የመጨረሻው ናፍቆት
ካይኔ ዋሻ ተደብቄ ፣ ከል ሳለቅስ
የህጻንነቴን እርጥብ ዝምታ...
በመናፈቅ ባሁን መዳፍ ፣ ስደባብስ
ካይኔ ዋሻ እንዳለሁ
ነፍሴን እጠይቃለሁ?
ናፍቆት ትንሳኤ አለው?
“የናፍቆትን ክራር
በጣትህ ብቃኘው
ይጠዘጥዛል እንጂ
ዜማ አይሆንም ምነው?”
ጌታሆይ
በሰማዬ ላይ ያንዣበበው ፣ እዥ የደመና ቁስል
በጽሃይህ አታጥገው ፣ ላንተ ናፍቆት መቃጥያ ይሆነኛል።
ካሻት ህጻን ማለዳ ፣ የብርሃን ልሃጭ አትትፋ
የጽሃይም እግር ይሰበር ፣ ተስፋም ከማዕከሉ ይጥፋ።
ጌታሆይ
ናፍቆቴን መናገር ፣ ሞት ይወልዳል
የህጻንነቴን ለጋ ዝምታ ፣ መልስልኝ
የናፍቆቴ ትንሳኤ ፣ እሱ ይሆናል
ማን ያውቃል?
ካይኔ ዋሻ ተደብቄ ፣ ከል ሳለቅስ
የህጻንነቴን እርጥብ ዝምታ...
በመናፈቅ ባሁን መዳፍ ፣ ስደባብስ
ካይኔ ዋሻ እንዳለሁ
ነፍሴን እጠይቃለሁ?
ናፍቆት ትንሳኤ አለው?
“የናፍቆትን ክራር
በጣትህ ብቃኘው
ይጠዘጥዛል እንጂ
ዜማ አይሆንም ምነው?”
ጌታሆይ
በሰማዬ ላይ ያንዣበበው ፣ እዥ የደመና ቁስል
በጽሃይህ አታጥገው ፣ ላንተ ናፍቆት መቃጥያ ይሆነኛል።
ካሻት ህጻን ማለዳ ፣ የብርሃን ልሃጭ አትትፋ
የጽሃይም እግር ይሰበር ፣ ተስፋም ከማዕከሉ ይጥፋ።
ጌታሆይ
ናፍቆቴን መናገር ፣ ሞት ይወልዳል
የህጻንነቴን ለጋ ዝምታ ፣ መልስልኝ
የናፍቆቴ ትንሳኤ ፣ እሱ ይሆናል
ማን ያውቃል?