊ የአጻጻፍ ፍልስፍና ሲሆን በራሺያ በሥፋት የተሰራጨ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል። ሪያሊዝምን ያጠኑት ደራሲና ኀያሲ ኤምሊ ዞላ እንደሚሉት ከሆነ የአጻጻፍ ይትብሃሉ እሙናዊ(faithful) በሆነ መልኩ ሕይወትን ድጋሚ መግለጽ ነው።² እውናዊ ሥነ-ጽሁፍ እንዲህ ይተረጎማል።

ለ. ጭብጥ (Themes)

አንድ ልቦ-ለድ ልብ ወለድ ከሚያስብሉት አንዱ ጭብጥ ነው። ነገር ግን በእውናዊ (Realism) አጻጻፍ ጊዜ ጭብጡ ሊያንስ ይችላል።³ "ዓይኖቿን ጨፍና ዕንባዋ ጠይም ጉንጮቿ ላይ ግራና ቀኝ ወደ ጆሮዋ እየፈሰሰ ነበር"(©አልተዛወረችም ገጽ-31) ይሁንና የሥነልቦና መደፍረስ፣ የሰውነት ግንብ በሌላ ሲናድ፣ ፍቅር፣ ጥላቻና ብቸኝነት ተራኪውን አብርሃምን የልቡ ጓዳ ገብተው የሚጎበኙት ስሜቱች ሲሆኑ ማህደርና ዮናስም የሚታመሱበት ትራውማ(ሽብር) በመጽሐፉ ተተርኳል።

ሐ.መቼት(Setting)

እውናዊ የሥነ-ጽሑፍ አጻጻፍ ይትብሃልን ያጠኑ ምሁራን እንደሚሉት ከሆነ መቼና የቱ ተለምዷዊ(ordinary) ነው ይላሉ "ግድግዳው፣ ጣሪያው፣ መኝታ ቤቱ፣ ሳሎኑ፣ መታጠቢያ ቤቱና ማብሰያ ቤቱ ሁሉ ቁጥር ስፍር በሌለው ትዝታዬ ተሞልቶ፣ ገና ሳምንት ሳይሞላኝ አዲሱ ቤት ዕድሜ ልኬን የኖርኩበት አሮጌ ዋሻ መስሎ ተሰማኝ"(©አልተዛወረችም ገጽ-54) የአልተዛወረችም መቼት ቀለል ያለና ተለምዷዊ ነው። ደምሥራ ሳይቀር ውበት የሞላባት ማህደር ከንፈሯ የማደንስበት ካፍቴሪያ እንዲሁም የአብርሃም ቤት የልብ ወለዱ ተለምቶሻዊ መቼና የቶች ናቸው።

መ. Causality built into text

የሠው ልጅ የኅላዌ ጣጣ አያበቃም⁴ ከዚህም አልፍ በጥላ(shadowed) ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ግን የሰውን ዘለለት ያበራያሉ⁵ ወይም ያፈካሉ ይሄንን መመርመር የሥነ-ጽሑፍ በተለይም የእውናዊ አጻጻፍ ይትብሃል መገለጫው ነው። "ባሌ ዕረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሊመለስ ሲዘጋጅ፣ በመለያዬታችን እንደ ሴት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።"(©አልተዛወረችም ገጽ-68) ማህደር የአብርሃምን የዕድሞ⁶ ጫፍ ጣቱ ሲነካው ተራኪው አብርሃም የነፍሱ ጫፍ ላይ ሲደርስ መልኳን ተመልክቶ ብቻ ለመኖር ሲጓጓ የኦሄነሪን "The last leaf" ያስታውሰናል። ኦ ሄነሪ ጆንሲን ገጸ ባህሪ አድርጎ በተረከው ትረካ ጆንሲ የሚረግፉ ቅጠሎችን ስታይ የመኖር ነገሯ እየጠወለገ ሲመጣ መጨረሻ ቅጠል ቀረች እሱን እያየች መኖር ቀጠለች ይሄንን ሥዕል ሲስል የነበረው በህርማን በበሽታ ይሞታል። የማህደር የሕልሟ መክሰምና የልጅነት ትራውማ(ሽብር) የአገር እንደ ጀንበር መንጋደድ የተደበቁ የሁላችንም ጥላ ታሪኮች የዛሬ አካላችንን የሠሩ ናቸው። አሌክስ ይሄንን በደንብ ተርኮልናል።

ሠ.ፍልስፍና (Emphasis on morality)

ማህበራዊነት ፍልስፍናና ፍልሱፋን የተብሰከሰኩበት የፍልስፍና ዐይነት ነው። እውናዊ አሳቢያን ደግሞ ለሥነ ምግባር አጽንዖት ሲሰጡ ውስጣዊ አንጻራዊ ነው። ይላሉ ሆኖም ይህ አስተሳሰብ ማሕበረሰብን በደገኛ ይሰራል። እውናዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ያሉ ገጸ-ባህሪዎች መዳረሻቸውን ጨብጠው ማህበረ-ከባቢውን ያሳዩናል። ነገር ግን ልብ ወለዱ ሲያልቅ ለአፍቃሬ አንባቢው ሐሳቡም፣ ስሜቱም፣ እውነቱም፣ እምነቱም፣ ክፍት ነው። "ትንሽ ሐውልት ውለታቸው ባረፈበት ሰው ልብ ቢቀር ምኑ ነው ክፋቱ!?" (©አልተዛወረችም ገጽ-239)

ማጠቃለያ

ይኽ የአሌክስ የመጀመሪያ የረጅም ልብ ወለድ ሥራው ነው። እውናዊ አጻጻፍ ይትብሃል(Realism Literature) በአልተዛወረችም ልብ ወለድ ውስጥ እንዴት ስላለው ተጽኖ የተሰማኝ ይህ ነው። ሌሎች የሥነ-አዕምሮ፣ የፍልስፍና፣ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎችም ልብ ወለዱን ወደራሳችሁ ቤት ብትጋብዙት እላለሁ!

የሕዳግ ማስታወሻዎች

1.Dannyachew Worku in "Black Lion" -An Overview By Sebhat G/Egziabher p.2

2.ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም እንዲል መጽሐፉ የሥነ-ጽሑፍ ሰው የሚታወቅን እንደማይታወቅ የማይታወቅን ደግሞ እንዲታወቅ አድርጎ መጻፍ እንዳለበት ይላል ደራሲ ሳሙኤል ጆንሰን

3.Themes are less obvious Indira Gandhi National Open University American Drama P.128

4.ኀያሲ ዓብደላ እዝራ

5.why something happens foreshadowed Foreshadowing in everyday


ክረምት ነበር ፥ ርጥብ ዝናብ ከንፋስ ጋራ
(ከላይ ወረደ ፥ አወናወነኝ¹ ሊጥለኝ)
'ርቃን ገላዬ ቀለም የነካካው ጣቴ
ጸጉርሽን ሊጎትት፥ ሲጥር
(ገለሽ ከምስሉ አመለጠኝ)
"ትንሽ አመመኝ
ለምን? ሰዓሊ ነኝ"
ውሽንፍር ዝናቡ ዓይኔን እየጠበሰው
አማልዕክት-መሳይ ገላሽን ለመሳል
(ስታገል ዓይንሽ ዓይኔን እየፈጀው)
ምስልሽን ለመስራት ታገልኩኝ
በክረምት ታገልኩኝ በበጋ
(እየመሸ ነጋ)
ይሄ ሁሉ መጣር ይሄ ሁሉ መጋር
አንቺን ለመሳል ነው?
(አይደለም አይደለም)
ሥዕልሽ ያደርሳል ከሕይወት ዳር²
(እውነት)
(እውነት)
(እውነት)

1. መወዛወዝ፣ መንገዳገድ፣ ወደግራ ወደቀኝ ማለት
2. ዝመዳ In The Midst Of Winter Albert Camu


ከአዳማ ወደ ድሬ ዳዋ የሚወስድ መኪና ውስጥ ... ላብ ካቸፈቸፈበት አየር ስር አንዲት ሴት ተቀምጣለች ። ጸጉሯ ተበታትኑዋል። ፊቷ ላይ ማዲያት ጥላውን ጥሏል። ለንቦጩን የጣለው መኪና የሁሉንም ጩኸት አፍኖ ይዟል። ከሁሉም ሰዎች ይቺ ሴት ደመቅ ብላ ትታያለች ። በዛለ ክንዷ ሮዛ የሚል መጽሐፍ ይዛ : በመጽሐፉ መሃል ጠቋሚ ጣቷን ከታ መጽሐፉን ቆልፋዋለች ። ከውልደት እስከ አሁን ያለው ኅዘኗ አካሏን ሰርቷል ? ...2

ሳን ሚጉኤል የጻፈውን 'voices from silence' ን እየባከንሁበት : የልብ - መልኳን እያሰስሁበት : የሴቲቷን አይኖች ለማዬት ቀናሁ ። ታሪክ ድጋሚ ተፈጠረ ። የሰው ቀለሙ በቀን : አካሉም በፀሐይ ይሳላል ። የተናገርነው ጭምር የቃላት ቀለም ነው ። እነዚህ ናፍቆት ይሆናሉ ። አንዳንዴ ቢጫ ጥላ አያጠላም ። ተስፋ ማጣት : ተስፋ አለማዬት---ሕይወት--- ሳይወድ በግዱ ሰው ፈሳሽ ጨለማውን ተግቶ ያጋሳል ። ጥጋብ አይደለም---።

"የት ነው የምትሄደው?"

"ጨለንቆ ! አንቺስ?"

"ድሬ ዳዋ" መርጋት ተደላድሏል በድምጿ ::

"ለሥራ ነው?"

"አዎ ! አንቺስ ?''

"እኔም"

"ምን ትሰሪያለሽ ?"

ዝም .....

መኪናው በፍጥነት ይጓዛል ። መኪና ውስጥ ባሉ ሰዎች ሕመም ተደብቋል ። በወና ህዋ የተንሳፈፉ ቀለማት አርፈውባቸዋል ። በአበባና በአበባ መካከል እንዳለ ፈገግታ ፈገግ ብላ ጥርሷን ገለጠች ።በእርግጥም የስዕልን ርቃቄ ነች ።----

"ምንድነው? የምታነበው?"

"ሳን ሚጉኤልን ታውቂዋለሽ?"

" የሚወራለት ንባብ የለኝም :: አንድ ...አንድ ...ከሁለት አይበልጡም ያነበብኋቸው ። ምን ፃፈ ያንተስ ሰውዬ ?"

"ስለ አርጀንቲናዎች የጻፈው ነው።" ነገር በእንጥልጥል ...

ከንፈሮቿን በአይኔ ሰሳምኩ ...

