❗️ ኢትዮጵያ ለሱዳን 15 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ❗️
ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ የሚሆን 15 ሚሊየን ዶላር መለገሷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሱዳን አጠቃላይ ህዝብ 64 በመቶ የሚሆነው ድጋፍ ይፈልጋል ፡፡
በሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ የሚመክር የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ በአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤በሱዳን ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ እያደረጉ ላሉት ጥረት አመስግነዋል።
ጉባኤው የሱዳንን ቀውስ ለማስቆም በተለይም በረመዳን የጾም ወቅት የተኩስ አቁም እንዲደረስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ለሱዳናውያን እንዲደርስ ለማስቻል የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በበኩሏ ተጨማሪ 200 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሰጥታለች።
በጉባኤው የኬንያው ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ቢን ናህያን አልናህያን፣ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተካፍለዋል።