😍 አርቲስቶች ፣ ድምፃውያን ፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮችን በጎፈሬ ማሊያ ለማየት ዝግጁ ናችሁ? 🤩ጎፈሬ የታዋቂ ሰዎች አዝናኝ የስፖርት ፌስቲቫል ውድድርን አጋር ሆነ
በቅዳሜ ሚዲያ እና አድቨርታይዚንግ አዘጋጅነት በአርቲስቶች ፣ ድምፃውያን ፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች መካከል ደማቅ ስፖርታዊ ውድድር ሊደረግ ቀን ተቆርጦለታል። ውድድሩ እንደ ፌስቲቫልነቱ አዝናኝ ከመሆኑ ባሻገር ለመቄዶንያ የአረጋዉያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ገቢ የማሰባሰቢያ በጎ ዓላማ ይዞ በደማቅ ሁኔታ ሚያዚያ 23 እና 26 የሚከናወን ይሆናል።
የኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነው ጎፈሬም ውድድሩን በምርቶቹ እና በሽልማቶች ለማድመቅ የሁለት ዓመት የአጋርነት ስምምነት በዛሬው ዕለት ከቅዳሜ ሚዲያ እና አድቨርታይዚንግ ጋር ተፈራርሟል።
ዛሬ ቀትር ላይ በሀርመኒ ሆቴል በርካታ የጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ስርዓት እና ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ቅዳሜ ሚዲያ ከጎፈሬ ጋር ስምምነቱን ከፈፀመ በኋላ የአርቲስቶች፣ የድምፃውያን፣ የጋዜጠኞች እና የቲክቶከሮችን ቡድን በመወከል የቡድኖቹ አምበሎች ከውድድሩ በፊት የቃላት ጨዋታ የጀመሩበትን ፍልሚያ ከመድረክ ሆነው ጀምረዋል።
@goferesportswear