ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


እንኳን ደህና መጡ ወደዚህ ቻናል
የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥምና ስነፅሁፎች ከእራሳችንና ከገጣምያን ተሰብስበው የምናደርስበት ስሜታችንን የምንገልፅበት አውድ ነው።
ግጥማቹን ሌላ ችሎታቹን ለማጋራት የምትፈልጉ ላኩልን✍️

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ዕቡህ_ብዕር dan repost
በብላቴና ላይ አምላክ ተገለጠ
‎ሟች የተባለው ነፍስ ከሞት አመለጠ
‎በመከራው ሁሉ ሰሪዋ አልተዋትም
‎ያድነኛል አለች አላሳፈራትም !

ማዕዶትዬ ከነበረባት Cancer ድናለች 🥹
አያቹ ግን አይደል የእግዚአብሔርን ስራ ! አያቹ አይደል ግን በምንም ውስጥ ብንሆን እንደማይተወን....እግዚአብሔር ይመስገን.

አማልጅኝ ያለቻት ማርያም አቀፈቻት
በሰው ማይቻለውን እርሷ አሻገረቻት
✨

ያመነችው አምላክ አላሳፈራትም

ከዚህ በላይ ምናገርበት ቃል የለኝም.....ንጉሥ ይዘን ለባሪያ አንስገድ ሊያድነን የታመነው ከበራችን ነው ✨

[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel


ዕቡህ_ብዕር dan repost
#ፀፀት_ያንባት

የ 2019 የመጀመሪያ ግጥሜ ነው ✨
ልብ የፃፈው ግጥም ነው....
.
Inspired By True Story
የተኖረ ፣ እየተኖረ ያለ ፣ የሚኖር


.
ስለ ፆታዊ ፍቅር አይደለም
.
[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel


ዕቡህ_ብዕር dan repost
ሰላም እንዴት ናቹ ✨ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እናም ውድ ቤተሰቦች የራሴን ትንሽዬ የ T-Shirt Brand ጀምሪያለሁ " ሙሉወርቅ | Muluwerk Designs "😊
.
እና Channel ከፍቻለሁ ገባ ገባ እያላቹ ቤቴን መርቁ ORDER ማድረግ የምትፈልጉም ORDER አድርጉ ምትፈልጉት ሁሉ አለን CUSTOM ORDERም እንቀበላለን ✨
.
ቤቴን መርቁ ጅማሬዬንም ፍፃሜንም አምላክ ይባርክ🙏


THIS IS THE CHANNEL : @muluwerkdesigns






የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች dan repost
"ስትጣሉ እንዴት ናችሁ?"
(simple - story )

አባቷን
"ፍቅር ምንድነው" አለችው

ማሰብ አላሰፈለገውም።

"ፍቅር ማለት
ፍቅር በጠፋበት ጊዜ የምታሳይው መልካምነት ነው።"

"ማለት"

"ከምትወጂው ሰው ጋር ስትቀያየሙ የምታሳይው ባህሪ ነው ፍቅር።"አላት

"ጥያቄዬ ገብቶሀል?" አለችው

"የምትወጂው ሰው ሲያናድድሽ ምን ታረጊዋለሽ ነው ዋናው።
ታንቋሽሺዋለሽ?
ትንቂዋለሽ?
ለፈጣሪሽ ትነግሪዋለሽ? ወይስ ለሰዎች ታሚዋለሽ?
ወይስ ትበቀይዋለሽ ? ወይስ  በልብሽ ይዘሽው ትቆይዋለሽ።
ወይስ እንኳስ ፍቅርሽን እንደኳስ ጠልዘሽ በሰው ዘንድ ቆንጆ ታሪክ ፈጥረሽ"የልክ ነኝ" ጎል ለማስቆጠር ትጥሪያለሽ? ወይስ በብልሃት ታልፊዋለሽ?"

ተቆጣች።
"ከተጣላን ከተቀያየምን ብንስ ባረገው? ካስቀየመኝ ደጋግሞ ካስኮረፈኝ ምን አቆየኝ?"

ሊመክራት ሳይሆን ሊነግራት አቀፋት።

"ልጄ በደጉ ጊዜ መውደድማ መልስ ምት እንጂ ፍቅር አደለም።
ፍቅር ማለት አብሮሽ ያለው ሰው የማትወጂውን ባህሪ በሚያሳይሽ ጊዜ የምሰጪው የመውደድሽ መልስ ነው።
ሲስምሽማ መውደድ ተፈጥሯዊ ነው።
ሲያናድሽ መውደድ ግን ፍቅር ነው።
አንቺ ስታናድጂው የሚሰጠው ግብረ መልስ ፍቅር ይባላል"

አቀረቀረች።
"ሁሌ ፍቅር እንዳለን እንደምንዋደድ በምን አውቃለሁ"

"ስትጣሉ በምትመላለሱት ነገር:: "

"እኔ ምልሽ?"

