ከልብ ወለድ ባሻገር ባሻገር
”ሀገር ያጣ ሞት ሂሳዊ” ንባብ
ክፍል አንድ
ሳሙኤል በለጠ
አለመታደል ሆነና አንዱን ዘመን ሳናጣጥም ወደ አንዱ አዘመምን ልብ ወለዳችን ዘመናዊ ሆን ስንል ዮሃንስ አድማሱ ዘመናዊ ልብ ወለዳችን በጣት የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነገሩን እንዲህ እንዲህ እያልን በገድምዳሜው ድህረ ዘመናዊ ድርሰቶች ላይ ደረስን ነገሩ እንዲህ ነው። ድህረ ዘመናዊ ድርሰት በሥነ ግጥሙ እነ ሰለሞን ደሬሳና ሌሎችም በድርሰቱ አዳም ረታ ከተዋወቀ ወዲህ መልኩንና ቅርጹን እየቀያየረ አሁን ላይ የደረሰ ሲሆን የአጻጻፍ ይትብሃሉን ወጣት ደራሲያንም እያዘወተሩት መጡ በቅርብ አመታት ለንባብ ከበቁ መጽሃፍቶች ድህረ ዘመናዊ የድርሰት አጻጻፍ ይትብሃልን የደገበረው የሄኖክ በቀለ ለማ ”ሀገር ያጣ ሞት” አንዱ ነው።
ለመሆኑ ድህረ ዘመናዊ ድርሰት ምንድነው? ከዘመናዊ ድርሰትስ የሚለየወ ጠባዩ ምንድነው? የሥነ ጽሁፍ ሃያሲው ሺቫ ኪርካህ ”Alienation and Loneliness of American Postmodern Characters in Salinger’s Masterpiece Catcher in The Rye” በሚለው የጥናቱ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል ”The postmodern texts reveal skepticism about the ability of art to create meaning, the ability of history to reveal truth, and the ability of language to convey reality. All that skepticism led to fragmented, open-ended, self-reflexive stories that are intellectually fascinating but often difficult to grasp. The stylistic techniques of postmodernism include the frequent use of intersexuality, Metafiction, temporal distortion, magical realism, faction, reader involvement and minimalist techniques of reduction, omission and suggestion.” ድህረ ዘመናዊ አጻጻፍ በእነዚህ ጠባዮች ከዘመናዊ አጻጻፍ ተቃርኖ የቆመ እንደሆነ ይነግረናል። ሳሙኤል ቤኬት፣ ኩርት ቮኔጉት፣ ጆን ባርት፣ ሳልማን ሩሽዲና ሌሎች ድህረ ዘመናዊ የድርሰት አጻጻፍ ይትብሃል የሚከተሉ ደራሲዎች ናቸው ይላል።
የሄኖክ በቀለ ለማ ”ሀገር ያጣ ሞት” ከላይ ሃያሲ ሺቫ ኪርካህ የገለጸውን የድህረ ዘመናዊ የአጻጻፍ ይትበሃል መለያ ጠባይ ያለው መሆኑን እንረዳለን magical realism - አስማታዊ እውነታ የሄኖክ በቀለ ለማ በእያንዳንዶቹ ገጸ ባህሪያት እንዲሁም Self-reflexive Stories - የራስ ልዋጤ ታሪኮች አስማታዊ እውነታዎችን ይነግረናል። የህላዌ ስንክሳርን ለመፈከር ይጠይቃል ፍቅር፣ ክህደት፥ ወሲብና መቀማማት፥ ፀፀትና መስዋዕት፥ የትዝታ፣ ሞት፣ ህይወት ተስፋን መቀማት፣ በገጸ ባህሪዎቹ በዱና፣ በሊቀ መኩዋስ፣ በጸሎት በስዕለ፣ የተተወሩ - Plot- በጊዜ ውስጥ የተሰነጉ የተፈቱ፣ ያልተፈቱ፣ የሚያስቃትቱ፣ የሚያስነቡ የሚመስጡ የህላዌ ስንክሳር ናቸው። -Reader involvement- አፍቃሬ አንባቢን ማሳተፍ የድህረ ዘመናዊ የአጻጻፍ ይትብሃል አንዱ መንገድ ነው። ”ሳቁን ተሻምቼ አልጽፍለትም። ታዲያ ዛሬ በምን እዳው? እንደልጆቹ በቻለው ቋንቋ አፍ ላስፈታው። ከዛስ? ነፍስ እስከፈቀደ ይጨመርለታላ ይህ እንዲህ በሚያልፍ ዛሬ ላይ የተቃጣ ቅናት ነው። የቃል ፍቅር እዳው ምን ድረስ ነው?” (ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 200) ሄኖክ በቀለ ለማ በድርሰቱ በእያንዳንዱ መሥመር የአንባቢን ምናብ እየፈተነ ያሳትፋል። በእነዚህና መሌሎች መስፈርቶች ”ሀገር ያጣ ሞት” ድህረ ዘመናዊ ድርሰት ነው ማለት እንችላለን።
