ለመወለዱ ጥንት በሌለው አስቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር በመለኮቱ ከአብ በተወለደ ዳግመኛም እኛን ለማዳን በኋላ ዘመን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በእግዚአብሔር ልጅ እናምናለን የቀኑ ቀጠሮ ሲደርስ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከድንግልም ተወለደ
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ነው እርሱም የባሕርይ አምላክ ነው። መለኮት ቢያድርበት በጸጋ የከበረ አይደለም ሥጋን በመንሳት ሰው የሆነ እርሱ ብቻ ነው በመለኮት የእግዚአብሔር ልጅ ነው አምላክም ነው እርሱ ወልድ አንድ ብቻ ነው።"
#ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ምዕራፍ 23÷ቁጥር 2 እና 7
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን አደረሳችሁ በዚህ ቀን ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት የታረቁበት ከኖሎት ጋር የተወደደ ምስጋናን ያቀረቡበት ነው እኛም ከዋዜማው ጀምረን በእግዚአብሐር ቤት በመቅደሱ በመገኘት ጌታ በተወለደ ሰዓት በዛ ከነበሩት እንደ አንዱ በመሆን በውዳሴ በቅዳሴ በማኅሌት እንድናሳልፍ ፤ ከዛ ስንመለስ ደግሞ እንደ ባለ እምነት በጾም መሰንበታችንን አስበን አበላላችን ማስተካከል እንዲሁም ለተቸገሩ በማካፈል በዓሉን እንድናሳልፍ አምላክ ይፍቀድልን።
መልካም በዓል
@sebhwo_leamlakne