የህልሜ በር ቁልፍ
(በእውቀቱ ስዩም)
ከመንገዷ ሸሸሁ
በማትውልበት ዋልሁ
በማታመሽበት፤ ሰፈር ውስጥ አመሸሁ
ፎቶዋን አክስየ
ፊት የሌለው ምስል በላዩ ላይ ስየ፥
“ይደምሰስ ስራዋ
ይወድም አሻራዋ ፥
የሰደድ ነበልባል እንደበላው ሰፈር
የመታሰቢያዋ አመዱ ይሰፈር
ወግ ታሪኳ ያክትም
ከንግዲህ በሁዋላ
እንኳን ወደ ቤቴ፤ ወደ ትዝታየ፥ ድርሽ አትላትም”
ብየ ፎከርኩና አልጋየን አነጠፍኩ
የሰራ አከላቴን፥ እንደ ጃንጥላ አጠፍኩ
አበባ ይመስል ፥ጉልበቶቼን አቀፍኩ፤
ታድያ ብዙም ሳይቆይ፥ በእንቅልፌ ስረታ
ኮቴዋን አጥፍታ
እንደ መንፈስ ገባች
ከትራሴ ግድም ከተማ ገነባች፤
ነግቶ ብንን ስል ፥ ያ ሁሉ ሙከራ
ከንቱ እንደ ሆን ገባኝ ፤ ሳይገድሉ ፉከራ
ሳይጥሉ ቀረርቶ
የህልሜ በር ቁልፍ ፥ መዳፏ ላይ ቀርቶ::
(በእውቀቱ ስዩም)
ከመንገዷ ሸሸሁ
በማትውልበት ዋልሁ
በማታመሽበት፤ ሰፈር ውስጥ አመሸሁ
ፎቶዋን አክስየ
ፊት የሌለው ምስል በላዩ ላይ ስየ፥
“ይደምሰስ ስራዋ
ይወድም አሻራዋ ፥
የሰደድ ነበልባል እንደበላው ሰፈር
የመታሰቢያዋ አመዱ ይሰፈር
ወግ ታሪኳ ያክትም
ከንግዲህ በሁዋላ
እንኳን ወደ ቤቴ፤ ወደ ትዝታየ፥ ድርሽ አትላትም”
ብየ ፎከርኩና አልጋየን አነጠፍኩ
የሰራ አከላቴን፥ እንደ ጃንጥላ አጠፍኩ
አበባ ይመስል ፥ጉልበቶቼን አቀፍኩ፤
ታድያ ብዙም ሳይቆይ፥ በእንቅልፌ ስረታ
ኮቴዋን አጥፍታ
እንደ መንፈስ ገባች
ከትራሴ ግድም ከተማ ገነባች፤
ነግቶ ብንን ስል ፥ ያ ሁሉ ሙከራ
ከንቱ እንደ ሆን ገባኝ ፤ ሳይገድሉ ፉከራ
ሳይጥሉ ቀረርቶ
የህልሜ በር ቁልፍ ፥ መዳፏ ላይ ቀርቶ::