”ሰማይ በደመና ጭረት ፊቱ ተዥጎርጉሮ በዋለበት፤ የልጅገረድ ቅንድብ በመሰች ጭረት ጨረቃ በተኩዋለበት፤ በክዋክብት ውቅራት ስግግ ገላውን ባቀፈበት፤ የምድር ብሌን በስልችት ቁልቁል ካፈጠጠበት፤ የሀገር ሰው ሰነፍ ቆሎውን እያሻመደ ኩታውን እየተከናነበ የመከኑ ሕልሞቼን በሚከልስበት፤ ከጣሪያው ሥር ጥላሸትና ጠረን የጠገበ መረባ የተተከሉትን አይኖች በሚጠየፍበት፤ ግዑዛን አፋቸውን በምጥን ሃሌታ በሚፈቱበት፤ ወጣት ለቂሙ መቁዋጫ ቀጠሮ መሚቀጥርበት፤ የሃዋዝ መሰንቆ ሳይታለብ.....”(ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 10) ሁሉም የድህረ ዘመናዊ ሃያሲዎች እኔም የምስማማበት አንድ ነገር አለ ለድህረ ዘመናዊ ድርሰት የቋንቋ አጠቃቀም ቅጥ ራሱን ችሎ ገጸ ባህሪ ይሆናል። (the language style has become a characteristic of the novel) ሄኖክ ይህንን በድርሰት የሞከረ ብርቱ ደራሲ ነው።
”ባለ መሰንቆውን ሐዋዝ ተጫወት ቢሉት....
”ሞት ይቅርይላሉ ሞት ቢቀር አልወድም
ድንጋዩም አፈሩም ከሰው ፊት አይከብድም”ብሎ ነው። አይንህን ያሳየኝ ያሉት።
”ይሄ ምላስህ አንድ ቀን ይጠልፍሃል። የለፈለፍከው እርጥብ ገመድ ሆኖ ያንቅሃል” ብለውት መርቀውታል።(ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 39) ሥነ ጽሁፍ ከተለያዩ የህይወት የህይወት ህላዌ ጥያቄዎች ጋር ትስስር ይፈጥራል የሥነጽሁፍ ዳርዊኒዝም ሊቁ ጆሴፍ ካሮል ”literature deals with death in relation to three specifc themes in human life history: imminent threats to survival, childhood, and pair bonding” የሚል አጽኖት አለው ሥነ ጽሁፍ ከተለያዩ የህላዌ ጣጣዎች ጋር አጣምሮ መጻፍ ለጽሁፍ ፍካሬም ውበትም አውንታዊ ተጽኖ አለው ”ሀገር ያጣ ሞት” በጽሞና ላነበበው የሊቀ መኩዋስንና የሐዋዝን ነገረ ሞት ብቻ ሳይሆን የተዋቡን መቃተት በራስ ለዋጤ ታሪኮች የሚነገሩ ታሪኮች ውስጥ ሀገር የሚያህል የህላዌ ጣጣና ጥያቄ ያገኛል።
ታላቁ ዕዝራ አብደላ እንደሚለው ደግሞ ”በአንድምታ የተለበለብ የቋንቋ ትርታና ንዝረት ነው።” ሄኖክ ገጸ ባህሪን፣ ከህላዌ ጣጣ የህላዌ ጣጣን ከሃሳብ ሃሳብን ከ ግዜ ጋር ጊዜን ከሃገር ጋር አገርን ከህልውና ጋር አሹዋርቦ ነው የጻፈው ይች አገር ግን ሞቱን አልተቀበለችውም ወለፈንዳድ ህላዌአችንን ያሳያል በዕውቀቱ በአንድ ግጥሙ እንዳለው ”መንሳፈፉስ ይቅር እንዴት መስጠም ያቅተዋል ሰው?” ይህ የባይተዋር ገድላችን ነው መሰል ሄኖክ ይሄን ሁሉ አጣምሮ አንድ ተስማሚ አጽኖት ሳልሰጠው ባልፍ ትውልድ ይቅር አይለኝም ሂሴም ውሃ አያነሳም ብዙ ቲዎሪዎች ያሉትና የሥነጽሁፍ ሃያሲው ብራያን ማከል ”POSTMODERNIST FICTION” በሚለው መጽሃፉ ዋቢ ያደረገውን ሃሳብ ላንሳ ልሰናበት ”The skeleton of the layers and the structural order of sequence a literary work of art are of neutral artistic value; they form the axiologically neutral foundation of the work of art in which the artistically valent elements…of the work are grounded”
ክፍል ሁለት ይቀጥላል።