⚡️በአዲስ አበባ ከተማ 18 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ ሊቀርብ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፤ በጥቅሉ 18 ሄክታር ስፋት ያላቸው 427 ቦታዎችን ለሊዝ ጨረታ ሊያቀርብ ነው። በመዲናይቱ ዘጠኝ ክፍለ ከተሞች የሚገኙት እነዚህ ቦታዎች፤ ለመኖሪያ እና ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸው ተገልጿል።
በከተማይቱ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ዝግጅት እና ባንክ ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ ለጨረታ የሚቀርቡት ቦታዎች “በተለያየ አግባብ ወደ መሬት ባንክ የገቡ ይዞታዎች” ናቸው። በአሁኑ ዙር ጨረታ በቦሌ እና ልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የመሬት ይዞታዎች እንዳልተካተቱ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ለጨረታ የሚቀርቡት ቦታዎች ዝርዝር፤ በነገው ዕለት ታትሞ በሚወጣው “አዲስ ልሳን” ጋዜጣ ማግኘት እንደሚቻል የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህንን ተከትሎ የጨረታ ሰነድ ሽያጩ “ከእጅ ንኪኪ በጸዳ መልኩ” ከመጪው ሰኞ መጋቢት 1 እስከ መጋቢት 12 ድረስ ባሉት ቀናቶች የሚከናወን መሆኑንም ጠቁሟል።
@seledadotio