''ሮዛ ደስ ይለኛል ። ይሄ መጽሐፍ ብዙ ጣእሞች አሉበት ። ቡዙ እጆች ፣ ብዙ ገላዎች ፣ ተነክተውበታል ። አፎች ተጣመዋል ። ድምጾች ሰልለው ፣ ጸጉሮች ጸጥ : ጭጭ : ረጭ : ብለውበታል። ብዙ ሕመሞች ...! ትራስ ላይ ተንሰቅስቀው ፣ ሲያለቅሱም ፡ ሳያለቅሱም ፡ ሳግ ፡ ሲያንቃቸው ጭምር አይበታለሁ... ። አንዳንዴኮ... አንዳንድ አካሎችም : አእምሮ ላይ እንደ በረዶ ይረጋሉ ። ደስ አይልም ? አንዳንድ አካሎች ደግሞ በሌላ ይሰንፋሉ ። ሲያስጠላ ! ይሄ ፍቅር ። የሰው ልጅ ተጫውቶ የሚሸነፍበት ካርታ ። ጦር ያለው ። የሚዋጋ ። የሚያቃጥል ...''3

"ካነበብሁት ቆዬሁ ። በለኮስሽኝ ... እስካልበርድ : እስካልረግብ : በትውስታ ምሪት እንደ አጥቢያ ኮከብ እንዳልበርቅ ፈራሁ ። ሃሃሃ ... "

'' ጥሩ ታወራለህ ። ድምፅህ መግራት አለው ።''

'' መኖርን አታስመስግኝኝ ! ''
.
.
.

ለፀሐይ እንደተተወ ውጥር ቆዳ : የሁሉም ሰው ፊት ሲቃጠል : ዜማም : ግጥምም : እንደ ሌለው ሙዚቃ ነገሮች ዝም ሲሉ : ብልቶች እንቅስቃሴ ሲያቆሙ----- ልቦች በልቦች ሲጎዱ : ቀጭን ሰይጣን ግንባሩ ላይ በለኮሳት እሳት ሲነድ----- በመጽሐፍ መልካ - መልክ ላይ ተዘበራርቆ ተደርሷል። ስለ ቀለም : ማንም... ስለሌላቸው ነፍሶች : ተወግረው እንደጎበጡ አካሎች : እንደተዘበራረቀው ተፈጥሮ : መኪናው ጥሎ እንዳለፋቸው የትላንት መንገዶች : እንዳልተከፈተ ሙዚቃ : ቅላጼ እንደሌለው ሕመም : በውስጥ እንደሚመላለስ : የሚንሴጠሰጥ ጩኸተ - ራስ : የማይያዝ : የማይጨበጥ : የማይደረስበት : የራቀ : በጣቶቼ ልጨብጠው ስል ...ሲያዳልጠኝ : በቃ! በቃ ! ይሄም ...ትንሽ ትንሽ ያማል።''---4

"የት ደረስን?"

"አዋሽ 40"

ካንቀላፉ ትላንቶች ቅዠት ...ቀለም ሲውለበለብ...! ረጋ ካለ የአዋሽ ተንሳፋፊ ሐይቅ : ሙቀት የሚያነጥባቸው ላቦች... በገላ : በገጻችን ሲሰፉ : በቃ! ----አይኗ ተስለመለመ ። ቅንድቧ ስር ላብ አቸፈ---።

"እምልሽ ለምን ሮዛን ወደድሽ ?"

"እኔ እንጃ ! ምናልባት ታሪኬን ስለሚነግረኝ ?።"

" ብዙ ኖርሽለት ለሃዘን ? ተጎናበስሽለት ለደስታ ?"

ምኑ ይነገራል ብለህ ?

እዚህ ጥያቄ ምልክት ላይ! ብዙ አዳፋ ታሪኮች አሉ ። ቢጻፉ የማይጠሩ ። ሸፋፋነታቸው በጫማ የማይሸፈን ። መንገድ የጠፋባቸው የታሪክ እግሮች : አቅጣጫ የሌላቸው : ቀለም የሌላቸው : ስሜት የሌላቸው : ብዙ ምንም የለሾች -----ያልተሞሸሩ ሕመሞች : ማንም ያልካደመላቸው : የበለዘ ወዝ : ጠረን የሌለው ሰመመን : ምጽአት የራቀው በድን : በአይን ቆብ ተጠቅልሎ ያሸለበ አይን : በጨረር የተጠቀጠቀ አይን ... ለህመሟ ስታሸልብ እያያሁዋት ...! ---- ከተከፈተው ጭኗ ጠባሳዋን ማዬት : ለአዋሽ እንደ ገባር የገባ ዕንባዋን ማለቂያውን ማዬት ፈለግሁ ። ኦ ! አንተ አላህ ። ኦ ! ያንተ ያለህ ...።

ከታሪኳ : ከነካካችው ገላዋ : ከነኳት ገላዎች : የሚነሱ ታሪኮች ታሪክ ለመሆን ሲጣጣሩ : ሲጥሩ : ሲፈጉ : ዝም ብለው ዝም አስባሏት ። የወገገ ታሪኳን ሲያርመጠምጡት : በጣታቸው ሲያጨማልቁት---- የማያውቋት : የማታቃቸው : ደሟን : ደም ግባቷን : ከደምስሯ ሰርገው ሲጠቡት : አያውቁ ይሄን መከራ---- አያውቁ ይህንን ሕይወት ---- ልስልስ ሞትና ---ከራስ መለየት ነው የሕይወት ኋላና ፊቷ ።

"እኔ እምልሽ ድሬ ዳዋ ለምን ነው ምትሄጅው!"

"ቁልቢ ነኝ"

" ኧረ ? ዘመድ ጥዬቃ ? ወይስ... ?"

" አይ ! ለንግስ... ስዕለት አለብኝ ። ዘቢብ መልኬን : ፀጋ ወዜን አደርሳለሁ ። "

" ስለ ቀደስሻት ቀኔ : ሌሊቶቼን ሰዉቼ እጎናበስልሻለሁ ። ሃሌታን እወጣልሽም ዘንድ አስብሻለሁ ። ''

'' ሃዘን ተቃመስን አይደል ? በደስታህ በኩል ተጋደምኩ ?''

'' የዕንባ መና የሕይወት ችሮታም ነው :: ''

ከተሳፈርኩበት ወረድኩ :: የሳን ሚጎኤልን መጽሐፍ ጨርሼ እጄላይ ተዝረክርኳል :: ጨረቃ ... ከርቀት ተቀበለችኝ ። ባለንጀራዬ ከሩቅ ጨረቃዋን ቀድሟት ይመጣል። የምናየው የማይታየውን ቀለም ነው ? የምናየው የኛ ቀለም ነጸብራቁ አይናችን እንዳልሆነስ ? የደም ዝውውራችን የተደበቀ ሌላ ቀይ ቀለም ይሰጣል ። የኖርነው ዛሬ : የዛሬ ቀለም ነው ። የናፍቆት ቀለሙ - መለያዬት ነው ? የተለዬኋትን ? የተነጠልኳቸውን አሰብሁ ።

ዞር ብዬ መኪናውን አየሁት ። የተጫነበት ሃሳብ እንደሚያንገዳግደው : ወደ ቀኙ : ወደ ግራው እንደሚያስዘምመው ይሆናል ::

1.The color introduced by daylight ግጥም ፓሬ
2.ግራ ገብ በሆነ ዓለም አንዳንዴ ክምችት(restኸ mass) በሐዘን ሊፈጠር ይችላል አካልም
3. እንቅልፍ አሸለብ አረጋት የሚዘንበው የኃዘን ዝናብ ቆመ
4.የመንገድ ኃሳቦቸ
6.የሚቀጥ[...]


የውስጥ ቀለሞች ...
:

ቀና አለ ። ግራጫው ሰማይ ላይ የተሰመሩት ወፎች ቁልቁል : ወደ ታች : ይወርዳሉ ። ዝቅ ሲል ...ከከንፈሩ የሚያፈተልከው የሲጋራ ጢስ ፊቱ ላይ ብን : ብን : ይላል ። አእምሮው ውስጥ ቀይ - ቢጫ - ነጭ - ቀለሞች ተፈጥረዋል:: -----1

ከአዳማ ወደ ድሬ ዳዋ የሚወስድ መኪና ውስጥ ... ላብ ካቸፈቸፈበት አየር ስር አንዲት ሴት ተቀምጣለች ። ጸጉሯ ተበታትኑዋል። ፊቷ ላይ ማዲያት ጥላውን ጥሏል። ለንቦጩን የጣለው መኪና የሁሉንም ጩኸት አፍኖ ይዟል። ከሁሉም ሰዎች ይቺ ሴት ደመቅ ብላ ትታያለች ። በዛለ ክንዷ ሮዛ የሚል መጽሐፍ ይዛ : በመጽሐፉ መሃል ጠቋሚ ጣቷን ከታ መጽሐፉን ቆልፋዋለች ። ከውልደት እስከ አሁን ያለው ኅዘኗ አካሏን ሰርቷል ? ...2

ሳን ሚጉኤል የጻፈውን 'voices from silence' ን እየባከንሁበት : የልብ - መልኳን እያሰስሁበት : የሴቲቷን አይኖች ለማዬት ቀናሁ ። ታሪክ ድጋሚ ተፈጠረ ። የሰው ቀለሙ በቀን : አካሉም በፀሐይ ይሳላል ። የተናገርነው ጭምር የቃላት ቀለም ነው ። እነዚህ ናፍቆት ይሆናሉ ። አንዳንዴ ቢጫ ጥላ አያጠላም ። ተስፋ ማጣት : ተስፋ አለማዬት---ሕይወት--- ሳይወድ በግዱ ሰው ፈሳሽ ጨለማውን ተግቶ ያጋሳል ። ጥጋብ አይደለም---።

"የት ነው የምትሄደው?"

"ጨለንቆ ! አንቺስ?"

"ድሬ ዳዋ" መርጋት ተደላድሏል በድምጿ ::

"ለሥራ ነው?"

"አዎ ! አንቺስ ?''

"እኔም"

"ምን ትሰሪያለሽ ?"

ዝም .....

መኪናው በፍጥነት ይጓዛል ። መኪና ውስጥ ባሉ ሰዎች ሕመም ተደብቋል ። በወና ህዋ የተንሳፈፉ ቀለማት አርፈውባቸዋል ። በአበባና በአበባ መካከል እንዳለ ፈገግታ ፈገግ ብላ ጥርሷን ገለጠች ።በእርግጥም የስዕልን ርቃቄ ነች ።----

"ምንድነው? የምታነበው?"

"ሳን ሚጉኤልን ታውቂዋለሽ?"

" የሚወራለት ንባብ የለኝም :: አንድ ...አንድ ...ከሁለት አይበልጡም ያነበብኋቸው ። ምን ፃፈ ያንተስ ሰውዬ ?"

"ስለ አርጀንቲናዎች የጻፈው ነው።" ነገር በእንጥልጥል ...

ከንፈሮቿን በአይኔ ሰሳምኩ ...

