ስሜትን በግጥም dan repost
....ረሳሁት ያልኩት ነገር በጊዜ ቆይታ እየተመላለሰ ያንገዳግደኛል። በስንት ፍጭት ገነባሁት ያልኩት ማንነቴን እንክትክቱን ያወጣዋል። እራሴን የማዘዉ እኔ ልሁን አልያም ሌላ አንዳች ሀይል አላውቅም። ግራ መጋባት ውስጥ ነኝ ምክንያቱም ነኝ ብዬ የማስበውን አይደለሁምና። እሳቤዬ ሌላ ድርጊቴ ሌላ። አለኝ ብዬ የማስበው ማንነት የለኝም ያለኝን ማንነት አልፈልገውም። ምን እየተካሄደ እንደሆነ መረዳት አልቻልኩም። ማነኝ? ምንድነኝ? አእምሮዬ ያዘኛል? ወይስ እኔ ነኝ የማዘው? የሱ ነኝ? ወይስ እሱ የኔ ነው? አላውቅም። የማውቀው ነገር ቢኖር ያለፍቃዴ የሚመራኝ ከኔ በተቃራኒ መስመር ላይ ያለ ማንነት እንዳለ ነው። እውነቱን ለመናገር ውስጤ ካሉት ማንነቶች የትኛው እኔ እንደሆንኩ አላውቅም። ብቻ........ሌላውም እንደኔ ግራ ገብቶት ይሆን?........ከሀሳቧ ተመለሰች። ያገባደደችውን ምግብ ጨርሳ አስተናጋጁ ሂሳብ እንዲያመጣላት በእጇ ምልክት ሰጠችው፤ አመጣላትም። አየችው እንደገና ሌላ ሀሳብ....ለኔ ድርጊት ለምን ሌላው ሂሳብ ይሰራልኛል? ያገኘሁት እና የምከፍለው ዋጋ ሚዛናዊ ይሁን አይሁን ከኔ በላይ ማን ሊያውቅ ይቻለዋል?......በሀሳብ ውስጥ ሆና ከቤቷ ደረሰች። ሀሳቧን ባትደርስም.......
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