"አቤት አባዬ"

" አንቺና እጮኛሽ
ስትጣሉ እንዴት ናችሁ"

መልሷ አስፈራት!

(elias shitahun)




ቶጳዝዮን dan repost
ትንሣኤሽን ልየዉ

ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣
በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ።

ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣
ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ።

ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣
ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ።

ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣
አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ።

ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣
ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ።

እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣
ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ።

ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣
በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ።

እንኳን አደረሳችሁ🙏

✍ዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn


ዕቡህ_ብዕር dan repost
‎ብታጭ ለምስራች ታበስረኝ ብትመጣ
‎ስለ አለማመኔ
‎እንደ ዘካርያስ ዲዳነት ነው የኔ ዕጣ
‎ይኩነኒ አላልኩም እንደ እመአምላክ
‎ከአምላክ ፊት የሚቆም ቢላክልኝ መልዓክ
‎ታንኳ ተሰዶልኝ ማህበሉን ማለፊያ
‎እኔን ሚያሳስበኝ ወጀቡን መቅዘፊያ
‎ገብርኤል ገብርኤል መልዓከ ራማ
‎ለደረቀ ልቤ ቃሉን ለተጠማ
‎ላላመነ ነፍሴ ገድሉን እየሰማ
‎ድረስለት ፈጥነህ! እርዳው አለማመኔን
‎ለውጥልኝ ስሜን !
‎


[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel


Check Out! 👇👇👇👇

https://vt.tiktok.com/ZSXDGbJQk/


ሰው ሲሞት ብቻ ሳይሆን በቁሙም አበባ ይሰጠዋል እዘዙ 😊😁




ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ ገላሽን ይንካና
ወዮለት ሰማዩ
ወዮለት ደመና ።

ወፍ አይዘምርልሽ
ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ ።

ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ ።
እኔ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ ።

ክነፍ በዪኝ ልክነፍ
እረፍ በዪኝ ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።

By Hab Hd
@topazionnn
@topazionnn


ዕቡህ_ብዕር dan repost
>
ስትል ጠየቀችኝ !

መጨረሻዬ ምንም ሆነ ምን ለአምላኬ የማቀርበው አንድ ተማፅኖ ይኖረኛል!

>

በማርያም አንድ ጊዜ መታቀፍን ! በማርያም አንድ ጊዜ መነካትን ! በማርያም አንድ ጊዜ ልጄ መባልን ! በማርያም አንድ ጊዜ መዳሰስን ! ተማፅኖዬ ይሄ ነው !

>

አቅፋ ለገሃነም እንደማትሰጠኝ አውቃለሁ! በእሷ ተዳስሼ ሲዖልም ብገባ ጠረኗ ገነት ሆኖ ያቆየኛል!

[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel


ዛሬ የ ስሜትን በግጥም Channel Owner የሆነችው አ....ፊት ቤዛ......ድ......ማ.... ልደት ነው 😁😁😁

አንቺ የግጥም አርበኛ
አንቺ የስንኝ ጦረኛ
እሰይ እልልል እንኳን ተወለድሽ 😁😂😂

መወለድሽን ብጠራጠርም መልካም ልደት
.
.
የዕድሜሽ ጉዳይ እየተጣራ ነው 🙏



✨ መልካም ልደት በሏት ✨

@semetnbegtm


Check out this TikTok I posted! 

https://vt.tiktok.com/ZSQKKP8tt/


ዕቡህ_ብዕር dan repost
#ከተውሽኝ_ቦታ_ላይ

እኔ እዚያው ነኝ !

[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel


ቶጳዝዮን dan repost
ሰላም ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ።በቶጳዝዮን መወያያ ግሩፓችን ላይ የግጥም ወጋችን ለረጅም ጊዜያት ተቋርጦ እና ተቀዛቅዞ እንደነበር ይታወቃል።
ዛሬም እንደተለመደዉ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ የግጥም ወጋችን ይጀመራል።ሀሳባችንን በግጥም መልክ እንገልፃለን።
ያልተቀላቀላችሁ ገባ ገባ እያላችሁ።የተቀላቀላችሁ ወዳጅ ጓደኞቻችሁን Add እያደረጋችሁ ጠብቁን።😊😊🙏
https://t.me/topazionnn_gp


ቶጳዝዮን dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn


Ålem poêⓂs🎀🌎(ስነ-ግጥም) dan repost
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨  ፨፨፨፨፨፨፨
እንዳበባ~ቅጠል
እንደ ክረምት~ጠል
እንዳለቀ~ከሰል
እንደ ጢሰ~ሰንደል

     ክፍተት እያበጁ
     በተስፋ እያጃጁ

            የካብናቸው ሁሉ
            ቀስ ቀስ እያሉ

       በዝምታ በደል
       ተነጠሉን አይደል?!:፧:

[ዓለም]

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.