ታኅሣሥ ፳፰/28
በዚችም ዕለት መቶ ሃምሳ ወንዶች ሃያ አራት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ።
እሊህም ቀድሞ ከሀዲያን ነበሩ የእንዴናው መኰንን የከበረ ሶርያዊ ጳውሎስን በሚያሠቃየው ጊዜ ከዚያ ነበሩ ሲአሠቃየውም ይመለከቱ ነበር መኰንኑም ችንካሮችን በእሳት አግለው ዐይኖቹን እንዲአወልቁ አዘዘ ። ይህንንም ባደረጉበት ጊዜ ዐይኖቹ ወለቁ ከወህኒ ቤትም ጣሉት ። በማግሥቱም እሊህ ሰዎች ሊያዩት በሔዱ ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ድኖ ጤነኛ ሁኖ አገኙት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖታልና።
ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው እጅግ አደነቁ ጣዖቶቻቸውም ምንም መሥራት እንደማይችሉ አስተዋሉ ። የክርስቲያኖች አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ አወቁ ወደከበረ ጳውሎስ ሒደው ሰገዱለት እንዲጸልይላቸውም ለመኑት እርሱም ባረካቸው እግዚአብሔር እምነታችሁን ተቀብሎ ከሰማዕታት ጋር ይቊጠራችሁ አላቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ራሶቻቸውን ቊረጡ ብሎ አዘዘና ቈረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።