''ሮዛ ደስ ይለኛል ። ይሄ መጽሐፍ ብዙ ጣእሞች አሉበት ። ቡዙ እጆች ፣ ብዙ ገላዎች ፣ ተነክተውበታል ። አፎች ተጣመዋል ። ድምጾች ሰልለው ፣ ጸጉሮች ጸጥ : ጭጭ : ረጭ : ብለውበታል። ብዙ ሕመሞች ...! ትራስ ላይ ተንሰቅስቀው ፣ ሲያለቅሱም ፡ ሳያለቅሱም ፡ ሳግ ፡ ሲያንቃቸው ጭምር አይበታለሁ... ። አንዳንዴኮ... አንዳንድ አካሎችም : አእምሮ ላይ እንደ በረዶ ይረጋሉ ። ደስ አይልም ? አንዳንድ አካሎች ደግሞ በሌላ ይሰንፋሉ ። ሲያስጠላ ! ይሄ ፍቅር ። የሰው ልጅ ተጫውቶ የሚሸነፍበት ካርታ ። ጦር ያለው ። የሚዋጋ ። የሚያቃጥል ...''3

"ካነበብሁት ቆዬሁ ። በለኮስሽኝ ... እስካልበርድ : እስካልረግብ : በትውስታ ምሪት እንደ አጥቢያ ኮከብ እንዳልበርቅ ፈራሁ ። ሃሃሃ ... "

'' ጥሩ ታወራለህ ። ድምፅህ መግራት አለው ።''

'' መኖርን አታስመስግኝኝ ! ''
.
.
.

ለፀሐይ እንደተተወ ውጥር ቆዳ : የሁሉም ሰው ፊት ሲቃጠል : ዜማም : ግጥምም : እንደ ሌለው ሙዚቃ ነገሮች ዝም ሲሉ : ብልቶች እንቅስቃሴ ሲያቆሙ----- ልቦች በልቦች ሲጎዱ : ቀጭን ሰይጣን ግንባሩ ላይ በለኮሳት እሳት ሲነድ----- በመጽሐፍ መልካ - መልክ ላይ ተዘበራርቆ ተደርሷል። ስለ ቀለም : ማንም... ስለሌላቸው ነፍሶች : ተወግረው እንደጎበጡ አካሎች : እንደተዘበራረቀው ተፈጥሮ : መኪናው ጥሎ እንዳለፋቸው የትላንት መንገዶች : እንዳልተከፈተ ሙዚቃ : ቅላጼ እንደሌለው ሕመም : በውስጥ እንደሚመላለስ : የሚንሴጠሰጥ ጩኸተ - ራስ : የማይያዝ : የማይጨበጥ : የማይደረስበት : የራቀ : በጣቶቼ ልጨብጠው ስል ...ሲያዳልጠኝ : በቃ! በቃ ! ይሄም ...ትንሽ ትንሽ ያማል።''---4

"የት ደረስን?"

"አዋሽ 40"

ካንቀላፉ ትላንቶች ቅዠት ...ቀለም ሲውለበለብ...! ረጋ ካለ የአዋሽ ተንሳፋፊ ሐይቅ : ሙቀት የሚያነጥባቸው ላቦች... በገላ : በገጻችን ሲሰፉ : በቃ! ----አይኗ ተስለመለመ ። ቅንድቧ ስር ላብ አቸፈ---።

"እምልሽ ለምን ሮዛን ወደድሽ ?"

"እኔ እንጃ ! ምናልባት ታሪኬን ስለሚነግረኝ ?።"

" ብዙ ኖርሽለት ለሃዘን ? ተጎናበስሽለት ለደስታ ?"

ምኑ ይነገራል ብለህ ?

እዚህ ጥያቄ ምልክት ላይ! ብዙ አዳፋ ታሪኮች አሉ ። ቢጻፉ የማይጠሩ ። ሸፋፋነታቸው በጫማ የማይሸፈን ። መንገድ የጠፋባቸው የታሪክ እግሮች : አቅጣጫ የሌላቸው : ቀለም የሌላቸው : ስሜት የሌላቸው : ብዙ ምንም የለሾች -----ያልተሞሸሩ ሕመሞች : ማንም ያልካደመላቸው : የበለዘ ወዝ : ጠረን የሌለው ሰመመን : ምጽአት የራቀው በድን : በአይን ቆብ ተጠቅልሎ ያሸለበ አይን : በጨረር የተጠቀጠቀ አይን ... ለህመሟ ስታሸልብ እያያሁዋት ...! ---- ከተከፈተው ጭኗ ጠባሳዋን ማዬት : ለአዋሽ እንደ ገባር የገባ ዕንባዋን ማለቂያውን ማዬት ፈለግሁ ። ኦ ! አንተ አላህ ። ኦ ! ያንተ ያለህ ...።

ከታሪኳ : ከነካካችው ገላዋ : ከነኳት ገላዎች : የሚነሱ ታሪኮች ታሪክ ለመሆን ሲጣጣሩ : ሲጥሩ : ሲፈጉ : ዝም ብለው ዝም አስባሏት ። የወገገ ታሪኳን ሲያርመጠምጡት : በጣታቸው ሲያጨማልቁት---- የማያውቋት : የማታቃቸው : ደሟን : ደም ግባቷን : ከደምስሯ ሰርገው ሲጠቡት : አያውቁ ይሄን መከራ---- አያውቁ ይህንን ሕይወት ---- ልስልስ ሞትና ---ከራስ መለየት ነው የሕይወት ኋላና ፊቷ ።

"እኔ እምልሽ ድሬ ዳዋ ለምን ነው ምትሄጅው!"

"ቁልቢ ነኝ"

" ኧረ ? ዘመድ ጥዬቃ ? ወይስ... ?"

" አይ ! ለንግስ... ስዕለት አለብኝ ። ዘቢብ መልኬን : ፀጋ ወዜን አደርሳለሁ ። "

" ስለ ቀደስሻት ቀኔ : ሌሊቶቼን ሰዉቼ እጎናበስልሻለሁ ። ሃሌታን እወጣልሽም ዘንድ አስብሻለሁ ። ''

'' ሃዘን ተቃመስን አይደል ? በደስታህ በኩል ተጋደምኩ ?''

'' የዕንባ መና የሕይወት ችሮታም ነው :: ''

ከተሳፈርኩበት ወረድኩ :: የሳን ሚጎኤልን መጽሐፍ ጨርሼ እጄላይ ተዝረክርኳል :: ጨረቃ ... ከርቀት ተቀበለችኝ ። ባለንጀራዬ ከሩቅ ጨረቃዋን ቀድሟት ይመጣል። የምናየው የማይታየውን ቀለም ነው ? የምናየው የኛ ቀለም ነጸብራቁ አይናችን እንዳልሆነስ ? የደም ዝውውራችን የተደበቀ ሌላ ቀይ ቀለም ይሰጣል ። የኖርነው ዛሬ : የዛሬ ቀለም ነው ። የናፍቆት ቀለሙ - መለያዬት ነው ? የተለዬኋትን ? የተነጠልኳቸውን አሰብሁ ።

ዞር ብዬ መኪናውን አየሁት ። የተጫነበት ሃሳብ እንደሚያንገዳግደው : ወደ ቀኙ : ወደ ግራው እንደሚያስዘምመው ይሆናል ::

1.The color introduced by daylight ግጥም ፓሬ
2.ግራ ገብ በሆነ ዓለም አንዳንዴ ክምችት(restኸ mass) በሐዘን ሊፈጠር ይችላል አካልም
3. እንቅልፍ አሸለብ አረጋት የሚዘንበው የኃዘን ዝናብ ቆመ
4.የመንገድ ኃሳቦቸ
6.የሚቀጥ[...]
:

ቀና አለ ። ግራጫው ሰማይ ላይ የተሰመሩት ወፎች ቁልቁል : ወደ ታች : ይወርዳሉ ። ዝቅ ሲል ...ከከንፈሩ የሚያፈተልከው የሲጋራ ጢስ ፊቱ ላይ ብን : ብን : ይላል ። አእምሮው ውስጥ ቀይ - ቢጫ - ነጭ - ቀለሞች ተፈጥረዋል:: -----1


