🙏🙏🙏❤️❤️❤️
ተመስገን.........
በሶሻል ሚዲያ ንቅናቄ ከ 12,000,000 ብር በላይ የተሰባሰበ ቢሆንም አሁንም ገዳሙ ድጋፍ ይፈልጋል"
በማዕከላዊ ጎንደር ሐገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው ይህ ገዳም፣ ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት እጅግ ድንቅ ተዓምር ያለበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም ቢሆንም መነኮሳቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር ተጋርጦባቸው ይገኛሉ።
በአንድ በኩል አካባቢው በርሃማ በመሆኑ በበጋ ወቅት ለከፍተኛ ድርቅ ይጋለጣል፣በዚህም ምክንያት ምንም ዓይነት አዝዕርት አይበቅልበትም፣ይህን ተከትሎ ቀደም ሲል ድጋፍ ያደርጉ የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ሳይቀር ለገዳሙ ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ተቸግረዋል።
ገዳማዊያኑ የሚቀምሱት እህል፣የሚለብሱት ልብስ በመጠኑ የተሟላላቸው ቢሆንም ከጾም፣ ጸሎት መልስ ስጋቸውን የሚያሳርፉበት በዓት (ቤት) የላቸውም። በአንድ ደሳሳ ጎጆ በዓት ውስጥ ለሶስት ለአራት የሚያድሩበት በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ዉስጥ ይገኛሉ።
በዚህ ገዳም የሚገኙ ገዳማዊያን ዛሬም ከጸሃይ፣ ከብርድ፣ ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር እየተፈተኑ የሚገኙ በመሆኑ፣ ገዳማዊያኑን ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገው፣ በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፣ ገዳሙም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት፣በሐገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት በመሰራት ላይ ይገኛል።
እነዚህን የታቀዱ ለገዳሙ አስፈላጊ እና መሰረታዊ የሆኑትን የልማት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ገቢ ለማሰባሰብ የሚረዱ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ለመጠቀም ጥረት ተደርጓል።
ከነዚህም ውስጥ፦ ገዳሙ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የሚገልጹ እና የሚያሳዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እንዲሁም ትሁፊት በጠበቀ መልኩ፡
❖ በቴሌቪዥንና ራዲዮን ማስታወቂያዎችን በማስተላለፍ ሕብረተሰቡ መረጃዉ ኖሮት የተቻለውን ድጋፍ እንዲያደርግ
❖ በማሕበራዊ ሚዲያ ማለትም፡ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክ፣ በቴሌግራም፣ በኢንስታግራምና ሌሎችንም በመጠቀም ለታቀዱት የልማት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ገቢ ለማሰባሰብ ጥረት ተደርጓል።
በዚህም እስካሁን 11,000,000.00 (አስራ አንድ ሚሊዮን) ብር የሚያህል የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም 1,200,000.00(አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር የሚሆን የአይነት ድጋፍ ማሰባሰብ ተችሏል።
ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 11(አስራ አንድ) ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን በነዚህ ጊዚያት በመጀመሪያው ምዕራፍ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።
ከተሰሩ ስራዎች መካከል ፡-
❖ የእናቶች በዓት ወይም ቤት በጥሩ ሁኔታ ተሰርቷል።
❖ 170 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ ለእናቶችም ለአባቶችም ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረው ቦታ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ለገዳማዊያን እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን ተደርጓል።
❖ በአካባቢው ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት ያልነበረ ሲሆን አሁን የሶላር መብራት ተሟልቶ የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል።
❖ ቤተ-እግዚአብሔር ወይም ማዕድ ቤት ተሰርቷል፤ የሚያስፈልጉ ሙሉ ቁሳቁሶችም ተሟልተዋል።
❖ ገዳማዊያኑ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸውን የምግብ አቅርቦት ችግር እና የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
❖ ለገዳማዊያኑ የእደ-ጥበባት ውጤቶችን ማምረቻ ሼድ ግንባታ ተከናውኗል እንዲሁም የሸማ ስራ ሙያ እንዲሰለጥኑ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፣ ለስራው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች እና የጥሬ እቃ ግብዓቶችም ተሟልተዋል።
