#ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ካሉ ከሶስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት የመጨረሻው አረጋወ መንፈሳዊ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ የጻፈው ታላቁ ገዳማዊ ጻድቅ አባት አረጋዊ መንፈሳዊ ወይም ዮሐንስ ሳባ ነው፡፡ ይህ ታላቅ አባት እየቀደሰ እያለ በተገለጸለት ታላቅ ምስጢረ ምክንያት ነበር ዓለምን ትቶ የመነነው፡፡ እግዚአብሔር በዓለም ሆኜ ይህን ካሳየኝ ከዓለም ብሸሽ የበለጠ ለእርሱ እቀርባለሁ ብሎ፡፡
ገዳማውያን አባቶቻችን እንዲህ ናቸው ወደ ፈጣሪያቸው ለመቅረብ ዓለማዊ ክፋት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ መገለጥም ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ ገዳማትን ስንደግፍም የእነዚህን አባቶች በረከት ነው የምናገኘው፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፣ ታዲያ አረጋዊ መንፈሳዊ በየጊዜው በዓለም ላለው ለታናሽ ወንድሙ መንፈሳዊ ደብዳቤ ይጽፍለት ነበር፡፡ ዓለምን እንዲተው ስላስወሰነው ምስጢር፣ ስለነበረበት፣ ስላለበት፣ በአጠቃላይም ስለ ገዳማዊ ሕይወት ነበር የሚጽፍለት፡፡
እነዚህን #”ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ” በሚል ርዕስ የሚጻፉ ደብዳቤዎች እኔ ሳልሞት ለማንም እንዳታሳይ ብሎ ቢያዘውም ወንድሙ ግን በመጽሐፍ መልክ ለማጻፍ ደብዳቤዎቹን ለጸሐፊ ሊሰጣቸው ሲል አጣቸው፡፡ ከአስራ ስንት ዓመታት በኋላ ግን ደብዳቤዎቹን መጀመሪያ ያስቀመጣቸው ቦታ አገኛቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ወንድሜ ሞቷል ብሎ አለቀሰ፡፡ በረከቱ ይደርብንና ይህን ታላቅ ጸጋ የታደለው አባት ነው እንግዲህ ራሱን በትሕትና የዱር አውሬ ብሎ የሚጠራው፡፡
ገዳማውያን አባቶች መሻታቸው አንድ ብቻ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ለሀገርና ለሕዝብ መጸለይ፡፡ ታዲያ ገዳማቸውን እናጽና፣ ድጋፍ እናድርግ ስንል በሌላ አባባል በረከት እንፈስ እያልን ነው፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444