❗ በሬክተር ስኬል 6.0 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ ተከሰተ ❗
ከመተሐራ ከተማ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ላይ በሬክተር ስኬል 6.0 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ዛሬ አርብ ምሽት 5 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ላይ የደረሰው ርዕደ መሬት፤ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ከተመዘገቡት ሁሉ በመጠን ከፍተኛው ነው።
የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ንዝረት “በጣም ጠንካራ” ሆኖ የተሰማው በመተሐራ ከተማ ይሁን እንጂ መዲናይቱን አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ ከተሞችን ማዳረሱን የአሜሪካው የምርምር ተቋም ገልጿል። የርዕደ መሬቱ ንዝረት በአዋሽ ከተማ “መጠነኛ” እንደነበር ያመለከተው ተቋም፤ በአዳማ፣ ሞጆ፣ ቢሾፍቱ እና ደብረ ብርሃን ከተሞችም በተመሳሳይ መጠን መከሰቱን ጠቁሟል።
በመተሐራ እና አዋሽ ከተሞች አቅራቢያ ያሉ አካባቢዎች ባለፉት ወራት የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ ሲከሰትባቸው የቆዩ ናቸው።