❗የአለም ዋንጫ ተሳታፊ አገራት ወደ 64 ከፍ ለደረግ ነው
የአለም እግር ኳስ ማህበር ፊፋ በ2030 የአለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሀገራትን ቁጥር ወደ 64 ለማሳደግ እያጤነ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡
ባሳለፍነው ረቡዕ በጀመረው የእግር ኳስ ማህበሩ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ኡራጓይ ያቀረበችው ሀሳብ ተቀባይነት ካገኘ ከማህበሩ አባላት አንድ አራተኛው በአለም ዋንጫ እንዲሳተፉ እድል ይፈጠራል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ተከታታዮች እና ተወዳጅነት ያለው የአለም ዋንጫ በየአራት አመቱ በተለያዩ ሀገራት አዘጋጅነት ከ1930 ጀምሮ ለ22 ጊዜ ተካሂዷል፡፡
በ18 የተለያዩ ሀገራት አስተናጋጅነት የተካሄደው ውድድር ከጊዜ ወደጊዜ ከተሳትፎ እና ከአካታችነት ኮታ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ይነሱበታል።
@seledadotio