❖ የሻማ እና የጧፍ መስሪያ ማሽን ግዢ ተከናውኗል።
❖ አካባቢው በተደጋጋሚ በድርቅ የሚጠቃ በመሆኑ ለገዳማዊያኑ የተሻለ ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
❖ ወደ ገዳሙ የሚያደርስ 8 (ስምንት) ኪሎ ሜትር ደረጃ አንድ የጠጠር መንገድ ሥራ ተሰርቷል።
❖ የእናቶች የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ተከናውኗል።
❖ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል የሲምንቶ ማቡኪያ ማሽን፣የብረታ ብረትና የእንጨት መስሪያ ማሽነሪ ግዥ ተፈጽሟል።
❖ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የገዳሙ ይዞታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ያልነበረው በመሆኑ የገዳሙ ህጋዊ ይዞታው እንዲረጋገጥለት ተደርጓል።
❖ ገዳማዊያኑ እየሰሩ ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዲያመነጩ ለማድረግ በማሰብ በሃሙሲት ከተማ የሸቀጣ ሸቀጥ እና የንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ተከፍቶ ወደ ስራ ተገብቷል።
❖ ለግንባታ የሚውል በሃሙሲት ከተማ 30 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግስት በሊዝ በመውሰድ በዚህም የአብነት ት/ቤት ፣ አለማዊ ት/ቤት እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ በተጨማሪም ሌሎችም ለገዳማዊያኑ አስፈላጊ የሆኑ የልማት ስራዎች የሚሰሩበት ይሆናል።
የልማት ስራዎች ከተጀመሩ አጭር ጊዜ በመሆኑ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም ከዚህ በተሻለ ፍጥነት መስራት እንዳይቻል የተለያዩ ተግዳሮቶች አጋጥመዋል፡፡
❖ በገዳሙ ውስጥ ስራ የሚሰራባቸው ቀናት ውስን መሆን፤ ማለትም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ገዳማዊያኑም የሚያከብሯቸው በዓላት ሲጨማመሩ በወር ውስጥ የሚሰራባቸው ቀናት ከ 4 (አራት) – 14 (አስራ አራት) የሚሆኑ ቀናት ብቻ ናቸው።
❖ በግንባታ እቃዎች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚስተዋል የዋጋ ልዩነትም አንዱ ችግር ነው።
❖ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ተጠቃሽ ሲሆኑ
❖ ከሚዲያው አካባቢ በተለይም ቲክቶክ አንዳንድ ቲክቶከሮች ፣ የገዳሙ አባቶችን ሆነ የቤተክርስቲያን መዋቅር ምንም አይነት መረጃ ሳይጠይቁና ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በይመስለኛል ብቻ፣ የገዳሙንም የተከታዮቻቸውንም ክብር በማይመጥን መልኩ ተገቢና ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን ማሰራጨት የሚሉት ከብዙዎቹ ተግዳሮቶች ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው።
እስካሁን የተከናወኑ ስራዎች በተለይም የእናቶችን ችግር በመቅረፍ ደረጃ ጥሩና አስደሳች ቢሆንም በአባቶች በኩል ገና ብዙ ስራዎች ይቀራሉ፡፡በመሆኑም በቀጣይ በትኩረት ከሚሰሩ ስራዎች መካከል፡-
❖ የአባቶች በዓት ግንባታ ሥራ
❖ የአባቶች ቤተ እግዚአብሔር ግንባታ ሥራ
❖ የአባቶች የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ
❖ የእንጨት እና የብረታብረት ውጤቶችን ማምረቻ ሼድ ግንባታ ሥራ፣
❖ የእህል መጋዘን ግንባታ ሥራ
❖የቅዱስ ሚካኤል ህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ሥራ
❖ የአብነት ት/ቤት ፣ ዓለማዊ ት/ቤት እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ ግንባታ ሥራ
❖ የጸበልተኞች ማረፊያ ቤት ግንባታ ሥራ እንዲሁም
❖ የውሃ እና መብራት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ በቀጣይ ከሚሰሩት ስራዎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በቀጣይ ለሚሰሩት የልማት ሥራዎች ማከናወኛ የሚሆን ድጋፍን ለማሰባሰብ በቀጣይም የተለያዩ መርሀ-ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል።
ለአብነትም፡-
❖ ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ምዕመኑ ከገዳሙ በረከት እንዲያገኙ እንዲሁም ገዳሙን እንዲጎበኙ የጉዞ መርሃግብር ተዘጋጅቷል።
❖ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ-ግብር በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሚከናወን ይሆናል።
❖ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያ በተገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉባኤ ይኖራል፤