https://t.me/goferaleather Mini baguette bag 👜
@Tsika23 DM
+251930326888 call


ከልብ ወለድ ባሻገር ባሻገር
”ሀገር ያጣ ሞት ሂሳዊ” ንባብ
ክፍል አንድ
ሳሙኤል በለጠ
አለመታደል ሆነና አንዱን ዘመን ሳናጣጥም ወደ አንዱ አዘመምን ልብ ወለዳችን ዘመናዊ ሆን ስንል ዮሃንስ አድማሱ ዘመናዊ ልብ ወለዳችን በጣት የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነገሩን እንዲህ እንዲህ እያልን በገድምዳሜው ድህረ ዘመናዊ ድርሰቶች ላይ ደረስን ነገሩ እንዲህ ነው። ድህረ ዘመናዊ ድርሰት በሥነ ግጥሙ እነ ሰለሞን ደሬሳና ሌሎችም በድርሰቱ አዳም ረታ ከተዋወቀ ወዲህ መልኩንና ቅርጹን እየቀያየረ አሁን ላይ የደረሰ ሲሆን የአጻጻፍ ይትብሃሉን ወጣት ደራሲያንም እያዘወተሩት መጡ በቅርብ አመታት ለንባብ ከበቁ መጽሃፍቶች ድህረ ዘመናዊ የድርሰት አጻጻፍ ይትብሃልን የደገበረው የሄኖክ በቀለ ለማ ”ሀገር ያጣ ሞት” አንዱ ነው።
ለመሆኑ ድህረ ዘመናዊ ድርሰት ምንድነው? ከዘመናዊ ድርሰትስ የሚለየወ ጠባዩ ምንድነው? የሥነ ጽሁፍ ሃያሲው ሺቫ ኪርካህ ”Alienation and Loneliness of American Postmodern Characters in Salinger’s Masterpiece Catcher in The Rye” በሚለው የጥናቱ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል ”The postmodern texts reveal skepticism about the ability of art to create meaning, the ability of history to reveal truth, and the ability of language to convey reality. All that skepticism led to fragmented, open-ended, self-reflexive stories that are intellectually fascinating but often difficult to grasp. The stylistic techniques of postmodernism include the frequent use of intersexuality, Metafiction, temporal distortion, magical realism, faction, reader involvement and minimalist techniques of reduction, omission and suggestion.” ድህረ ዘመናዊ አጻጻፍ በእነዚህ ጠባዮች ከዘመናዊ አጻጻፍ ተቃርኖ የቆመ እንደሆነ ይነግረናል። ሳሙኤል ቤኬት፣ ኩርት ቮኔጉት፣ ጆን ባርት፣ ሳልማን ሩሽዲና ሌሎች ድህረ ዘመናዊ የድርሰት አጻጻፍ ይትብሃል የሚከተሉ ደራሲዎች ናቸው ይላል።
የሄኖክ በቀለ ለማ ”ሀገር ያጣ ሞት” ከላይ ሃያሲ ሺቫ ኪርካህ የገለጸውን የድህረ ዘመናዊ የአጻጻፍ ይትበሃል መለያ ጠባይ ያለው መሆኑን እንረዳለን magical realism - አስማታዊ እውነታ የሄኖክ በቀለ ለማ በእያንዳንዶቹ ገጸ ባህሪያት እንዲሁም Self-reflexive Stories - የራስ ልዋጤ ታሪኮች አስማታዊ እውነታዎችን ይነግረናል። የህላዌ ስንክሳርን ለመፈከር ይጠይቃል ፍቅር፣ ክህደት፥ ወሲብና መቀማማት፥ ፀፀትና መስዋዕት፥ የትዝታ፣ ሞት፣ ህይወት ተስፋን መቀማት፣ በገጸ ባህሪዎቹ በዱና፣ በሊቀ መኩዋስ፣ በጸሎት በስዕለ፣ የተተወሩ - Plot- በጊዜ ውስጥ የተሰነጉ የተፈቱ፣ ያልተፈቱ፣ የሚያስቃትቱ፣ የሚያስነቡ የሚመስጡ የህላዌ ስንክሳር ናቸው። -Reader involvement- አፍቃሬ አንባቢን ማሳተፍ የድህረ ዘመናዊ የአጻጻፍ ይትብሃል አንዱ መንገድ ነው። ”ሳቁን ተሻምቼ አልጽፍለትም። ታዲያ ዛሬ በምን እዳው? እንደልጆቹ በቻለው ቋንቋ አፍ ላስፈታው። ከዛስ? ነፍስ እስከፈቀደ ይጨመርለታላ ይህ እንዲህ በሚያልፍ ዛሬ ላይ የተቃጣ ቅናት ነው። የቃል ፍቅር እዳው ምን ድረስ ነው?” (ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 200) ሄኖክ በቀለ ለማ በድርሰቱ በእያንዳንዱ መሥመር የአንባቢን ምናብ እየፈተነ ያሳትፋል። በእነዚህና መሌሎች መስፈርቶች ”ሀገር ያጣ ሞት” ድህረ ዘመናዊ ድርሰት ነው ማለት እንችላለን።
”ሰማይ በደመና ጭረት ፊቱ ተዥጎርጉሮ በዋለበት፤ የልጅገረድ ቅንድብ በመሰች ጭረት ጨረቃ በተኩዋለበት፤ በክዋክብት ውቅራት ስግግ ገላውን ባቀፈበት፤ የምድር ብሌን በስልችት ቁልቁል ካፈጠጠበት፤ የሀገር ሰው ሰነፍ ቆሎውን እያሻመደ ኩታውን እየተከናነበ የመከኑ ሕልሞቼን በሚከልስበት፤ ከጣሪያው ሥር ጥላሸትና ጠረን የጠገበ መረባ የተተከሉትን አይኖች በሚጠየፍበት፤ ግዑዛን አፋቸውን በምጥን ሃሌታ በሚፈቱበት፤ ወጣት ለቂሙ መቁዋጫ ቀጠሮ መሚቀጥርበት፤ የሃዋዝ መሰንቆ ሳይታለብ.....”(ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 10) ሁሉም የድህረ ዘመናዊ ሃያሲዎች እኔም የምስማማበት አንድ ነገር አለ ለድህረ ዘመናዊ ድርሰት የቋንቋ አጠቃቀም ቅጥ ራሱን ችሎ ገጸ ባህሪ ይሆናል። (the language style has become a characteristic of the novel) ሄኖክ ይህንን በድርሰት የሞከረ ብርቱ ደራሲ ነው።
”ባለ መሰንቆውን ሐዋዝ ተጫወት ቢሉት....
”ሞት ይቅርይላሉ ሞት ቢቀር አልወድም
ድንጋዩም አፈሩም ከሰው ፊት አይከብድም”ብሎ ነው። አይንህን ያሳየኝ ያሉት።
”ይሄ ምላስህ አንድ ቀን ይጠልፍሃል። የለፈለፍከው እርጥብ ገመድ ሆኖ ያንቅሃል” ብለውት መርቀውታል።(ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 39) ሥነ ጽሁፍ ከተለያዩ የህይወት የህይወት ህላዌ ጥያቄዎች ጋር ትስስር ይፈጥራል የሥነጽሁፍ ዳርዊኒዝም ሊቁ ጆሴፍ ካሮል ”literature deals with death in relation to three specifc themes in human life history: imminent threats to survival, childhood, and pair bonding” የሚል አጽኖት አለው ሥነ ጽሁፍ ከተለያዩ የህላዌ ጣጣዎች ጋር አጣምሮ መጻፍ ለጽሁፍ ፍካሬም ውበትም አውንታዊ ተጽኖ አለው ”ሀገር ያጣ ሞት” በጽሞና ላነበበው የሊቀ መኩዋስንና የሐዋዝን ነገረ ሞት ብቻ ሳይሆን የተዋቡን መቃተት በራስ ለዋጤ ታሪኮች የሚነገሩ ታሪኮች ውስጥ ሀገር የሚያህል የህላዌ ጣጣና ጥያቄ ያገኛል።
ታላቁ ዕዝራ አብደላ እንደሚለው ደግሞ ”በአንድምታ የተለበለብ የቋንቋ ትርታና ንዝረት ነው።” ሄኖክ ገጸ ባህሪን፣ ከህላዌ ጣጣ የህላዌ ጣጣን ከሃሳብ ሃሳብን ከ ግዜ ጋር ጊዜን ከሃገር ጋር አገርን ከህልውና ጋር አሹዋርቦ ነው የጻፈው ይች አገር ግን ሞቱን አልተቀበለችውም ወለፈንዳድ ህላዌአችንን ያሳያል በዕውቀቱ በአንድ ግጥሙ እንዳለው ”መንሳፈፉስ ይቅር እንዴት መስጠም ያቅተዋል ሰው?” ይህ የባይተዋር ገድላችን ነው መሰል ሄኖክ ይሄን ሁሉ አጣምሮ አንድ ተስማሚ አጽኖት ሳልሰጠው ባልፍ ትውልድ ይቅር አይለኝም ሂሴም ውሃ አያነሳም ብዙ ቲዎሪዎች ያሉትና የሥነጽሁፍ ሃያሲው ብራያን ማከል ”POSTMODERNIST FICTION” በሚለው መጽሃፉ ዋቢ ያደረገውን ሃሳብ ላንሳ ልሰናበት ”The skeleton of the layers and the structural order of sequence a literary work of art are of neutral artistic value; they form the axiologically neutral foundation of the work of art in which the artistically valent elements…of the work are grounded”
ክፍል ሁለት ይቀጥላል።


የመጨረሻው ናፍቆት

ካይኔ ዋሻ ተደብቄ ፣ ከል ሳለቅስ
የህጻንነቴን እርጥብ ዝምታ...
በመናፈቅ ባሁን መዳፍ ፣ ስደባብስ
ካይኔ ዋሻ እንዳለሁ
ነፍሴን እጠይቃለሁ?
ናፍቆት ትንሳኤ አለው?
“የናፍቆትን ክራር
በጣትህ ብቃኘው
ይጠዘጥዛል እንጂ
ዜማ አይሆንም ምነው?”

ጌታሆይ
በሰማዬ ላይ ያንዣበበው ፣ እዥ የደመና ቁስል
በጽሃይህ አታጥገው ፣ ላንተ ናፍቆት መቃጥያ ይሆነኛል።
ካሻት ህጻን ማለዳ ፣ የብርሃን ልሃጭ አትትፋ
የጽሃይም እግር ይሰበር ፣ ተስፋም ከማዕከሉ ይጥፋ።

ጌታሆይ
ናፍቆቴን መናገር ፣ ሞት ይወልዳል
የህጻንነቴን ለጋ ዝምታ ፣ መልስልኝ
የናፍቆቴ ትንሳኤ ፣ እሱ ይሆናል
ማን ያውቃል?


የአንዲት ሴት መከራ የወሲብ ቅድስናን ፍለጋ
𝕴𝖓 𝖘𝖊𝖆𝖗𝖈𝖍 𝖔𝖋 𝖘𝖊𝖝𝖚𝖆𝖑 𝖍𝖔𝖑𝖎𝖓𝖊𝖘𝖘
ሰው ለመከራ ነው የተፈጠረው የሚለው የነቪክቶር ሁግ አባባላዊ አጽንኦት አንዳንዴ ዋጋውን ያጣል ለምሳሌ የነቪክቶር ሁግ ሌስሚዘረብል ልብወለድ ላይ ፈንቲ ከጎረቤት እንዴት ያለስራ መኖር እንዳለባት ትማራለች፣ መከራ ሲቀጥል እንዴት ያለ ምግብ መኖር እንዳለባት ልትማር ትችላለች እነዚህ ሁሉ የመከራ ምሳሌዋች ትክክለኛ መከራን ለመፈከር አይሆኑም መከራ የሚመዘነው በሆነብን ነገር ክብደት ላይሆን በስሜቱ ጥልቀት ነው። ፓብሎ ኮሄልዮ “Eleven Minutes” የሚል ዝነኛ መጽሃፍ አለው እሲ ይህን መጽሃፍ እንዳሰው መጽሃፉ በብዙ ሺህ ኮፒዎች ከመታተም በላይ አልፎ በበርካታ ትርጉም ተሰርቶለታል።
እውቁ ሃያሲ ናስረላህ ናምቦሮል ከአመታት በፊት በመጽሃፉ ዙሪያ በሰራው ሂስ “ይህ ልብ ወለድ ውሎ አድሮ እውነተኛ ፍቅር ያገኘች ይህንን ለማግኘት ብዙ መስዋዕትነት የከፈለች የአንዲት ወጣት የዝሙት አዳሪነት ታሪክ ነው። ታሪኩን ስንገልጠው የወሲብ ቅድስናን ጭብጥ ላይ ያጠነጥናል። ለቁሳዊ ጥቅም ሲባል ወሲብ ርኩስ መሆኑን ያስገነዝባል፣ የወሲብ ጥምረት ወደ ቅዱስ ድርጊት የሚል አንደምታንም እናገኛለን” የሚል ምስክርነት ስለ መጽሃፉ ይሰጣል።
ደራሲው ለመጽሃፉ ካራክተር ያረጋት አንዲት ብራሊላዊት ሴት ሲሆን ማርያ ትባላለች ማርያ በወሲብ ንግድ ውስጥ የሰራች፣ የተሰደደችም ጭምር መከረኛ ናት እኔ ያለኝ የእንግሊዘኛው ቅጂ ላይ የማርያ የእለት እለት ባስታወሻዎች ከጀርባው አሉበት ኮሄሎ ታሪኩን ሲጀምር በአንድ ወቅት በአንድ ከተማ የምትኖር አንዲት ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች ይነግረናል ታሪኩ ለማመን የሚቸግር በመሆኑ ተጨባጭ ለማድረግ ሲጥር ደራሲው ከፍተኛ ሥነ ውበት ያለው የአጻጻፍ ይትብሃልን ይጠቀማል። ማሪያ ፍቅር ለማግኘት ያደረገችውን ጥረትና ስቃይ በደንብ ይተረካል። ማርያ የልጅነት ሽብር ወይም ትራውማ አለባት በዚህም ሰበብ የህልውና ስቃይ ውስጥ ገብታለች ገንዘብን ፍቅርን በየዳንኪራ ቤት ስትፈልግ የነበረችው ማርያ ያሳለፈችው መከራ ቀላል የሚባል አልነበረም።
የዕለት እለት ማስታወሻዋን ያነበበ አንባቢ ደራሲው በዘይቤ የካራክተሩዋን ፍለጋ ለማወቅ ይረዳል። ሁዋላ ላይ ይችው ገጽ ባህሪ “an adventurer in search of treasure,” ትሆናለች ፍለጋዋ አበቃ የፈለገችውን ፍቅርና አፍቃሪ አገኘች በመንገዶቹዋ ብዙ የፍትወት እግሮች ተራምደዋል። ረካች ረኩባት? ግድ ሊሰጣትም ላይሰጣትም ይችላል እያንዳንዱ ነገር ቅድስናም ርኩሰትም አለው በህይወት አጋጣሚ ማርያ የፍቅርንና የወሲብን ቅድስና በመከራ ውስጥ ፈልጋነው ያገኘችው የመከራ መዳፍ ቅድሳን ፈልቀቀች ሃያሲያን ማሪያን አልኬሚስት ላይ እንዳለው ሳንቲያጎ ጀብደኛ ናት ይላሉ የወሲብንም የፍቅርንም ቅድስና ከመከራ አውጥላለችና መከራ ይቅጥላል ከመከራው ሊመለክ የሚችል አንድ ቅዱስ ነገር አንድ ቀን ይወጣል። እዚሁ መጽሃፍ ላይ እንዲህ ብላለች “When I had nothing to lose When I stopped being who I am, I found myself.” መከራ ወደ ቅድስና መውጫ መሰላል የሚሆንበት አጋጣሚ በየታሪኩ ቢፈለግ ታሪክ ይጠፋል?


