⚡️ሁሉም ወንድ ዜጎቿ ወደ ወታደራዊ ስልጠና
ፖላንድ ሁሉም ወንድ ዜጎቿ በወታደራዊ ስልጠና ውስጥ እንዲያልፉ የሚያደርግ ረቂቅ ህግ ለፓርላማው አቀረበች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ ረቂቅ ህጉን ለፓርላማው ባቀረቡበት ወቅት በሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና እንዲሰጥ ያስችላል የተባለው ዕቅድ ዝርዝር በመጪዎቹ ወራት ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
እቅዱ ወታደራዊ ስልጠና የሚያገኙት ወንዶች በቀጥታ መከላከያ ሰራዊቱን የሚቀላቀሉ ሳይሆኑ በግጭት ወቅት ብቁ ወታደራዊ ቁመና ተላብሰው መሰለፍ የሚችሉበትን ክህሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።
ፖላንድ በአሁኑ ወቅት 200 ሺህ ወታደሮች ያሏት ሲሆን በአቅራቢዋ ከሚገኙ ሀገራት አንጻር አነስተኛ ነው የተባለውን የሰራዊት ቁጥር ወደ 500 ሺህ ለማሳደግ አቅዳለች።
@seledadotio