"ተውት እሱ እግሩ ቀጭን የደሀ ልጅ ነው ኳስ ተጫዋች ከመሆን ይልቅ ምግብ መግቡት " ብለው በድህነቱ ላይ ቀለዱበት። የሚጫወትበት ጫማ እንኴን አቶ የሀብታም ልጆች ተጠቅመው የጣሉትን እሱ ይለብሳል። ርሀብ ሲጠናበት ባቅራቢያው ወደሚገኝ ማክዶናልድ ሄዶ ትርፍራፊ ካለ ይለምናል።
እያልን ካወራን ብዙ ነው ይህ ሰው ዛሬ ምድር ላይ ተፈጠሮ ከኖረም ሆነ አሁን ላይ በሂወት ካለ ሰው ከተባለ ዘር ሁሉ የሱን ያህል ታዋቂ የለም አልነበረም አሁንም የለም በምድር ከሚኖረው ስምንት ቢሊዮን ህዝብ 83% እሱን ያውቀዋል ሲል ፎርብስ ለአለም ህዝብ ጥናቱን ስለሱ አበሰረ።
ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ሶስት ነገሮችን መማር ካልቻልክ አምልጦሀል።
1. መነሻህ የቱንም ያህል ፈታኝ ከባድ እና አሳዛኝ ቢሆንም ያጠረህ ድህነት ችግር ሳይሆን ህልምህ ነው ማድረሻ ገመድህ
2. ቆራጥ ለህልሙ ኑዋሪ በህልሙ ላይ ምንም ነገር ቢመጣ ሰልችቶ የማይቆም እጅግ ታታሪ መሆን አለብህ
3. የደረስክበት ስኬት በቃኝ አትበል ይበልጥ በርታ ይበልጥ ሞክር ይበልጥ ስራ ልበቀና ለሌሎችም ደራሽ ሁን። አንድ ታቱ በሰውነቱ አልተነቀሰም ምክንያቱም ቋሚ የቀይ መስቀል ደም ለጋሽ ነው የተሰጠውን ሽልማት ሸጦ ፍትህ ለተነፈጉት ፍልስጤማውያን ሰጠ ስለነሱ ሲል ከእስራኤይ ብሄራዊ ቡድን ጋር አልጫወትም አለ የአለማችን ለጋሱ ስፖርተኛም ነው።
ስኬትህ ላይ ስትደርስ እንዳንተ መነሻ እርዳታ ለሚሹ እጅህን ዘርጋ ከመናቅ እስከ መንገስ የሱ ሂወት ሁሌም አነቃቅቶኛል ጠቅሞኛል ራሴን እንዳይ አድርጎኛል። ችግር ይሁን መገፋት ርሀብ ይሁን መታረዝ መናቅ ይሁን መሰደብ የቱም ሀይል ለአላማህ ቆራጥ ከሆንክ አያስቆምህም።❤❤
Subscribe our channel
youtube.com/@jesus_lights
youtube.com/@jesus_lights