ጸጋዬ በአፍሪካ ሥነ ጽሁፍ ሰማይ ሥር
ሰውየው የአፍሪካ የቲያትር ታሪክ ተመራማሪ ነው እንደ ደራሲም የገነነ ነው። በዚምባብዌ ሥነ ጽሁፍ ዘረፍ ደማቅ አሻራዎችን ካሳረፉት መካከል ሲጠቅስ የሱ ሥም አይጠፋም ቤተሰቦቹ ሮበርት ምሼንጉ ካቫናግ የሚል ሥም ሰጥተውታል። በሥራ አጋጣሚ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በምጣበት ወቅት ሎሬት ጸጋዬን ተዋወቀው ሮበርት ምሼንጉ ካቫናግ ወደ አገሩ ተመለሰ በቀጣይ ጊዜ ሲመለስ ጸጋዬን አንድ ሆቴል አገኘው ወደ አግሩ በተመለሰ ማግስት ሮበርት ምሼንጉ ካቫናግ “TSEGAYE GEBRE-MEDHIN: LET HIS LIGHT SHINE” የሚል ጽሁፍ በሰባት ገጽ ጻፈ ጽሁፉን አንብቤ ስጨርስ ጋሽ ጽጋዬ በጣም ራቀብኝ ምናቤ ሊቆጣጠረው አልቻለም ምንም እንኩዋ ጋሽ ጽጋዬ በህይወት ባይኖርም ሁለተኑ የአፍሪካ ቀንድ እንቁዎች መንፈሳቸውን ላቀራርብ ብዬ ይህንን ለመጻፍ ኮሚፒተሬን ከፈትኩ። በዚህ ጽሁፍ አብዛኛው በመሃል ከምሰነዝራቸው ጥቂት ሃሳቦች በቀር ሃሳቡ የሚያጠነጥነው “TSEGAYE GEBRE-MEDHIN: LET HIS LIGHT SHINE” በሚለው መጣጥፍ ላይ እንደሆነ አንባቢ ልብ ሊል ይገባል።
ወትሮ እኛ እፍሪካውያን ጣታችን እጅ የፈታው በጠብመንጃ ነው ማለት ይቻላል ዳዴ ስንል አፈር ለመላስ አልታደልንም ለጋ መላሳችን ባሩድ ቀመሰ አፍሪካዊ ጎለመሰም፣ መሪም ሆነ ተመሪ የጦርነት አታሞ ሲደልቅ ጣቱ ለብዕር አይታዘዝለትም ከኪነት ለሚገኝም የነፍስ ሃሴት መንፈሱ እሩቅ ነው። በአጠቃላይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አፍሪካዊ ኪነት የኦግስታቮ ቫሳን የቅኝ ግዛት ትረካን ከማጫወቻ ሸክላው አላወረደም ወደ አገራችን የኪነት ዘርፍ ስንመጣ ምንም እንኩዋ አገሪቱዋ ቀኝ ባትገዛም የጎረቤቶቹዋ ቅኝ የመገዛት መንፈስ ተጭኑዋት እንደቆየ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል። ስለ አፍሪካ ሥነ ጽሁፍ የሚያትቱ ድርሳናትን፣ የግብጽ ጥንታዊ ሥነ ጽሁፍ በስሱ የአረብ ሥነ ጽሁፍ ላይ ተጽኖ አድርጉዋል። ይላሉ አገራችንም በጥንታዊነቱዋ ከዚህ የምትጋራው የስልጣኔ ማውረስ ባህሪ አለ ይሁንና አገራችንን ጨምሮ ሌሎችም የአፍሪካ አገራት በቁዋንቀዋቸው ዘገምተኛ ባህሪ ምክንያት ሥነ ጽሁፋቸው አላደገም ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰለሞን ደሬሳ በአንድ ቃለመጠይቁ ላይ “በግዕዝ አለሳይንስ አልተጻፈም” ይላል።
ከላይ በተነሱት ምክኛቶች የአገራችን ከያኒያን ልፋታቸው አልሰመረም ሮበርት ምሼንጉ በአፍሪካ ሥነ ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያላቸውን ኬንያዊውን ደራሲ ናግዋጊ ዋ ቱንጊዎን ጠቅሶ የአፍሪካ ጽሃፊዎች የቅኝ ግዛት ታሪካቸው እንደፈተናቸው ሰፊ ተነባቢነት ለማግኝት ሲሉ በሌላ ቁዋንቁዋ ለመጻፍ ተገደዋል ይላል። “Still, Tsegaye’s fate is an object demonstration of what an African writer must sacrifice if he writes in his native tongue – fame and love among his people but insignificance in the Anglophone or Francophone international mainstream. Almost all Africa’s best-known writers write in a European language in order to reach a wider readership or audience though there is a slight suspicion that many African writers who write in European languages, write with at last half an eye on their European market – and their publishers probably with a lot more than half.” በእኔ አተያይ ኢትዮጵያ ቅኝ አለመገዛቱዋ ለተውኔና ለግጥም ስራዎቹ ትልቅ መንፈስ የሰጠው ይመስለኛል።
ሃያሲ ቴዎድሮስ ገብሬ ጸጋዬን ከ አዳም ጋር አነጻጽረው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በዳሰሱበት ጥናታቸው ላይ ጋሽ ጸጋዬን እንዲህ ይገልጹታል። “ጸጋዬ ተሰርቶ ያለቀ symbol ይፈልጋል። የጸጋዬ narrative ወይንም national myth ሙከራ በግዙፋን እሴቶች ላይ ለምሳሌ በአባይ፣ በአዋሽ፣ በምኒልክ፣ በዓድዋ፣ በቴዎድሮስና በዘርዓይ ታሪክ ላይ ይመሰረታል። እዛ ላይ ተመስርቶ seriously የሚፈልገውን ይሰራል።” ለእኔጋሽ ጸጋዬ በአሁንችን፣ በሁኔታችን አስቆጥቶት ሁዋላችንን ሊከስትልን በቅርጽ ሊያሳየን የለፋ ይመስለኛል። ዓድዋ ሩቅዋ-የዓለት ምሰሶ ጥግዋ-ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ-ዓድዋ…-ባንቺ ህልውና - በትዝታሽ ብጽዕና ማለቱ ከላይ ለጠቅስኩት አጽንኦት ማስረጃ ይሆነኛል። ሮበርት ምሼንጉ ምን አልባት የቁዋንቁዋ ነገር ይዞት ይሆነንጂ ጋሽ ጸጋዬ ስራዎች ላይ ታሪካዊና ሂሳዊ ምልከታዎቹን ቢያጋራል በአማርኛ ለተጻፉት ማጀቢያ አድርን እናነባቸው ነበር.።
ጋሽ ጸጋዬ በበርካታ አገራት ዘይቤና ቁዋንቁዋ መጻፍ ሲችል ለምን በአማርኛ በስፋት ጻፈ? ለሮበርት ምሼንጉ ሰለሞን ደሬሳ አንድ ዕድሜ ለአንድ ህይወት ላይበቃ አይነት አባባል በሚመስል መልኩ እንዲህ ነበር ያለው“ I have only one life and that life I have dedicated to writing plays for my people in our own language.” በቀኝ የተገዙ የአፍሪካ አገራት ቅኝ የመገዛት መንፈስ መጅ ሆኖ ወደሁዋላ ሲጎትታቸው ጋሽ ጸጋዬ ደግሞ በአገሪቱ ተንሰራፍቶ የነበረው የፊውዳል ስርአት በተለይ በተውኔት ስራዎቹ ላይ ፈተና እንደሆነበት ለለሮበርት ምሼንጉ አጫውቶታል። ስለ ጋሽ ጸጋዬ ለመጻፍ አንድ እድሜ ይበቃል? ገጣሚ ነው፣ እንዳንል ጽሃፌ ተውኔት ነው፣ ደራሲ ነው እንዳንል የታሪክ ተመራማሪ ነው፣ አፍሪካዊ ነው እንዳንል፣ አለማቀፋዊ ነው፣ አለማቀፋዊ ነው ብለን እንዳንዘጋው አዋሽን አረሳውም በአፍሪካ ሰማይ ስር ግን ጸጋዬ እንዲህ ይታወቃል “For Tsegaye Gebre-Medhin Qawasa was a unique polymath, a poet, a writer and an extraordinary man. He deserves an honoured place in the African theatre Hall of Fame.” ሮበርት ምሼንጉ ካቫናግ የአፍሪካ የቲያትር ታሪክ ተመራማሪና ደራሲ


የቀለም ዳር ዘላለም
(ሰለሞንን በምናቤ)

ዕውቁ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰለሞን ደሬሳ በአማርኛ መጻፍ ከመጀመሩ በፊት በፈረንሳይኛና በእንግሊዘኛ ነበር የሚጽፈው እንደ ግሪጎሪያን አቆጣጠር 1969 እ.ኤ.አ “Shifting Gears” የሚል ርዕስ ስጥቶት በከፍተኛ ጥራት ታትሙዋል። ከሆነ ዘመን ቡሃላ በአማርኛ መጻፍ ቀናው መሰል በፈረንሳይኛና በእንግሊዘኛ እምብዛም የጻፈ አይመስለኝም “ዋይ ድምጼ ለሙዚዋ ቢሆን ግጥሞቼን በየ አዝማሪ ቤቱ አዘምራቸው ነበር” ብሉዋል። ሰለሞን ለቃል ትልቅ ትኩረት ይሰጣል። በ1994 ዓ.ም በአሁኑ ኢቢሲ በበፊቱ ኢቲቪ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጠው ቃለ መጠየቅ “ለደራሲ ለጽሃፊ በማንኛውም ቁዋንቁዋ የማይገለጽ ነገር ያለ አይመስለኝም” ያው በተዘዋዋሪ የትም አገር ዘይቤ ቢገለጽ ዋናው የሚገለጸው ሃሳብ፣ ስሜት፣ ፍልስፍና ሳይንስ፣ ይኑር እንጂ ማለቱ ነው። የዚህ ነገር መነሻው ደግሞ ቃል ራሱ ነው።

ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰለሞን ደሬሳ “Shifting Gears” ግጥሙ ላይ ስለቃል በዙ የትተብሰለሰለ ይመስለኛል። ግጥሙን ላላነበበው አንባቢ እንዲመች ለግጥሙ ምናባዊ ስጋ እንስጠው የሚዋኝ አንድ ሰው አለ ሰውዬው በህልም ስውር ተሰፍቱዋል። የእብድ ዝምታ አስጨንቆታል። የቀለም እስትንፋስ ቢተነፍስለት፣ እሚያማምሩ ጣቶች ቢዘረጉ፣ ቀለም ቢፈራረቅ የገጣሚው ስሜት ባዶ ነው። መጨረሻ ላይ እንዲህ ብሎ ነው የሚዘጋው ግጥሙን አንተ ፍቅር ያላወዛህ የጥላቻን ዘላለም የግድግዳ ስዕል የምሰነጣጥቀው በአፍህ ቃል ቀለም ነው።

በርግጥ የሰለሞን “Shifting Gears” ብዙ እንድናስብ የሚያደርገንና ብዙ ሊጻፍበት የሚገባ ግጥም ነው። በምናቤ ወደሁዋላ ተመልሼ አሰብኩ ሰለሞን ይህንን ግጥም እንዲህ የጻፈው ይመስለኛል። ጠባብ ክፍል ነው ብዙ ስዕሎች አሉ እያንዳንዱን ሰዕል እየዞረ ያሸታል ስሜቱ ይቀያየራል። በክፍሉ ውስጥ እንዳለ ስሜቱ ከቀለማቱ ጋር ተደበላለቀ ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ተሰማው ነጭ ጺህሙን በጣቶቹ ነካካ አራት ጊዜ ተነስቶ አራት ጊዜ ተቀመጠ መነጽሩን አወለቀ እንደገና አደረገው ከተቀመጠበት ተነሳና ወደ መጻፊያ ክፍሉ ሄደ ቀለሞቹ፣ ስዕሉ፣ እንደ አለት የጠነከረ ስሜት ተከተለው ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብሎ ብጣሽ ወረቀት አነሳ ትንሽ ቆይቶ ወረቀቱን አየ ምንም አልጻፈም። ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ “In the colourles breath, With grapnel-fingers in an empty colour rack,” የሚል ሁለት መስመር ጻፈ ፓሪስ ናንተር ሰፈር በስፋት የሚከፈተው ሙዚቃ ወደ ጆሮው መጣ ሙዚቃ ምንድነው? ግጥም ምንድነው? ዜማ ምንድነው? ቀለም ምንድነው? ስዕል ምንድነው? ብሎ አይኑን ጨፈነ

ብዙም አልቆየ አይኑን ገለጠ ከናንተር ሰፈር የተከፈተውን ሙዚቃ ተከትሎ ግጥሙን ጨረሰ እንዲህ ብሎ ዘጋው “You whose love never wavered Towards whom I forever crack On the tip of my parched tongue.” አዎ ሰለሞን ልክ ነው አንተ ፍቅር ያላወዛህ የጥላቻን ዘላለም የግድግዳ ስዕል የምሰነጣጥቀው በአፍህ ቃል ቀለም ነው። ግጥሙን እንደጨረሰ በሁዋላ ከክፍሉ ተነስቶ ወጣ። ቅድም የሰማውን ሙዚቃ ተከተለው ዝም ብሎ መራመድ ቀጠለ ከናንተር ወደ ሩልማላምሶ ሰለሞን ደስ አለው ከቀለም ዳር የሆነ ዘላለም ያየ መሰለው ስዕሉ ያልተናገረውን በግጥም እንደተናገረ አሰበ ጥቂት ፈገግ አለ በዛን ምሽት ፓሪስ ላይ ጨረቃ ስላልወጣች ፈገግታውን የተቀበለው ማንም አልነበረም።


የ Betemariam Teshome ጠያይም መላእክት ላይ የተሰሩ የኔን ጨምሮ ሁሉንም ዳሰሳዎች ጋዜጠኛ Reeyot Alemu ቆንጆ አንድጋ ዳሳቸዋለች ዳሰሳዎቹንና የፕሮግራሙን መገኛ ሊንክ ከታች አስቀምጣሉሁ ፕሮግራሙ https://www.youtube.com/watch?v=E-JeOS0e0jY የዳሰሳዎቹ መገኛ https://www.youtube.com/@betemariamteshome..8581


የሰለሞን ናፍቆት
ሰለሞን ደሬሳ ካረፈ እንደ ቀልድ አመታት ተቆጠሩ ስለ ሰለሞን ምን? ይባላል ምንም ሰለሞን ግዙፍ ነው። አስታውሳለሁ ያረፈ ጊዜ ወዳጄ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ እንዲህ ብሎ ነበር “ሰሎሞን ደሬሳ ባለቅኔም፣ ገጣሚም አይደለም፤ ወለልቱ ነው፡፡ የወለልቱ ነፍስ ፈጣን ናት - ካማጠችው ሀሳብ በላይ የምጥ ስሜቷን ለማጋት የምትተኮስ፡፡ ወለሎ የሚገጠም ወይ የሚቃና - በይሁነኝ የሚከረከም አይደለም፤ የሚጠለቅ - የሚቀዳ ነው፡፡ መጥለቅ ደግሞ ከይሁነኝ ለስሜት ይቀርባል፡፡” እውነቱን ነው የሰለሞንን ጥልቅነት ለመረዳት ግጥሙን ማንበበ በቂ ነው። ለዛሬ ሰቅዞ የያዘኝን ከዘበትል ፊቱ አንድ ነጠላ ግጥም እንዳስሳለን ግጥሙ “ስጠብቅሽ ቀርተሽ” ይሰኛል።
በዚህ ግጥም ብቻ ነፍስ ያለው በርካታ ጽንሰ ሃሳብ እናገኛለን እንደ ብርሃን ብልጭ ከሚለው የናፍቆት ስሜት አንስቶ እንደ ጀምበር እስከሚርቀው ናፍቆት በፈካ ውበት ታጅሎ እዝራ እንደሚለው ተናዳፊ ሆኖ ግጥሙ ቀርቡዋል። “ በየማህሌቱ /በየመስጊዱ / በየኢሬፈቻው ጥላ/ ስጠብቅሽ አንጀቴ ደቂቃውን እየበላ/ ጠይም ነበርሽ የጠይም ማለቂያ/ ” ጥርሶችሽ የንጣት መለኪያ [ገፅ፥ 56] በሶስት ቦታ ጠበቃት ሲጠብቃት ጨርቅ ህላዌው ነተበ ይህ የወለሎት አንጉዋ የኢምራን ሻኪን አንድ ግጥም ያስታውሰናል ግጥሙ በአማርኛ ይዘቱ ይሄ ነው። ባትቀር ባትቀር/ ነፍሱዋ የፍቅር ወይን ነበር። ማግባትሽን ከሰው ሰምቼ/ ከ ናት መወለዴን ጨርሼ ረስቼ/ ከሰውነት ርቄ ጭራሽ ተበትኜ/ መልህቄን ለቅቄ በጽልመት ተውጬ/ የፈላ ወርቅ ለጠበል መጣሁኝ/ ክብደቴ ተሰምቱዋት መሬት እንድትውጠኝ [ገፅ፥ 56] ታዋቂው ተዋናይ ካርል ክሪስቲያን ፍሎረስ “How many more days will you wait for that clink--That you'll cross her mind and she'll finally see? People don't think of people as much as we think, But we think of people, so which people are we?” "ስንት ቀን ትጠብቃለህ ያን ድምጽ--ወደ አእምሮዋ ትመጣለህ? በመጨረሻም ታያለች?ሰዎች የምናስበውን ያህል ሰዎችን አያስቡም፣ እኛ ግን ሰዎችን እናስባለን፤ ታዲያ እኛ የትኞቹ ሰዎች ነን?" የጥሩሱዋ ውበት ከናፍቆቱ አይገዝፍም በአንጻሩ ናፍቆቱዋ የሱን ህልውና ከ ጨለማ ያቀላቅለዋል።
ከቆሰለ ልቤ በሱዋ ስሰናበት/ ማእበሉን ቁዋጥኙን ተመስገን እንዳልኩት/ ለጋስ አካላቱዋን ከልቤ እንዳቀፍኩት/ ለሎማንዲ ባህር ድፊት ሰገድኩለት [ገፅ፥ 57] ይህን ግጥም ፓሪስ የተጻፈ ነው። ምን አልባት ግጥሙን በደንብ ያነበበ እንደሚረዳው በዚህ ግጥም የተቀረጸው ናፍቆት ሎማንዲ ባህር ይገዝፋል። በአራእንድ ቢ ዘፈኑ የሚታወቀው ኦሊ You & I በሚለው ሙዚቃ ያለው ነገር ትዝ እነዛ ቀናት ይናፍቁኛል ይህ ስሜት ወደ ጥልቅ ያሰርጠኛል። ኦ ሰለሞን


