በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ታማኝ የሆነ ቅዱስ አባት አባ በአሚን በሰማዕትነት አረፈ ።
እርሱም በደቡብ ግብጽ በእስሙናይን አውራጃ ለሀገረ ቴርሳ አቅራቢያ ከሆኑ ከሐፂብ ተወላጆች ወገን ነው ለአንድ ባለጸጋም በጅሮንድ ሆኖ ሳለ ስለ ንጽሕናውና ስለ ቅድስናው በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ሆነ የባለ ጸጋውም ሚስት አባ በአሚንን እጅግ የምትወደውና የምትተማመንበት ሆነች ።
እርሱ ግን የዚህን ዓለም ፍጻሜ አሰበ የባለጸጋውንም አገልግሎት ትቶ ወደ ገዳም ሒዶ መነኰሰ ባለጸጋውም መሔዱን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም ይዞ አባ በአሚን ወዳለበት በአንድነት ሔዱ ወደ እርሳቸው እንዲመለስም ለመኑት እንዲህም አሉት ከአንተ እንለይ ዘንድ ከቶ አንችልም ስለዚህ አንተውህም አሉት ።
አባ በአሚንም እኔ ራሴን ብፅዓት አድርጌ ለእግዚአብሔር ሰጥቻለሁ እኮን አላቸው ይህንንም ሲሰሙ ከእርሱ በመለየታቸው እያዘኑ ተትውት ተመለሱ ።
ከዚህም በኋላ ስለ ጌታችን ብዙ መከራዎችን ተቀበለ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ዲዮቅልጥያኖስ ያሠራቸውን እሥረኞች ሁሉ ቆስጠንጢኖስ እንዲፈቷቸው አዘዘ ጌታችንም ለአባ በአሚን ተገለጠና ከሰማዕታት ጋር እንደቆጠረው አስረዳው።
@sebhwo_leamlakne