አዲሱ አዋጅ‼️
በአዲሱ የንብረት ማስመለስ አዋጅ "አንድ ሰው ያለው ንብረት እና የነበረው ገቢ ካልተመጣጠነ ወደ ፍርድ ቤት ከማምራቱ በፊት በቅድመ ክስ ስርአት እንደሚጠየቅ" ፍትህ ሚኒስትር አስታወቀ‼️
የንብረት ማስመለስ አዋጅን በተመለከተ የአዋጁን ዓላማ፣ መሠረታዊ ይዘቶች፣ እንዲሁም ቀጣይ አተገባበር በተመለከተ የተፈጠሩ ብዥታዎችን ለማስተከከል በሚል ፍትህ ሚኒስትር መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም፤ በኢትዮጵያ ይህ ህግ ከመውጣቱ በፊት በወንጀል የተገኘ ሃብት ማስመለስን በተመለከተ ራሱን የቻለና ወጥ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ ያልነበረ በመሆኑ በሕግ ማስከበር ሂደት ክፍተት ፈጥሮ ቆይቷል ብሏል።
የፍትህ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ ቀደም ሲል የንብረት ማስመለስ አዋጁን በተመለከተ ያለ ህግ ቢኖርም ብዙ ህጎችን ያካተተ እንዳልነበር ገልፀዋል።
ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ በቅድመ ክስ ሂደት ማንኛውም ሰው ጉዳዩን እንዲያስረዳ የሚቀርቡ ጥያቄዎች እና አቤቱታዎች የፍርድ ቤቶች የሥነ ሥርዓት ሕጎችንና መርሆዎችን ተከትለው ማጣራት እንደሚደረግባቸው አንስተዋል።
አቤቱታ የሚቀርብባቸውም ሰዎች በሕጉ መሰረት ያላቸውን ማስረጃዎች የማቅረብ በፍርድ ቤት ዘንድ ቀርበው የመደመጥ መብታቸው እንዲከበርላቸው ይደረጋል ብለዋል። (Ethiofm)
@sheger_press