❗አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል 28 ቢሊዮን ብር ፈጀ
የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ከ28 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ተነግሯል።
የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ሲሳይ ገመቹ እንደገለጹት፣ ከዚህ ውስጥ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በባለአክሲዮኖች የተከፈለ ካፒታል ነው።
ማዕከሉ በምስራቅ አፍሪካ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ የሚመደብ ሲሆን፣ ሁለት ትላልቅ አዳራሾች እና ስምንት ትናንሽ አዳራሾች አሉት። በተጨማሪም በዙሪያው የሚገኙ ስድስት ህንፃዎች ወደ 1000 አልጋዎችን ወደሚይዙ ሆቴሎች እየተቀየሩ መሆኑ ተገልጿል።
ወደ 2000 ገደማ መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው ይህ ማዕከል 50 የንግድ ድርጅቶችን ማስተናገድ የሚችሉ የንግድ ቦታዎችም አሉት ተብሏል።
በቀጣዮቹ ሶስትና አራት ወራት 10 ተቋማት ዝግጅቶቻቸውን ለማካሄድ ቦታ ማስያዛቸውን ዋና ስራ አስኪያጁ መናገራቸውን የዘገበው ኢፕድ ነዉ::
@seledadotio
@seledadotii