ስሜትን በግጥም dan repost
ሰላም፣ሰው፣ጤና ሁሉም ሞላልኝ። ነገር ግን አንቺ ጎደልሽ። ያንቺ መጉደል እኔን አጎደለኝ። ዱኒያ ብትሞላ እኔ ከጎደልኩኝ ምን ሊረባኝ?...ታስታውሻለሽ ለመጨረሻ ጊዜ ስንገናኝ ህመማችንን በምን እንደብቀው ስልሽ የሰጠሽኝ ምላሽ "አንተ በፅሁፎችህ እኔ በጥርሶቼ" እንደዛ ስትዪኝ አምኜሽ ነበር። ሞከርኩ ሞከርኩ ግን አልሆነልኝም። ህመሜን ለመደበቅ ፅሁፎቼ በቂ አልሆኑም። አንቺስ እንዴት ነው ህመምሽን በጥርሶችሽ መደበቅ ሆኖልሻል? ከሆነልሽ እባክሽ ነይና አስተምሪኝ። ጥርሶቼ እህል ከማላመጥ የዘለለ ፋይዳ የማይሰጡ ከሆኑ ሰነባበቱ። አንድ አፍታ ከባልሽ እቅፍ ተነጠይና ሳቅን ካልሆነም ፈገግታን አስለምደሽኝ ከደረቱ ትሰየሚያለሽ። መቼስ ለኔ ስትይ ቅፅበታዊ ብርድ ቢመታሽ ቅሬታሽ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ሀኑኔ የኔ ህመም የኔ ጤና የኔ መሪር የኔ ጣፋጭ ሀኑኔ የኔ ሳቅ የኔ ሀዘን የኔ ጉድለት የኔ ሙላት እንዴት ውብ አርጎ ፈጠረሽ? እንዴትስ የምታሳሺ ነሽ? እንዴት የማትረሺ ሆንሽ? ሀኑኔ ህይወቴ ሀኑኔ ሞቴ።
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