❗️የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብርና ታክስ በተጨማሪ በሌሎች ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ ተገለፀ
የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ፎረም በከተማው ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ከባድ ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን ገልጿል። ፎረሙ የባለሀብቶችን ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የባለአብቶች ፕሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ለካፒታል እንደገለጹት፣ ባለሀብቶቹ ያላግባብ ድርጅቶቻቸው መታሸግ፣ መፍረስ፣ መነጠቅ (መቀማት)፣ ሥራ እንዲያቆሙ መደረግ፣ ያላመኑበትን ከፍተኛ ግብርና ታክስ ለማስከፈል ማስገደድ፣ የባንክ አካውንታቸው መታገድ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ወይም እንዳይገቡ እየተደረጉ ነው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በስልክ ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረስ፣ የማያምኑበትን አሰልቺና ተደጋጋሚ መዋጮዎች መጠየቅ፣ እንዲሁም ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳይከውኑ ማዋከብ፣ የብድር አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ያለማግኘት እና የመሳሰሉት ችግሮች እየደረሱባቸው መሆኑን ሰምተናል ብለዋል።
ይህን ተከትሎ ፎረሙ ከመጋቢት 01 እስከ 27 ቀን 2024 ዓ.ም ድረስ የከተማውን ባለሀብቶች ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል መዘጋጀቱንና ባለሀብቶችም መረጃቸውን በሰነድ በማቅረብ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።
የባለሀብቶቹ ቅሬታ ከተሰበሰበ በኋላ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ችግሮቹ እንዲፈቱ ፎረሙ እንደሚሰራ አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ተናግረዋል።
@seledadotio