ጥር ፲፫ /13/
በዚችም ቀን አባ ነካሮ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ሰው ሳያውቀው በሥውር የሚጋደል ሆነ እርሱም ከምንጣፉ በታች እሾህ ይጐዘጕዛል ጤና አግኝቶ እንዳይተኛ ነው በቀንና በሌሊትም ለጸሎት ይተጋ ነበር።
ከትሑትነቱም የተነሣ የበር ጠባቂ አደረጉት። በዚያም ገዳም በመንፈስ ቅዱስ የተሠወሩ ነገሮችን የሚያይ ባሕታዊ መነኰስ አለ በአንዲትም ሌሊት በሕልሙ በከፍታ ቦታ ላይ ቁሞ አየ ከበታቹም ፍሬው በየዓይነቱ የሆነ አትክልት አለ ወንዞችም ከበውታል አባ ነካሮም በመካከላቸው ሁኖ በወዲያና በወዲህ ያጠጣቸው ነበር።
ያ መነኰስም ወንድሜ ነካሮ ሆይ ይህ አትክልት የማን ነው አለው አባ ነካሮም እኔ የተከልኳት ናት ብሎ መለሰለት መነኵሴውም ከፍሬዋ ትሰጠኝ ዘንድ እሻለሁ አለው አባ ነካሮም ሦስት የሮማን ፍሬ ቆርጦ ሰጠው በልብሱም ቋጠረው።
በነቃም ጊዜ እነዚያን የሮማን ፍሬዎች አገኛቸው ወዲያውኑ ወደ አባ ነካሮ ሔደ ከበር ቁሞ አገኘውና ወንድሜ ነካሮ ሆይ በዚች ሌሊት አይተኸኛልን አለው እርሱም አዎን አይቼሃለሁ ሦስት የሮማን ፍሬዎችን ሰጥቼህ የለምን አለው። በዚያንም ጊዜ ያ መነኵሴ ወደ ገዳሙ ሔዶ የሆነውን ሁሉ ለአበ ምኔቱና ለመነኰሳቱ ነገራቸው እነዚያንም የሮማን ፍሬዎች አሳያቸው መነኰሳቱም ከአባ ነካሮ ቅድስና የተነሣ አደነቁ ያን ጊዜም የበጋ ወራት ነበረና የሮማንም ጊዜው አልነበረምና።
በዝቅተኛ ማዕረግ ላይ ስለአደረጉት መነኰሳቱ አዘኑ በከፍተኛም ማዕረግ ሊያደርጉት ሽተው ወደርሱ በሔዱ ጊዜ አጡት ታላቅ ኀዘንንም አዘኑ ከዚህም በኋላ በዚች ዕለት እንዳረፈ መጻተኞች ነገሩአቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@sebhwo_leamlakne