ራሴን ላጥፋ ወይስ ቡና ልጠጣ ?
[ጥቂት ስለ ድህረ ዘመናይ ህምሞችና ራስን ስለ ማጥፋት]
የውልህ ዘመኑ ተቀይሩዋል ድህረ ዘመናይ ህምም በሰው ልጅ ልብ ውስጥ እንደ አለት ጠንክሩዋል። አንድ ምሳሌ ልንገርህ ለምሳሌ የዚህ ዘመንን ሰው “ኑር ባንተ አለም” ብለህ ልታጽናናው አትችልም እንዴት በለኝ ጥያቄ ይጠይቃል። የኔ አለም የታል? ይልሃል ያው ብለህ አለሙን ብታሳየው እኔ የታለሁ? ይልሃል ስለዚህ እንዴት በዚች ወለፈንድ አለም መኖር እንዳለበት ማወቅ ግድ ይለዋል። የአለም መልክ ምን ይመስላል? ትውልደ አልጀሪያዊው ፈረንሳዊው ፈላስፋ አልበርት ከሙ ”The Myth of Sisyphus” "ሰው ምክንያታዊነት የጎደለው መስታወት ፊት ይቆማል። ሰው ለደስታና ለምክንያት የሚጓጓ እንደሆነ ይሰማዋል። በሰዎች ፍላጎትና በዓለም ላይ በሚፈጠር ምክንያታዊ ያልሆነ ነገር መስታወቱ ላይ ሲያይ ግራ ይጋባል መልኩንም መስታወቱንም ይጠራጠራል።"
አየህ አለም አንተም እንዲህ ነህ ድህረ ዘመናይ ህምም እንዴት ተፈጠረ ካልን አሜሪካዊው ስኮላር ዴቪድ ቢ ሞሪስ ከአመታት በፊት አካዳሚያ ላይ ድህረ ዘመናይ ህምም የሚል ጥናት ይፋ አድርጎ ነበር በዚህ ጥናት ላይ የአውስትራሊያውን ፈላስፋ ካርል ፖፐርን ጠቅሶ እንዲህ ይላል። "All moral urgency has its basis in the urgency of suffering or pain" "የዘመናዊው አለም የሞራል ጥመት ለድህረ ዘመናይ ህመም መፈጠር መሰረት ሆነ" ብለን ለዚህ አውድ እንተርጉመው ሌላ አንድ የዛሬውን አለም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነገር ልንገርህ ”THE HOUSE THAT JACK BUILT” የሚለው ፊልም ላይ የተጠቀሰ ነገር አለ ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ ነው የሚለው "ሰው በዚህ ምድር እውነትን መፈለግ የለበትም ምክንያቱም ብዙ ማሰብ ይጠይቃል ብዙ ማሰብ ደግሞ ... ሞኝ ያደርጋል።"
አንባቢ ሆይ ይቅርታ ይህን ሁሉ የዘበዘብኩት የድህረ ዘመናይ ትልቁ ህምም በዚህ አለም ሞኝ መሆን ነው ልልህ ነው። ሰው ይህን ማስታረቅ ሲከብደው አልበርት ከሙ እንድሚለው ፈልስፍናዊ ራስ ማጥፋትን ይከውናል። በአንጻሩ ስጋዊ ራስን ማጥፋት በራሳቸው ላይ የሚፈጽሙ አይጠፉም በሃገራችን በተደረገ አንድ ጥናት በርግጥ ከ 2000 አመተምህረት ወዲህ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቀንሰዋል ይልና በአገራችን በአመት ስምንት ሺህ ሰዎች እራሳቸውን ያጠፋሉ ይላል።
ከላይ እንዳልኩት ሰው በፍልስፍናም በስጋም ራስሱን ማጥፋተንድለለበትና ከወለፈንድ አለም ጋር መስማማት እንዳለበት አሳቢያን ይናገራሉ ሁለት የአልበርት ከሙ ብያኔዎችን ላንሳና ላብቃ ከላይ "መፈጠር እንደ መሰብሰብ ያለ ነገር ሲሆን መፍጠር መኖር በእጥፍ እንደ መኖር ያለ ነው አበቦችን፣ ወረቀቶችን እሲ ሰብስብ ጭንቀቶችን ብታከማቻቸው ምንም ትርጉም አለው?" ይልና በሌላ መጽሃፉ ደሞ ማለትም ሃፒ ዴዝ ላይ “Should I kill myself, or have a cup of coffee? But in the end one needs more courage to live than to kill himself.” “ቡና ልጠጣ ወይስ ራሴን ላጥፋ ወይስ ቡና ልጠጣ ነገር ግን የሁዋላ የሁዋላ ራስን ለማጥፋት ከሚያስፈልገው ጥንካሬ ለመኖር ጥንካሬ......... ያስፈልጋል” ይህው ነው። ድህረ ዘመናዊውን አለም ለማወቅ ”THE HOUSE THAT JACK BUILT” የሚለውን ፊልም በመጋበዝ ልሰናበት......።




በመከራ ውስጥ ስለመኖር

እስቲ ስለዚህ ፊልም እናውራ በርግጥ ብዙ ሰው አይቶታል ሆኖም የፊልሙ ጽንሰ ሃሳብ በውስጡ ድህረ ዘመናይ አኑዋኑዋራችንን ፍንትው አድርጎ ስለሚያሳይ በዘርፉ ብዙ የተመራመረውን ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊንን እያነሳን ሰው እንዴት በመከራ መኖር እንደሚችል። እንመልከት ኖዌር ፊልም ላይ ገጸባህሪዋ ወይም ማያ ከባሉዋ ጋር ወደስደት ስትሄድ ድንገት ከባልዋ ጋር ትለያለች እሱ በሊላ የስደተኛ መኪና እሱዋ በሌላ በዛላይ እርጉዝ ናት የመኖር ህልውናዋ መፍረስም መደፍረስም የሚጀምረው ከዚህ ቡሃላ ሲሆን መከራዋም ሀ ብሎ የጀመረው በዚህ ሰአት ነው።

ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ቡሃላ የገነነው ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊን ከሚስቱ ጋር እንዲሁም ቤተሰቦቹ ወደ ካምፕ እንዲገቡ ተገደዱ ታሪኩን ያጠኑ እንደሚሉት ቪክቶር ፍራንክሊን ወደ ካምፕ ሲገባ ልብሱ ተነጥቁዋል አሰቃቂ ነበር ይላሉ ከዚህ ተነስቶ ነው ቪክቶር ፍራንክሊን በከባድ ሁኔታ ውስጥም ብንሆን ህይወት ትርጉም አላት የሚለው ለምን እንዲህ አለ? ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊን ሎጎቴራፒን ለአለም አስተዋውቁዋል። ሎጎ ማለት ምንነት ሲሆን ቴራፒ ደግሞ መዳን ማለት ነው። የሎጎ ቴራፒ ሃሳብ ሲጠቃለል የተደበቀን አላማን በመፈለግ መኖር ማለት ነው። ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊን የታላቁን ፈላስፋ የኒቼን አባባል ይጠቅሳል “He who has a why to live can bear almost any how.” ብቻ በካምፕ ውስጥ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ የነበሩ ሰዎችን ያነጋገረው ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊን አራት መንገዶችን ይጠቁማል። “Man's Search for Meaning” በሚለው መጽሃፉ የተብራራ ቢሆንም ቅንጭቤ ላቅርበው

1. ከአጽናፈ አለሙ መነካካት
ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊን ከላይ በጠቀስኩት መጽሃፍ ላይ አንድ ታሪክ አስፍሩዋል ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊን ካምፕ የገባ ቀን ከሁሉም ተለይቱዋል ማንንም አያውቅም ቪክቶር ፍራንክሊን የለበሰውን አውልቆ ሌላ እንዲለብስ ተገደደ የልብሱ ኪሱ ውስጥ አንድ የጁሽ ውዳሴ ያለበት ወረቀት አገኘ አነበበው ለራንክል ሃያል ነበር ይህኔ ነው ሰው ከአጽናፈ አለሙ ፈጣሪ የተነካካ በምንም አይነት ሁኔታ ተስፋ አይቆርጥም ያለው በሌላ ጊዜ ደግሞ ምንም ማንም ሳይኖረው ፍራንክል ሚስቱን፣ ልጆቹን ማሰብ ጀመረ ለመኖር ጥንካሬን አገኝ “Man's Search for Meaning” ላይ እንዲህ ይላል ፍራንክል “Everything can be taken from a man but one thing: the last of the human freedoms—to choose one’s attitude in any given set of circumstances, to choose one’s own way.” "ሁሉም ነገር ከሰው ሊወሰድ ይችላል ሰው ነፃነት የመጨረሻው ስጦታው ነው። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን አንድ ሰው የራሱን መንገድ መምረጥ ሳይኖርበት አይቀርም።" እንደማለት ነው።

2. ነፍስ መጋቢ ስራ መስራት

ዶክተር ቪክቶር ፍራንክሊን በካምፕ ውስጥ እያለ ይጽፍ ነበር ከውጣ ቡሃላም መጽሃፍ ሆኖ ታተም እዚህ ጋር አንድ ታሪክ ላንሳ እውቁ ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰንአ ታፍኖ ወደጨለማ ሲላክ ያልገጠመው ፈተና አልነበረም ከቡዋንቡዋ ጉጥ ጋ አጋጭቶ ራሱን ለማጥፋት አስቦ ነበር ነገር ግ ን እነዛን የጭንቅ ጊዜያቶቹን እስፖርት በመስራት መመጻፍ እንዳሳለፈ "የታፋኑ ማስታወሻ" ላይ ጽፉዋል። ፍራንክል ይህን በተመለከተ እንዲህ ይላል “When we are no longer able to change a situation, we are challenged to change ourselves.” «ሁኔታዎችን መቀየር በከበደህ ጊዜ ራስህን ቀይር» እንደማለት ነው።

3. የምንወዳቸውን ማሰብ

ፍራንክል ሚስቱን ይወዳል በመጽሃፉ “I understood how a man who has nothing left in this world still may know bliss, be it only for a brief moment, in the contemplation of his beloved.” ሲል በመከራ ወቅት የሚወዱትን ማሰብ መከራን ለማለፍ እንደሚረዳ ሲያስረዳ ፍቅር ሃያል ነው እንዲል።

መውጫ

ኖዌር ፊልም ላይ ማያ የመከራ ወቅቶችን ያለፈችው በነዚህ መንገዶች እንደሆን ፊልሙን ያስተዋለ ይረዳል ራሱዋን ልታጠፋ ስትል በማህጸን ያለው ልጅ ተንቅቀሳቀሰ ብዙ ብዙ ማንኛውም መከራ ያልፋል ያልፋል፣ ራሱም ያልፋል ያልፋል ዶስቶየቭስኪ አንድ ጊዜ እንዲህ አለ "የምሰጋው አንድ ነገር ብቻ ነው እሱም ለመከራ ብቁ እንዳልሆንኩ ብዬ" ራስን ለመከራ ማብቃት ትልቅ ክህሎት ነው ምውሰለኝ






መቀንበቢያ

ባይለየኝ ጣሳው የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ባሳተመው የአባይን አፈ-ታሪኮች ጥናት መፅሓፍ ላይ ያሰፈረው አንድ ሐሳብ የአባይ ወንዝ ደራሲዎችና ገጣሚዎች እንዲሁም ሠዓሊዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ይላል። ለሐረር ብዙ ተዘፍኗል። በየአይነቱ ተዚሟል! አዲስ ዜማ ያለው ዘፈን መፍጠር አይቻልም! ግና ሐረር ስትታይ ሐረር ናት! ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊ ባኽዳድ! የምትንቦገቦግ የስልጣኔ አርማና አሻራ! ውስጧ ሲገባ ዓለም ናት! በአንጻሩ ስለ ባህልና ሥልጣኔ ሲወሯ አፍ መፍቻ ቋንቋችን አለመሆኗ ያስቆጫል።


