☄️የባንክ ተሽከርካሪ በመገልበጡ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ተበተነ
የሶርያ ማእከላዊ ባንክ ተሽከርካሪ በመገልበጡ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ መበተኑ ሳያንስ የበተነውን እንደ እቃ ለመሰብሰብ ባካባቢው የነበሩ ሰዎች እንዲተባበሩት ማድረጉ እያስገረመ ነው።
ከአመታት ጦርነት በኋላ የመንግስት ሽግግር ላይ የምትገኘው ሶርያ ማእከላዊ ባንክ የሆነ ተሽከርካሪ አንድ ጎማው ፈንድቶ የመገልበጥ አደጋ ሲገጥመው በውስጡ ይዞት የነበረው በሚሊየኖች የሚቆጠር የሶርያ ፓውንድ መበተኑ ተዘግቧል።
አሽከርካሪው እንዳልተጎዳ የተገለፀ ሲሆን። እዚም እዚያ የተበተነውን ገንዘብ ለመሰብሰብ ባካባቢው የነበሩ ሰዎች መሳተፋቸው አጀብ አሰኝቷል።
በምስሉም ላይ የታሰረ ገንዘብ ጨምሮ የተበተነውን የሶርያ ፓውንድ ሰዎች ሲለቅሙ ይታያል።
ከሶርያ የወጡ ዘገባዎች እንደገለፁት ገንዘቡ ለሰራተኞች ደሞዝ ለመክፈል ሲጓጓዝ የነበረ መሆኑ ተዘግቧል::
@seledadotio