የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ መቅረቡን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ Capital ዘገበ ።
የውጪ ምንዛሪ ለውጡን ተከትሎ ከግምት ውስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ ቀረበ ።
መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ የነበረውን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ቢያደርግም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋማት ግን ተጨማሪ ክለሳዎች እንዲደረጉ እየጠየቁ መሆኑን ካፒታል ተረድታለች።
የሚኒስትሮች ም/ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን ያፀደቀ ሲሆን ይህም ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።
አገልግሎቱ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያዉ እስከ 200 ሜጋዋትስ ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ድጎማ እንደሚያደርግ ገልጿል ። ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል ቢባልም የተደረገው ጭማሪ በዓመት ውስጥ 122 በመቶ ደርሷል።
ይሁን እንጂ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር በተገናኘ እንደ ዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምን (አይ.ኤም.ኤፍ) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ አጋሮች የተለያዩ ድጋፍ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ መንግስት ያፀደቀውን የታሪፍ ጭማሪ በድጋሚ እንዲያጤነው መጠየቃቸውን ነው ለማወቅ የተቻለው። (Capital news)
@sheger_press