ስድስት ትንግርታዊ የሐረር ቱውፊታዊ ታሪኮች
- ሳሙኤል በለጠ

መነሻ

ጋሽ ዓለማየሁ ገላጋይ ጎንደር የሕልሙ ከተማ ብትሆንበት እንዲህ አለ "ጎንደር የሕልሜ ከተማ ናት፤ ምናልባትም ከልደት በፊት-በፊት የማውቃት፤ ለአንዱ ጀግና አድሬ የተዘዋወርኩባት፣ ወይም በክፋት ያስጨነኩባት …" እያለ ይቀጥላል። እኔም ለሐረር እንዲህ ነው የሚሰማኝ በመንፈስ የነቃች ይመስለኛል። ከዓለማዊ መልክ የሸሸች በመንፈሳዊ ሥልጣኔ ያ' በበች ትመስለኛለች። በሥራ ምክንያት የተለያየ አገር ብሄድም ሐረር እንደ ሄድኩ ስገባ ልቤ ደንገጥ ብሏል። ትመስለኛለች ያልኳት ሐረር ገዝፋ ታየችኝ። ስልጣኔ ከቤት ይጀምራል፤ ጥንታዊነትና ዘመናዊነትን ከጥልቅ ትርጉም ጋር አቅፎ የያዘው ኪነ-ህንፃዊ አሰራሩ/architectural style፣ ቴክኖሎጂ ባልተወለደበት ዘመን የተጠቀሟቸው ለጤና ስሙም የሆኑ ንጥረ-ስሪቶች/materials፣ የእስልምና ኋይማኖትና የሐረሪ ብሄረሰብ መገለጫ የሆኑ ልዩ እሴቶች/values ኪናዊ ስብጥር ከብዙ ጥቂት መገለጫዎች ናቸው። ቤቱ የተቀባው ቀለም ሲታይ ዝምብሎ ይመስላል - ታሪኩ ሲነገር በቀለሙ ውስጥ የቁዛሜ ታሪክ ይዟል። እነዚህ የጥንት ስልጣኔያቸውን የሚናፍቁ የሚመስሉ የቤት ታሪኮች እልፍ ታሪኮችን ይዘው የቤቱ 'ዲካው'(ጣሪያው) ላይ ባሉት የዋንዛ ርብራቦች ቁጥር ልክ ታሪካቸው አይቆጠርም፤ አይቋጭም ።

የሐረሪ ሕዝብን ለመግለጽ ስለተቸገርኩ የባላዝ ሚዲያ አዘጋጅ የነበረው ግሊን ባክ በአንድ ወቅት ያለውን ልጥቀስ "ለአንተ መልካም ነው! ልብ አለህ አይደል? ነጻ መሆን ትችላለህ ግን ልብህን ከአእምሮህ ጋር አጣምረህ ወግ አጥባቂ መሆን ትችላለህ።" (Good for you, you have a heart, you can be a liberal. Now, couple your heart with your brain, and you can be a conservative.)
የሐረሪ ሕዝብ ነጻ ሕዝብ ነው። እዛ ያሉ ነፍሶች ልብና መንፈሳቸው ያ'ወሩ(ስሙም) ናቸው። ከልብ ለልብ የሚኖሩ ለልብ የቀረቡ ነፍሶች ከተማይቱን ሞልተዋታል።

የሥነ ጽሑፍ ኀያሲው ቴዎድሮስ ገብሬ "ቱውፊታዊ ታሪኮች የሰውን ነገረ ፍጥረትና የኅላዌ እንቆቅልሾችን (ontological and cosmological questions) ለተመሰቃቀለው ዓለም ሥርዓት (cosmic order) ለማበጀት የባተለበት እምነታዊና ፍልስፍናዊ ጥበብ ነው" ሲል ቱውፊታዊ ታሪክን ይገልጸዋል። እኔም በሐረር ቆይታዬ ያስደነቁኝን ቱውፊታዊ ታሪኮችን ላስከትል።

1. የሐረር አመሰራረትና ስያሜ

የዛሬይቱ ሐረር ከመመስረቷ በፊት ከአንድ ሺህ አመት በፊት በሰባት ጎሳዎች የሚመሩ በሰባት መንደሮች የተከፋፈለች ነበረች። ዊኪፕዲያ የታሪክ መዝገብ እንደሚለው ሐረር በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በተለምዶ ሼኽ አባድር በሚባሉ በመደበኛ ስማቸው ሸኽ ኡመር አል-ሪዳ (Abadir Umar ar-Rida) በተባሉ ብጹዕ የሐይማኖት አባት ከርሳቸው ጋር አራት መቶ አራት የሐይማኖት አዋቂና መምህራንን በማስከተል የሳውዲ ግዛት ከሆነችው ሂጃዝ ተነስተው የዛሬይቱ ሐረር እንደደረሱ በአፈ ታሪክ ይነገራል።

እነዚህ ሰባት የተከፋፈሉ ስምምነት ያልነበራቸው ጎሳዎች በማሰባሰብ የአንድ ነገድ ግንድ ጎሳዎች የሆኑ አካላት በሐይማኖትም በስነ-ምግባርም መለያየት አግባብ አይደለም በማለት አሰባስበው በማስታረቅ፣ በወንድማዊ ክር በማሰርና በማዋደድ አንዲት ጠንካራ መዲነቱል ሐረር እንደመሰረቱ በሐረር ቃለ ቱውፊት ብሎም በታሪክ መረጃዎች በወርቃማ መልኩ ተጽፏል።

2. የአጥንት ትውፊት

በጥንት ዘመን ሐረር ላይ ሥጋ ከተበላ በኋላ የስጋ አጥንት አይጣልም። ምክንያቱ ደግሞ፤ አንድ፣ አጥንት የመልካም ጂኖች ምግብ ነው፤ ሁለት፣ በአጥንቱ ውስጥ ክፉ ጂኒ(ቆሪጥ፣ አጋንንት) ይኖራል ተብሎ ይታመናል። ስለዚህ አጥንቶቹ ተሰብስበው በጀጎል ግንብ ዙሪያ ይቀበራሉ። የአጥንቱ መቀበር በርካታ ጥቅም አለው አንዱና ዋነኛው ጥቅም ሐረር በምስጥ እንዳትወረር ይጠብቃታል ተብሎ ይታሰባል። ሌላው ዝማሚት(ምስጥ) ወደ ሐርር ግንብ እንዳይገቡ ይከላከላል። ከገቡ ግንዶች፣ ጥንታዊ መጽሐፎች ስለሚያበላሹ የተቀበሩት አጥንቶች እንደ ተከላካይ ሆነው አገልግሎት ላይ ይውላል።

3. የሐረር ጅቦች

ጅቦች በባህሪያቸው የሞተና የበሰበሰ ነገር እንደሚመገብ(Scavenger Animal) እንደሆነ የገባቸው የሐረሪ መንፈሳዊ አባቶች ከሐረር በሮች ልክ 'ወራባ ኑዱል' የተባለውን በር ለጅብ መግቢያና መውጪያ አበጁለት። ጅብም የማይታይ ጅን(ቆሪጥ፣ አጋንንት) ማየት ስለሚችል እነዚህን እንዲሁም በየቤቱ የምግብና የስጋ ትርፍራፊ በልቶ ይወጣል። የሐረር ጅብ በአካል ያለን ፍጡር ስለማይበላ የሐረር መንፈሳዊ አባቶች ጅብን እንደ የቤት ድመትና መሰል እንስሳ አላምደዋል። በሰውኛ መጥሪያ ስሞች ጠርተው በእጅና አፍ ይመግባሉ። በየአመቱም ለጅቦች የሚዘጋጅ ልዩ ገንፎ የማብላት ትርኢተ-ድርጊት/festival አላቸው።

4. ጫት በሐረር

የዛሬን አያርገውና በጥንቱ ሐረር ጫት ጥቅሙ ለተከበረ ድርጊያ ነው የሚውል የነበር። ለስራ፣ ለጸሎት፣ ለኋይማኖታዊ አሰላስሎት/contemplation እንዲሁም ለጠቃሚ የጉልበት ስራ ነበረ የሚቃም። የመቃሚያ ሰዓት ደግሞ ፀሐይ ወጥታ አምስት ሰዓት ሲሆን ቆይታውም ፀሐይ እስኪከር ይሆናል፤ እንዳ'ሁኑ ምሳ በልቶ እስከመፍዘዝ መወዘፍ አልነበረም። ከዛ ገበሬ የሆነ ወደ እርሻው፣ ነጋዴ ወደ ንግዱ፣ የኋይማኖት ሼሁ ወደ ንባብና ወደ ፀሎት ይሄዳሉ። በዛች ሰዓት የቃሟት አንዲህ ፍሬ ጫት እስከ ለሊት ኢሻ(የቀኑ መጨረሻ ስግደት) ድረስ ሃይ/ህያው/ንቁ አድርጎ በማዝለቅ ጠሃይ ጠልቃ ጨለምለም ሲል በድካም ወደ መኝታቸው እንዲያመሩ ምትሃታዊ ጉልበት ይቸራቸዋል።

5. የሐረር ባለከለር ድመቶች

ሐረር ድንቅ የድመት ቃለ ቱውፊት አለ። በፊት የሐረሪ ባህላዊ ቤቶች ከአፈር ነበር 'ሚሰሩት። ሐረር ግንብ ዙሪያ ግንብ ውስጥም ጭምር እባብን ጨምሮ የተለያዩ ተሳቢ እንሰሳት ነበሩ። ስለዚህ እያንዳንዱ የሐረሪ ቤት ውስጥ የሚገኙ ድመቶች ስራ ይህን እባብና አይጦች ለመከላከልና ሌሎች ምስጢራዊ ሚስጥሮችን ያጨቁ ግብሮችን የሚያጎናፅፉ የሚያማምሩ ድመቶች ነበሩ፤ አሁንም አሉ!

6. የማይሞቀው የማይቀዘቅዘው የሐረር አየር

ሐረር ለሰው ልጅ እጅግ ተስማሚ አየር አላት። ሪቻርድ በርተን የተባለ የታሪክ ተመራማሪና ተጓዥ የሐረርን አየር እንዲህ ይገልጸዋል "ሐረር የምትሞቅ የማታቃጥል፤ የምትቀዘቅዝ የማትበርድ አየር(warm but not hot, Cool but not cold)" ያላት ከተማ ናት ይላል። ጥንት ሐረርን የመሰረቱ የሐረሪ በመንፈሳዊ ትምህርትና ጥበብ/ religious wisdom የመጠቁ አባቶች የከተማዋን ቦታ ሲወስኑ ለጤና ጥሩና ተስማሚ አየር እንዲኖራት በማሰብ ሙዳ ስጋ ቆርጠው ዛፍ ላይ ሰቀሉ፤ በነጋታዉ ሲመጡ ስጋው የተሰቀለበት ከባቢያዊ አየር ሙቀት ቢሆን ስጋው ይበላሻል፤ እጅጉን ቀዝቃዛ ከባቢያዊ አየር ካለ ደግሞ ስጋው ይደርቃል። የአሁኗ የሐረር ጂኦግራፊያዊ መገኛ ስፍራ በዚህ ጥበባዊ ስሌት ከብዙ የሙከራ መነሳትና መውደቅ/try and error በኋላ ስጋው ከአንድ ቀን አዳር በኋላ ሳይበላሽና ሳይደርቅ በነበረበት ቆይቶ ምንም ለውጥ ባለማሳየቱ ለሰው ልጆች ተስማሚ አየር እንደሆነ ተምኖበት እዚህ ቦታ ሐረር ትቆርቆር ብለው ሐረርን መሠረቱ!



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

825

obunachilar
Kanal statistikasi