❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን #ጠምህዋ_ከሚባል_አገር_ሰዎች ለሆነች #በ12_ዓመቷ በከሀዲው ንጉሥ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ፍልፍልያኖስ በሚባል መኰንን እጅ በጊንጦች እፋኝቶችንና እባቦችን ሰብስበው በዳውላ ውስጥ ጨምረው በዚህ ሰማዕትነት ለተቀበለች #ለቅድስት_ምህራኤል_ለዕረፍት_በዓል፣ ለታላቋ ሰማዕት ለከበረች #ለቅድስት_እምራይስ_ለዕረፍቷ በዓልና በገድል ለተጠመደ የሴት ፊት ሳያይ ለኖረ ለከበረ አባት #ለአባ_አርከሌድስ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከከበረ ሕፃን #ከቅዱስ_ቂርቆስ_ማኅበር_ከሆኑ_አራት_ሽህ_ሠላሳ_አራት_ጭፍሮች በሰማዕትነት ከዐረፉና ከቅዱስ ዱማቴዎስ ወንድም ከከበረ #ከቅዱሴ_መክሲሞስ_ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_እምራይስ፦ ይቺም ብፅዕት በክርስቶስ ሃይማኖት ለጸኑ ለከበሩ አባቶች ልጅ ናት ፈሪሀ እግዚአብሔርንም እየተማረች አደገች። በአንዲትም ዕለት ውኃ ልትቀዳ ወደ ወንዝ ስትወርድ ስለ ክርስቶስ የታሠሩ እሥረኞችን አየች እነርሱም ጳጳሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት ናቸው ከእርሳቸውም ጋር ስሟን ይጽፍ ዘንድ መዝጋቢውን ለመነችው መዘገባትም ወደ ከሀዲውም መኰንን ወደ ቊልቁልያኖስ አቀረባት። እርሱም ለጣዖት ትሰግድ ዘንድ ብዙ ነገር ሸነገላት እምቢ ባለችም ጊዜ ቸብቸቦዋን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ከተባባሪዎቿም ጋር ምስክርነቷን ፈጸመች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና የሰማዕታት በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_ምህራኤል፦ የዚችም ቅድስት ወላጆቿ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ክርስቲያኖች ናቸው የአባቷም ስሙ ዮሐንስ የሚባል ቄስ ነው እናቷም ኢላርያ የምትባል ደግ ናት። ነገር ግን ልጅ ስለሌላቸው ስለዚህ እያዘኑ ወደ እግዚአብሔር ይለምኑ ነበር ከብዙ ዘመንም በኋላ ይህችን የከበረች የተቀደሰች ልጅ ተሰጠቻቸው ስሟንም ምህራኤል ብለው ጠርዋት። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሆናት ጊዜ በላይዋ በአደረ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ ድንቆች ተአምራቶችን መሥራት ጀመረች።
❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በተነሣ ጊዜ ወደ ባሕር ዳርቻ ወጣች መርከብም አግኝታ በላዩ ተሳፈረች ለሰማዕትነት ከሚሔዱት ጋር በመሔድ ወደ እንጽና ከተማ በደረሰች ጊዜ ስሙ ፍልፍልያስ በሚባል መኰንን ፊት ቆመች በአያትም ጊዜ ስለታናሽነቷ ራርቶላት ሊተዋት ወደደ። ሊተዋትም እንደወደደ ዐውቃ እርሱንና የረከሱ አማልክቶቹን በድፍረት ረገመች። ስለዚህም መኰንኑ ተቆጥቶ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃያት ከቀናች ሃይማኖቷ ሸንግሎ ይመልሳት ዘንድ በተሳነው ጊዜ ጊንጦችን፣ እፉኝቶችንና እባቦችን ሰብስበው በዳውላ ውስጥ እንዲጨምሩአቸው እርሷንም ከእርሳቸው ጋር በዳውላ ውስጥ እንዲጨምሩት አጥማጆችን አዘዛቸው እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።
