⚡️የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ከፑቲን ጋር ለመነጋገር ወደ ሩሲያ ይጓዛሉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛ ዊትኮፍ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዩክሬን ስላለው ጦርነት ለመደራደር በዚህ ሳምንት ወደ ሩሲያ እንደሚጓዙ ዋይት ሀውስ ማክሰኞ አረጋግጧል፡፡
ክሬምሊንም ልዩ መልእክተኛው በዚህ ሳምንት ሞስኮን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አስታውቋል፡፡
የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እየተጓዝን ነው ብለን ተስፋ እናደርጋለን። እናም ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ በዚህ ሳምንት ወደ ሩሲያ እንደገና በማቅናት ከቭላድሚር ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ይቀጥላሉ" ብለዋል።
ትራምፕ ከሦስት ዓመታት በላይ የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም በዚህ ሳምንት ሩሲያ እና ዩክሬን ከስምምነት ላይ ሊደርሱ የሚችሉበት "በጣም ጥሩ ዕድል" እንዳለ ሰኞ መናገራቸውን አናዶሉ አስታውሷል፡፡
ሚያዚያ ሶስት ፑቲን እና ዊትኮፍ ከዩክሬን ጋር ስላለው ግጭት አፈታት ዙሪያ 4 ሰአት ከ50 ደቂቃ የፈጀ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው ፡፡
@seledadotio