ከአዳማ ወደ ድሬ ዳዋ የሚወስድ መኪና ውስጥ ... ላብ ካቸፈቸፈበት አየር ስር አንዲት ሴት ተቀምጣለች ። ጸጉሯ ተበታትኑዋል። ፊቷ ላይ ማዲያት ጥላውን ጥሏል። ለንቦጩን የጣለው መኪና የሁሉንም ጩኸት አፍኖ ይዟል። ከሁሉም ሰዎች ይቺ ሴት ደመቅ ብላ ትታያለች ። በዛለ ክንዷ ሮዛ የሚል መጽሐፍ ይዛ : በመጽሐፉ መሃል ጠቋሚ ጣቷን ከታ መጽሐፉን ቆልፋዋለች ። ከውልደት እስከ አሁን ያለው ኅዘኗ አካሏን ሰርቷል ? ...2
ሳን ሚጉኤል የጻፈውን 'voices from silence' ን እየባከንሁበት : የልብ - መልኳን እያሰስሁበት : የሴቲቷን አይኖች ለማዬት ቀናሁ ። ታሪክ ድጋሚ ተፈጠረ ። የሰው ቀለሙ በቀን : አካሉም በፀሐይ ይሳላል ። የተናገርነው ጭምር የቃላት ቀለም ነው ። እነዚህ ናፍቆት ይሆናሉ ። አንዳንዴ ቢጫ ጥላ አያጠላም ። ተስፋ ማጣት : ተስፋ አለማዬት---ሕይወት--- ሳይወድ በግዱ ሰው ፈሳሽ ጨለማውን ተግቶ ያጋሳል ። ጥጋብ አይደለም---።
"የት ነው የምትሄደው?"
"ጨለንቆ ! አንቺስ?"
"ድሬ ዳዋ" መርጋት ተደላድሏል በድምጿ ::
"ለሥራ ነው?"
"አዎ ! አንቺስ ?''
"እኔም"
"ምን ትሰሪያለሽ ?"
ዝም .....
መኪናው በፍጥነት ይጓዛል ። መኪና ውስጥ ባሉ ሰዎች ሕመም ተደብቋል ። በወና ህዋ የተንሳፈፉ ቀለማት አርፈውባቸዋል ። በአበባና በአበባ መካከል እንዳለ ፈገግታ ፈገግ ብላ ጥርሷን ገለጠች ።በእርግጥም የስዕልን ርቃቄ ነች ።----
"ምንድነው? የምታነበው?"
"ሳን ሚጉኤልን ታውቂዋለሽ?"
" የሚወራለት ንባብ የለኝም :: አንድ ...አንድ ...ከሁለት አይበልጡም ያነበብኋቸው ። ምን ፃፈ ያንተስ ሰውዬ ?"
"ስለ አርጀንቲናዎች የጻፈው ነው።" ነገር በእንጥልጥል ...
ከንፈሮቿን በአይኔ ሰሳምኩ ...
''ሮዛ ደስ ይለኛል ። ይሄ መጽሐፍ ብዙ ጣእሞች አሉበት ። ቡዙ እጆች ፣ ብዙ ገላዎች ፣ ተነክተውበታል ። አፎች ተጣመዋል ። ድምጾች ሰልለው ፣ ጸጉሮች ጸጥ : ጭጭ : ረጭ : ብለውበታል። ብዙ ሕመሞች ...! ትራስ ላይ ተንሰቅስቀው ፣ ሲያለቅሱም ፡ ሳያለቅሱም ፡ ሳግ ፡ ሲያንቃቸው ጭምር አይበታለሁ... ። አንዳንዴኮ... አንዳንድ አካሎችም : አእምሮ ላይ እንደ በረዶ ይረጋሉ ። ደስ አይልም ? አንዳንድ አካሎች ደግሞ በሌላ ይሰንፋሉ ። ሲያስጠላ ! ይሄ ፍቅር ። የሰው ልጅ ተጫውቶ የሚሸነፍበት ካርታ ። ጦር ያለው ። የሚዋጋ ። የሚያቃጥል ...''3
"ካነበብሁት ቆዬሁ ። በለኮስሽኝ ... እስካልበርድ : እስካልረግብ : በትውስታ ምሪት እንደ አጥቢያ ኮከብ እንዳልበርቅ ፈራሁ ። ሃሃሃ ... "
'' ጥሩ ታወራለህ ። ድምፅህ መግራት አለው ።''
'' መኖርን አታስመስግኝኝ ! ''
.
.
.
ለፀሐይ እንደተተወ ውጥር ቆዳ : የሁሉም ሰው ፊት ሲቃጠል : ዜማም : ግጥምም : እንደ ሌለው ሙዚቃ ነገሮች ዝም ሲሉ : ብልቶች እንቅስቃሴ ሲያቆሙ----- ልቦች በልቦች ሲጎዱ : ቀጭን ሰይጣን ግንባሩ ላይ በለኮሳት እሳት ሲነድ----- በመጽሐፍ መልካ - መልክ ላይ ተዘበራርቆ ተደርሷል። ስለ ቀለም : ማንም... ስለሌላቸው ነፍሶች : ተወግረው እንደጎበጡ አካሎች : እንደተዘበራረቀው ተፈጥሮ : መኪናው ጥሎ እንዳለፋቸው የትላንት መንገዶች : እንዳልተከፈተ ሙዚቃ : ቅላጼ እንደሌለው ሕመም : በውስጥ እንደሚመላለስ : የሚንሴጠሰጥ ጩኸተ - ራስ : የማይያዝ : የማይጨበጥ : የማይደረስበት : የራቀ : በጣቶቼ ልጨብጠው ስል ...ሲያዳልጠኝ : በቃ! በቃ ! ይሄም ...ትንሽ ትንሽ ያማል።''---4
"የት ደረስን?"
"አዋሽ 40"
ካንቀላፉ ትላንቶች ቅዠት ...ቀለም ሲውለበለብ...! ረጋ ካለ የአዋሽ ተንሳፋፊ ሐይቅ : ሙቀት የሚያነጥባቸው ላቦች... በገላ : በገጻችን ሲሰፉ : በቃ! ----አይኗ ተስለመለመ ። ቅንድቧ ስር ላብ አቸፈ---።
"እምልሽ ለምን ሮዛን ወደድሽ ?"
"እኔ እንጃ ! ምናልባት ታሪኬን ስለሚነግረኝ ?።"
" ብዙ ኖርሽለት ለሃዘን ? ተጎናበስሽለት ለደስታ ?"
ምኑ ይነገራል ብለህ ?
እዚህ ጥያቄ ምልክት ላይ! ብዙ አዳፋ ታሪኮች አሉ ። ቢጻፉ የማይጠሩ ። ሸፋፋነታቸው በጫማ የማይሸፈን ። መንገድ የጠፋባቸው የታሪክ እግሮች : አቅጣጫ የሌላቸው : ቀለም የሌላቸው : ስሜት የሌላቸው : ብዙ ምንም የለሾች -----ያልተሞሸሩ ሕመሞች : ማንም ያልካደመላቸው : የበለዘ ወዝ : ጠረን የሌለው ሰመመን : ምጽአት የራቀው በድን : በአይን ቆብ ተጠቅልሎ ያሸለበ አይን : በጨረር የተጠቀጠቀ አይን ... ለህመሟ ስታሸልብ እያያሁዋት ...! ---- ከተከፈተው ጭኗ ጠባሳዋን ማዬት : ለአዋሽ እንደ ገባር የገባ ዕንባዋን ማለቂያውን ማዬት ፈለግሁ ። ኦ ! አንተ አላህ ። ኦ ! ያንተ ያለህ ...።
ከታሪኳ : ከነካካችው ገላዋ : ከነኳት ገላዎች : የሚነሱ ታሪኮች ታሪክ ለመሆን ሲጣጣሩ : ሲጥሩ : ሲፈጉ : ዝም ብለው ዝም አስባሏት ። የወገገ ታሪኳን ሲያርመጠምጡት : በጣታቸው ሲያጨማልቁት---- የማያውቋት : የማታቃቸው : ደሟን : ደም ግባቷን : ከደምስሯ ሰርገው ሲጠቡት : አያውቁ ይሄን መከራ---- አያውቁ ይህንን ሕይወት ---- ልስልስ ሞትና ---ከራስ መለየት ነው የሕይወት ኋላና ፊቷ ።
"እኔ እምልሽ ድሬ ዳዋ ለምን ነው ምትሄጅው!"
"ቁልቢ ነኝ"
" ኧረ ? ዘመድ ጥዬቃ ? ወይስ... ?"
" አይ ! ለንግስ... ስዕለት አለብኝ ። ዘቢብ መልኬን : ፀጋ ወዜን አደርሳለሁ ። "
" ስለ ቀደስሻት ቀኔ : ሌሊቶቼን ሰዉቼ እጎናበስልሻለሁ ። ሃሌታን እወጣልሽም ዘንድ አስብሻለሁ ። ''
'' ሃዘን ተቃመስን አይደል ? በደስታህ በኩል ተጋደምኩ ?''
'' የዕንባ መና የሕይወት ችሮታም ነው :: ''
ከተሳፈርኩበት ወረድኩ :: የሳን ሚጎኤልን መጽሐፍ ጨርሼ እጄላይ ተዝረክርኳል :: ጨረቃ ... ከርቀት ተቀበለችኝ ። ባለንጀራዬ ከሩቅ ጨረቃዋን ቀድሟት ይመጣል። የምናየው የማይታየውን ቀለም ነው ? የምናየው የኛ ቀለም ነጸብራቁ አይናችን እንዳልሆነስ ? የደም ዝውውራችን የተደበቀ ሌላ ቀይ ቀለም ይሰጣል ። የኖርነው ዛሬ : የዛሬ ቀለም ነው ። የናፍቆት ቀለሙ - መለያዬት ነው ? የተለዬኋትን ? የተነጠልኳቸውን አሰብሁ ።
ዞር ብዬ መኪናውን አየሁት ። የተጫነበት ሃሳብ እንደሚያንገዳግደው : ወደ ቀኙ : ወደ ግራው እንደሚያስዘምመው ይሆናል ::
1.The color introduced by daylight ግጥም ፓሬ
2.ግራ ገብ በሆነ ዓለም አንዳንዴ ክምችት(restኸ mass) በሐዘን ሊፈጠር ይችላል አካልም
3. እንቅልፍ አሸለብ አረጋት የሚዘንበው የኃዘን ዝናብ ቆመ
4.የመንገድ ኃሳቦቸ
6.የሚቀጥ[...]