❤ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸላትና ከጌታችን ዘንድ የተሰጣትን ቃል ኪዳን አስረከባት ከዚህም በኋላ ነፍሷን አሳረፈች የምስክርነት አክሊልንም ተቀበለች ከዳውላውም ውስጥ አውጥተው በዚያች ቦታ ቀበሩዋት። ከዚህም በኋላ አባቷና እናቷ በሰሙ ጊዜ ሥጋዋ ወዳለበት ከብዙ ሕዝብ ጋር መጡ ከዚያም ሥጋዋን አፈለሱና ወሰዱአት በታላቅ ክብርም ገንዘው በአማረች ሣጥን ውስጥ አኖሩዋት በሥውር ቦታም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠሩላት ከእርሷም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ምህራኤል በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_አርኬሌድስ፦ ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገር ከታላላቆች ወገን ነው የአባቱም ስም ዮሐንስ የእናቱም ስም ሰንደሊቃ ነው ሁለቱም ዕውነተኞች የሆኑ በእግዚአብሔር ሕግ ያለ ነቀፋ የጸኑ ናቸው። ቅዱስ አርከሌድስም ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ ሞተ እናቱም ሚስት ልታጋባው አሰበች እርሱ ግን ይህን አልወደደም። አባቱ በሕይወት ሳለ ንጉሡ የሾመው ነበርና እናቱ አሁንም ወደ ንጉሡ ሄዶ የአባቱን ሹመት ይቀበል ዘንድ አርከሌድስን መከረችው፡፡ ለንጉሡ የሚሰጥ እጅ መንሻንና አገልጋዮችን አድርጋ ብዙ ገንዘብ አስይዛ ላከችው፡፡ እርሱም በመርከብም ተጭኖ ሲሄድ ታላቅ ንፋስ ተነሣና ማዕበሉ አየለባቸው፡፡ መርከቡም ተሰበረ፡፡
❤ ቅዱስ አርከሌድም አንዲት የመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠልጥሎ ወደ የብስ ደረሰ፡፡ ከባህሩ ሲወጣ ማዕበል የተፋው አንድ በድን አገኘና ተቀምጦ ስለ በድኑ አለቀሰ፡፡ የዓለምን ኃላፊነትና እርሱም ከሞተ በኋላ አፈርነቱን አሰበ፣ ነፍሱንም ገሠጻት፡፡ ወደ ቀና መንገድ ይመራውም ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ፡፡ ረጅም መንገድ ተጓዘና ሶርያ ውስጥ በቅዱስ ሮማኖስ ስም ወደተሠራች አንድ ተራራማ ገዳም ደረሰ፡፡ ከገንዘቡም ከእርሱ ጋር የቀረውን ሁለት መቶ የወርቅ ዲናር ለአበ ምኔቱ ሰጠው፡፡ እንዲያመነኩሰውም ጠየቀው፡፡ መጀመሪያውኑ አርኬሌድስ ከመምጣቱ በፊት ለአበምኔቱ መንፈስ ቅዱስ የመምጣቱን ነገር አስረድቶት ነበርና እርሱ በደረሰ ጊዜ ደስ አለው፡፡ መነኰሳቱም ሁሉ ከጸለዩለት በኋላ አመነኰሰው፡፡
❤ ከዚህም በኋላ የከበረ አርከሌድስ ጽኑ ተጋድሎ መጋደል ጀመረ፡፡ ሲጸልይ ይውላል ሲጸልይ ያድራል፤ ሁልጊዜ በየሰባቱ ቀን የሚጾም ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም ሀብተ ፈውስን ሰጥቶት ብዙ ሕመምተኞችን ፈወሳቸው፡፡ ከዚህም በኋላ የሴቶችን ፊት ከቶ እንዳያይ ከጌታችን ጋር ቃል ገባ፡፡ እናቱም ለ12 ዓመት ያህል የልጇን ወሬ ምንም ስላልሰማች በእርሱ የሆነውን አላወቀችም ነበርና የሞተም ስለመሰላት እጅግ አዘነች፡፡ የእንግዶችና የመጻተኞች መቀበያ የሚሆን ቤት ሠርታ የመንገደኞች ማደርያ አደረገችው፡፡
❤ በአንዲት ዕለት ያሳደረቻቸው እንግዶች የቅዱስ አርከሌድስን ዜና ሲናገሩ ሰማቻቸው፡፡ እንግዶቹም ስለ ቅድስናው፣ ስለ ተጋድሎው የሚያሳያቸውን ምልክቶችና ተአምራቶቹን፣ የመልኩንም ደም ግባት ሲነጋገሩ ሰምታ ልጇ እንደሆነ ዐወቀች፡፡ መንገደኞቹንም ስለ ሥራው ጠየቀቻቸውና ሥራውን ሁሉ ነገሯት፡፡ ልጇ በሕይወት እንዳለና ሕያው እንደሆነ ተረዳች፡፡ በዚያን ጊዜ ተነሥታ ወደ ከበረ ሮማኖስ ገዳም ሄደች፡፡ ወደ ልጇዋ ወደ ቅዱስ አርከሌድስ "እነሆ ፊትህን አይ ዘንድ ወድጄ እኔ እናትህ መጥቻለሁ" ብላ መልእክት ላከች፡፡ ልጇ ቅዱስ አርከሌድም "ከቶ የሴቶችን ፊት እንዳላይ ከክብር ባለቤት ከባለቤት ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ቃል ገብቻለሁና ቃልኪዳኔን ማፍረስ አይቻለኝም" ብሎ መልሶ ወደእርሷ ላከ፡፡ እናቱም "ፊትህን ካላሳየኸኝ እኔ ወደ ዱር እሄዳለሁ፣ አራዊትም ይበሉኛል" ብላ ላከችበት፡፡ ቅዱስ አርከሌድስም እናቱ ካላየችው እንደማትተወው እርሱም ለእግዚአብሔር የገባውን ቃልኪዳን ማፍረስ እንደማይቻለው ባወቀ ጊዜ ነፍሱን እንዲወስዳት ወደ ጌታችን ለመነ፡፡ ከዚህም በኋላ የበሩን ጠባቂ "እናቴን ወደእኔ ትገባ ዘንድ ፍቀድላት" አለው፡፡ እናቱም ወደ ውስጥ በገባች ጊዜ ልጇን ቅዱስ አርከሌድስን ሙቶ አገኘችውና በታላቅ ድምፅ በመጮህ አለቀሰች፡፡ የእርሷንም ነፍስ ይወስድ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመነች፡፡ ጌታችንም ልመናዋን ተቀብሎ ነፍሷን ወሰደ፡፡