Bahiru Teka dan repost
🚫 ምቀኝነትን ተጠንቀቅ
ምቀኝነት የልብ በሽታ ሲሆን አላህ ለባረያው የሰጠውን ፀጋ እንዲወገድ መመኘትና ለዚህም አስባብ ማድረስ ነው ። የዚህ አይነቱ ምቀኝነት በክፋት የመጨረሻው ደረጃ የደረሰው አይነት ሲሆን መጨረሻ ላይ የሚጎዳው ባለቤቱን ነው ። ምክንያቱም የአላህን ውሳኔ ለመቀየር መታገል ስለሆነ አይሳካምና ። አላህ ከባሮቹ ለሻው በሚሻው ነገር ይለየዋል ወይም ስኬታማ ያደርገዋል ። ይህ ማለት በሰዎች እይታ ነው ምክንያቱም የመጨረሻው ስኬት ከጀሀነም ተጠብቆ የጀነት መሆን ስለሆነ ። ይኼኛውን ስኬት ደግሞ ከአላህ ውጪ የሚያውቀው የለም ። ነገር ግን በምቀኝነት በሽታ የተለከፈ ሰው ይህን ፀጋ በሚያይ ጊዜ ውስጡ በምቀኝነት እሳት ይነዳል ። ከዚህ በላይ ምን አይነት ጉዳት ይኖራል ።
ምቀኝነተ በሁሉም ላይ ሊኖራ የሚችል አስቀያሚ ባህርይ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ታግለው ይደብቁታል ። ግልፅ አያደርጉትም ለዚህም አላህን በመፍራት ይታገዛሉ ። የተበላሸ መንፈስ ያላቸው ወራዶች ግን ከላይ ለመግለፅ በተሞከረው መልኩ የአላህን ውሳኔ ወይም መሺአ ለመቀየር ይታገላሉ ። እንቅልፍ ያጣሉ ፣ ይብከነከናሉ ፣ ጨጓራቸውን ይልጣሉ በዚህም የዱንያ ላይ ቅጣት ያገኛሉ ።
የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ እንደ አይጥ ነው ። አይጥ ጥሩ ነገርን ከስር እየቦረቦረች ለማጥፋት ትዳክራለች ። ይሁን እንጂ ሀሳቧ ሳይሳካ የወጥመድ እራት ትሆናለች ። የምትያዘውም አንገትዋ ወይን አፏ ነው ።
ምቀኝነት መጀመሪያ የጀመረው ኢብሊስ ነው ። በአባታችን ኣደም ላይ በመመቅኘት ። አላህ አባታችን ኣደምን ከጭቃ ከፈጠረው በኋላ ለመላኢካዎች ስገዱለት አላቸው ። መላኢካዎችም የጌታቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ሰገዱ ። ከእነርሱ ጋር የነበረው ኢብሊስ ግን አልሰግድም አለ ። እንዳይሰግድ የከለከለውም ምቀኝት መሆኑን እንዲህ ብሎ መሰከረ : –
« وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ قَالَ أَأَسْجُدُ لِمَنْ خَلَقْتَ طِينًا »
الإسراء ( 61 )
" ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ወዲያውም ሰገዱ ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ፡፡ «ከጭቃ ለፈጠርከው ሰው እሰግዳለሁን» አለ ፡፡ "
« قَالَ أَرَأَيْتَكَ هَٰذَا الَّذِي كَرَّمْتَ عَلَيَّ لَئِنْ أَخَّرْتَنِ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَأَحْتَنِكَنَّ ذُرِّيَّتَهُ إِلَّا قَلِيلًا »
الإسراء ( 62 )
«ንገረኝ ይህ ያ በእኔ ላይ ያበለጥከው ነውን
እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስህተት በእርግጥ እስባቸዋለሁ» አለ ፡፡"
ኢብሊስ ሊሰግድ የከለከለው ሁለት ነገር ነበር ። ኩራትና ምቀኝነት ። ኩራቱን ከጭቃ ለፈጠርከው ልስገድ ወይ በማለት ገለፀው ። ምቀኝነቱን ደግሞ ይህ ነውን ከኔ ያስበለጥከው በማለት ገለፀው ። በዚህም ከአላህ እዝነት የተባረረና እስከቂያማ የሚረገም ሆነ ።
ምቀኝነት አላህ ለባሪያው የሰጠውን ፀጋ እንዲፃረር ያደረገው ሰው በመፃረሩ ልክ ከአላህ እዝነት የመራቅና የመረገም ድርሻ አለው ።
አላህ በዱንያ ላይ በምቀኝነት እሳት ከመንደድ ይጠብቀን ።
አንገብጋቢ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ
https://t.me/bahruteka