የመቐለ 70 እንደርታ የቡድን አባላት በሕመም ላይ ለሚገኙት የመቐለ 70 እንደርታው ምክትል አሰልጣኝ ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ የ600 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት በኢትዮጵያ እግርኳስ የራሱን አሻራ ያሰፈረው የቀድሞ የትራንስ ኢትዮጵያ እና ዋልታ ፖሊስ ትግራይ እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ በመሥራት ላይ የነበረው ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ በአሁኑ ወቅት በካንሰር በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ታሞ ይገኛል። በመሆኑም ሕክምናው በሀገር ውስጥ የማይሰጥ ስለሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ ወጥቶ እንዲታከም የሕክምና ባለሙያዎች ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በመሆኑም ለሕክምናው ውጭ ሀገር በመሄድ እንዲታከም ለመላው የስፖርት ቤተሰብ የቀረበውን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋቾች እና የአሠልጣኝ ቡድን አባላት መዋጮ በማድረግ የ600 ሺ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል። ሌሎች ክለቦችም ይህንን መልካም አርዓያ ያለውን ተግባር ተቀላቅለው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ድጋፍ ለማድረግ 👇
ወ/ሮ ትብለፅ ገብረመስቀል
👉 የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ | 1000184557375
👉 ወጋገን ባንክ | 0952411530101